TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰላም እና መረጋጋት እየታየ ነው...

በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች #መረጋጋትና #ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተገለፀ።

የአማራ ክልል ሰላም እና ደህንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት፥ የፀጥታ ችግሩ ተከስቶባቸው በነበሩ በሁሉም አካባቢዎች መረጋጋት እና ሰላማዊ ሁኔታ ታይቶባቸዋል።

የአካባቢውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ለመመለስ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁት ኮሎኔል አለበል፥ አጥፊዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አሁንም ቢሆን ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት እና ችግሩን ለማባባስ የተለያዩ ያልተጣሩ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች በመኖራቸው ህዝቡ ከወዲሁ መጠንቀቅ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ግጭቶቹ የተከሰቱባቸው አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የተሻለ መረጋጋት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

እንደ አስተያት ሰጭዎቹ፥ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ተደናግጠው አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ፈረዶ ውኃ እና መሀል ሜዳ ሸሽተው የነበሩ የአጣየ ከተማ ቀበሌ 01፣ 02 እና 03 ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው፡፡

በማጀቴም ከትናንት የተሻለ ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia