TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ያለውን የገቢና ወጪ ንግድ #ለመቆጣጠር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ነዳጅን ጨምሮ በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ #ገደብ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ፦

ከትላንት ህዳር 8ቀን 2011አ.ም ከሰአት በሃላ እና ህዳር 9ቀን እረፋድ ላይ በቀበሌ 09 ፖሊስ መሬትና #መጋላ_ጨብጡ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ አሁን ላይ መነሻ ምክንያቱን እያጣራው ያለው ግጭትና ሁከት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም ግጭት በህክምና ጭምር የተረጋገጠ በስለት ጉዳት ጉዳት ደርሶበት የ1ሰው ህይወት ሲያልፍ በ2 ቤቶች ላይ ቀጠሎ እንዲሁም በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስና ከመከላኪያ ጋር በመሆን ግጭቱ ወደ 01 ቀበሌ መልካ ጀብዱ የመስፋፋት አዝማሚያ መታየቱን ተከትሎ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ለመቆጣጠርም ችሏል።

በአሁን ወቅት ችግሩ በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ተገቢው ፀጥታን #የማረጋገጥና ሰላምን የማስፈን ስራ እየተሰራ ሲሆን ተፈጥሮ የነበረውን
ግጭትና ሁከትም አሁን ላይ ለማስቆምና #ለመቆጣጠር ተችሏል።

በመሆኑም መላው ህብረተሰብ ወደ ግጭት ሁከትና መረበሽ ሰዎችን እንዲያመሩ ከሚያደርጉ አንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችና
ያልተረጋገጠ መረጃ ከሚሰጡ ዘገባዎች እራሱን በመጠበቅ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን የማረጋገጥ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጨምሮ ጥሪውን ያቀርባል።

ህዳር 9/2011 አ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት #ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት #መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ #ልኪቱ_ተፈራ ይናገራሉ።

"መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ።

ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል።

ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ።

በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ።

ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል።

በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ።

'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው #የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን #ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይነበብ‼️

የትምባሆ፣ የአልኮል ፣ የመድኃኒትና ምግብ ነክ ምርቶችን #ለመቆጣጠር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ #የበለጠ_ጥብቅ እንዲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን ጠየቁ።

ካቀረቧቸው ጥብቅ የማሻሻያ ክልከላዎች መካከል፦

1. የአልኮል ምርቶች #በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ(ማለትም በሬዲዮናበቴሌቪዥን)
ሙሉ ለሙሉ እንዳይተዋወቁ ክልከላ እንዲጣል

2. የአልኮል ምርቶች ማለት የአልኮል ይዘታቸው ከሁለት በመቶ በላይ መሆኑን የሚገልጸው የረቂቅ አዋጁ ትርጓሜ ተሻሽሎ የአልኮል ይዘቱ ከ0 .5 በመቶ በላይ በሚል እንዲሻሻል ለዚህ ያቀረቡት ምክንያትም አልኮል የሚያመርቱ ኩባንያዎች ከሁለት በመቶ በታች የሆኑ የአልኮል ምርት ዓይነቶችን በማምረት የአልኮል መጠጦች በተጠቀሱት ሚዲያዎች እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

3. የአልኮል መጠጦችን ለማስተዋወቅና ገበያውን ለማስፋት ከፍተኛ #ሽልማቶችን_የሚያስገኙ ዕጣዎችን በቆርኪ ላይ ማያያዝ ክልከላ እንዲደረግበትም ሐሳብ አቅርበዋል።

4. የትምባሆና አልኮል ሽያጭን በተመለከተ ረቂቅ ሕጉ ላይ ሁለቱም ምርቶች ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች እንዳይሸጡ የሚደነግገውአንቀጽ ተሻሽሎ ከ21 ዓመት በታች እንዲባል ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሕዝባዊ ውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ወጣት ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ረቂቅ አዋጁ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆንና የአልኮል ማስታወቂያ እንዲቆም በተደጋጋሚ በመጠየቃቸው ነው።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአገር መከላከያ ሰራዊት‼️

የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የመለያ ደንብ ልብስ የቀለምና የዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀኔራል #አብዱራህማን_እስማኤል ገለጹ።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ በሰራዊቱ ስም #ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን #ለመቆጣጠር ያስችላልም ተብሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ለኢዜአ እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ የቀለምና ዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት ነው።

ፋውንዴሽኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 179/2002 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሰራዊቱ አልባሳትና ሌሎች ወታደራዊ ግብዓቶችን በማምረት ወይም ገዝቶ ያቀርባል ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚወዱት፣ በጥራት፣ በቀለምና በዲዛይን የተሻለ የመለያ ልብስ እንዲሆን ከተለያዩ አገሮች ተመክሮ መወሰዱን ገልጸዋል።

የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #ተሾመ_ገመቹ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊቱን አልባሳት መልበስ የሚችለው የሰራዊቱ አባል ብቻ ቢሆንም ተገቢ ቁጥጥር ባለመደረጉ የማይመለከታቸው ግለሰቦች ለብሰውት ተስተውሏል።

አዳዲስ አልባሳት በሚቀርቡበት ወቅት አሮጌዎቹ በአግባቡ ሳይወገዱ በመቅረታቸው ልብሱ በማይመለከታቸው አካላት እጅ ገብቶ የሰራዊቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ የተለያዩ ወንጀሎች እየተፈጸሙበት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣይ በሰራዊቱ አልባሳት ላይ የሚደረገው የቀለም ለውጥ እንዲሁም አዲስ አልባሳት ሲሰጥ ችግሩን ለመፍታት የሚያስቸሉ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ነው ያመለከቱት።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት ካሉ በወንጀል እንደሚጠየቁ ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡም የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ መልበስ የሚችለው ሰራዊቱ ብቻ መሆኑን ተረድቶ የማይገባውን ልብስ ባለመልበስ ወንጀል እንዳይፈጸም ሊተባበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ወላይታ ሶዶ‼️

ከሩፋኤል ዝቅ ብሎ ወይም ሀቢታት አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የአየሩ ሁኔታ ንፋስ የተቀላቀለበት በመሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎታል። የአካባቢው #ህብረተሰብ እሳቱን ሙሉ በሙሉ #ለመቆጣጠር እና #እንዳይሰፋ ለማድረግ ከፍተኛ #ጥረት እደረገ ይገኛል። የሚመለከታችሁ አካላትም ይህን ጥቆማ ሰምታችሁ ትብብር እድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

©z(TIKVAH-ETH ወላይታ ሶዶ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በሀላባ ቁሊቶ በሚገኘው #ፖስታ_ቤት #የእሳት_አደጋ መድረሱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የአደጋው ምክንያት ባይታወቅም እሳቱን #ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስሜን ተራሮች🔝

የስሜን ተራሮች ቃጠሎ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው:: የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ግጭ አካባቢ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እየተቃጠለ ነው። በፓርኩ አስተርጓሚና አስጎብኝ የሆነው ወጣት አስረሳኸኝ ሞላ ለአብመድ እንደገለፀው ቃጠሎው ሰፊ ቦታን ያካለለና #ለመቆጣጠር የከበደ ነው።

ከትናንት ጀምሮ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከዛሬ እኩለ ቀን በኋላ ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግራል። በቃጠሎው ምክንያት በአካባቢው ያለውን ማረፊያ ካምፕ ጥለው መውጣታቸውንም ነግሮናል።

የፓርኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ደግሞ እሳቱ በከፍተኛ ነፋስ እየታገዘ በመሆኑ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ተናግረዋል። በተለይ ከቀኑ 6:00 ገደማ ጀምሮ እሳቱ ሰፊ ቦታን እያካለለ መሆን ተናግረዋል።

ከፍተኛ የሰው ኃይል እሳቱን ለመቆጣጠር መሠማራቱን የገለጹት አቶ ታደሰ ምግብ እየቀረበላቸው አሁንም ከዚያው ሥራ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara እጅግ አስከፊ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ገና ያላገገመው አማራ ክልል ዳግም የግጭት ቀጠና እየሆነ መምጣቱና የፀጥታውም ሁኔታ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በ " ፋኖ " የታጠቁ ኃይሎች እና በ " መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች " መካከል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት አልፏል፤ ጉዳትም ደርሷል። በተለይ ከጥቂት ወራት ወዲህ " የክልሉና የአማራ…
#NewsAlert

የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር ጥያቄ አቀረበ።

የክልሉ መንግሥት ፤ ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት #ለመቆጣጠር_አዳጋች ሆኖ መገኘቱን ገልጿል።

በዚህም የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር ይፋዊ ጥያቄ አቅርቧል።

በክልሉ የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

" የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል " ያለው የአማራ ክልል መንግሥት ፤ " የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት ፤ ንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው ህግ የማስከበር ስርዓት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር " ሲል ጥይቄ አቅርቧል።

" ክልሉ ወደ ቀደመው መረጋጋቱ እንዲመለስ ፤ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል " በሚል የአማራ ክልል መንግሥት የፌደራል መንግስትን መጠየቁ ተነግሯል።

@tikvahethiopia