TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር #ሊያ_ታደሰ የኤርትራውን ሆሮታ ሪፍራል እና ቲቺንግ ሆስፒታል ጎበኙ፡፡ ለነፃ የህክምና አገልግሎት ወደ ኤርትራ የተጓዘውን የሀኪሞች ቡድን በመምራት ወደ አስመራ ተጉዘው የነበሩት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ኤርትራ የተላከው የሀኪሞች ቡድን በአስመራ በሚገኘው ኦሮታ ሪፈራል እና ቲቺንግ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካንሰር ቀን‼️

በኢትዮጵያ ያለው #የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ፡፡

ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ #ደሀ አገራት ላይ #ይበረታል ተብሏል፡፡

ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸው ካንሰርን የመከላከል ስራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአለም የካንሰር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰናዱት ምክክር ላይ ነው ይሄን የሰማነው፡፡
በኢትዮጵያ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች 65 ሺ ያህል ሰዎችም ይሞታሉ፡፡

ለህክምና የሚሆኑ ግብአቶች አለመሟላት እና የህክምና ተቋማቱ አነስተኛ መሆን ካንሰርን ለመከላል የሚሰራውን ስራ ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው የጤና ሚኒስትር ድኤታዋ ዶ/ር #ሊያ_ታደሰ ተናግረዋል፡፡

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ እንደሆነና የህክምና ግብአቶች እየተሟሉላቸው ነው መባሉን ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia