TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትን #ለማጠናከርና ለነዋሪዎቹና ለአባላቱ የቅርብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል 1ሺ 332 የሸማቾች ሱቆችን ለመገንባት ቦታዎች ተለይተው ወደ ግንባታ እየተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #ሲሳይ_አረጋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ሱቆቹ የሚገነቡት በ243 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲሆን፤ የግንባታውን ወጪ የሚሸፍኑት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ይሆናሉ፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia