TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮማንድ ፖስት‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር #የተጠረጠሩ 171 ሰዎች #በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ገንዘብም በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉ ተመልክቷል፡፡

የአካባቢውን ሠላም ለመመለስ የተቋቋመው ኮማን ፖስት አባል እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል #ጌትነት_አዳነ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ኮማንድ ፖስቱ ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከተቋቋመበት ጊዜ አንሰቶ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየሰራ ነው።  

በእዚህም በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች በታጠቀ ኃይል ተፈጥሮ በነበረ የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት የተጠረጠሩ 171 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች የተያዙት ግጭት ከተከሰተባቸው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን እና ቶንጎ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ደግሞ ምዕራብ ፣ ምስራቅና ቄለም ወለጋ፣ ሆሩ ጉድሩ፣ ኢሉአባቦራ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል በየደረጃው የሚገኙ #አመራሮች እንደሚገኙበት ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

የታጠቀው ኃይል ለግድያ እና ሌሎች #ጥፋቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ 49 ክላሽንኮብ ጠመንጃዎችና 1 ሺህ 31 የተለያዩ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሎኔል ጌትነት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦቹ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቀሱት የነበረ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር እና 12 ሺህ ዶላር ኮማንድ ፖስቱ መያዙን ነው ያስረዱት።

እንደ ኮሎኔል ጌትነት ገለጻ የጥፋት ኃይሎቹ ተጨማሪ ጥቃት ለመፈጸም ያዘጋጁት ሰባት ጸረ-ተሸከርካሪ ፈንጂዎች፣ 215 ቀስቶች እና የተለያዩ ኮምፒዩተሮችም ተይዘዋል፡፡

ታጣቂ ኃይሉ ከመንግስት መዋቅሮች እና ከግለሰቦች አስገድዶ በመውሰድ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ዘጠኝ አምቡላንሶች፣ አራት አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ ሦስት ቶዮታ ፒክአፕ መኪኖችም ኮማንድ ፖስቱ ማስመለሱን ነው የገለጹት፡፡

ቡድኑ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበረውን ንብረት ከማስመለስ ጎን ለጎን በጉዳዩ ላይ ሕብረተሰቡን የማወያየት ሥራ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት አስረድተዋል፡፡

የጸጥታ ችግር ሲከሰትባቸው በነበረባቸው ዞኖች በአሁኑ ወቅት ግጭት ሙሉ ለሙሉ ቆሞ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ጠቅሰዋል፡፡

ህብረተሰቡ ያደረገው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት ጠቁመው ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ ችግሩ እንዳይደገም አደረጃጀቱን ከህብረተሰቡ ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አጎራባች አካባቢ የደፈረሰውን ሠላም ለመመለስ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከፌደራልና ከሁለቱ ክልሎች መንግስታት እንዲሁም ከሀገር መከላከያ እና ከፌደራል ፖሊስ ሠራዊት የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvqhethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥረው በቀረቡ ግለሰቦች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን #ፎቶ_በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ፍርድ ቤቱ በድብቅ በመግባት ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሲያሰራጩ ነበር ተብለው #የተጠረጠሩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው በአሁን ወቅት ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን፥ በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፍጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ምስክርነት በመስጠት በፍርድ ቤት ቅድመ መርመራ ላይ እያሉ ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ #በማሰራጨት ስጋት ለመፍጠርና እንዲሸሹ ለማደረረግ መሞከራቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስም በአሁኑ ወቅት የምስክሮችን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር በቂ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተመለከተው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ🔝

በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ #በድጋሜ የእሳት ቃጠሎ ተከሰተ። ባለፋት ሳምንታት ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሁ በጥበቃ ቦታው ላይ የዚህ አይነት የእሳት ቃጠሎ በመነሳት ስፋት ያለው በአስታ ደን የተሸፈነ የፓርኩ አካል መውደሙ የሚታወቅ ነው።

በሌሎቹ የጥበቃ ቦታዎቻችንም ቢሆን እንዲሁ የዚህ አይነት ቃጠሎ በሰው ሰራሽ ችግር ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፓሊስ፣ በፈቃደኛ ወጣቶችና በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እርብርብ እየተደረገ የተነሳውን እሳት መቆጣጠሩ የተለመደ ነው።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በአገራችን ከሚገኙት ከፍተኛ ተራሮች መካከል የቱሉ ዲምቱ እና የሰናቴ ፕላቶዎች የሚገኙበት በመሆኑ አብዛኛው የመሬቱ አካል በአስታ ዛፎች የተሸፈነ ነው። በተጨማሪም የዚህ እጽዋት ዝርያዎች በቀላሉና በፍጥነት በእሳት የሚቀጣጠል ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ስሩ አካባቢ ያለው ግንድ እሳቱን ይዞ ስለሚቆይ የጠፋ ይመስልና ንፋስ ሲያገኝ እንደገና ይቀጣጠላል። ይህ ባህሪው አካባቢውን ከእሳት ለመታደግ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

አሁን ላይ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን እንደተለመደው እሳቱን ለመቆጣጠር የፀጥታ ሃይሉና ህብረተሰቡ ወደ ቦታው በመሄድ እሳቱን እያጠፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቃጠሎውን መንስሄ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት የአካባቢው ፓሊስ #የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ #ቁጥጥር_ስር አውሎ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን የፓርኩ ሃላፊ አቶ አስቻለው ገልፀውልናል።

Via ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Monkeypox (Africa) የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል። እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች…
#Monkeypox

(Ethiopia)

በኢትዮጵያ ፤ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ሳይያዙ አልቀሩም ተብሎ #የተጠረጠሩ 2 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ምንም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር / ኬዝ ካለበራቸው አሁን ላይ የተጠረጠሩ ኬዞችን ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ካደረጉ 7 ሀገራት አንዷ ናት ተብሏል (ሀገራቱ ኢትዮጵያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሞዛምቢክ ፣ ሴራሊዮን ፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ናቸው) ።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ናሙናቸው ውጭ ሀገር ተልኮ የምርመራ ውጤቱ እስኪታወቅ በለይቶ ማቆያ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን ገለሰቦቹ ከፍተኛ የቆዳ በሽታ ምልክት ይታይባቸዋል ነው የተባለው።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣን ከሁለቱ አንደኛው ግለሰብ አሁን ላይ ከዝንጀሮ ፈጣጣ ውጪ የሌላ ምልክት እያሳየ ነው ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መመርመሪያ የሌላት ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ናሙና መቼ ወደውጭ ሀገር እንደተላከ እንዲሁም ውጤቱ መቼ እንደሚደርስ የታወቀ ነገር እንደሌለ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia