ቢሾፍቱ🔝
16ኛዉ የጠቅላይ አቃቤ ህግና የክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ #በቢሾፍቱ እየተካሄደ ነዉ። "የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለፍትህ ስርአቱ ተግተን እንሰራለን!" በሚል መሪቃል በሚካሄደው ስብሰባ በተለይ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ከህግ የበላይነት መከበር ጋር የተያያዙ ነገሮች ትኩረት ተሰጥቶ ምክክር እንደሚደረግባቸው etv ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የአገር መከላከያ ሰራዊት ባለፉት 100 ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ #ምርጥ ስራ ከሰሩ ተቋማት መካከል ዋነኛው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያን ከልዕልናዋ ለማውረድና ለመድፈር ተሞክሮ የመከላከያ ሰራዊቱ ሰንፎ ያሳለፈበት ጊዜ የለም። ባለፉት ወራት ክልሎች ሰላምን ለማረጋገጥ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ችግሮች ሲገጥሟቸው ሰራዊቱ ገብቶ #መስዋእትነት በመክፈል #ማረጋጋት መቻሉንም አስታውሰዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የክልል እና የዞን ጥያቄዎችን በተመለከተ‼️
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናገሩ።
በአሁኑ ወቅት በርካታ የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በህጋዊ መንገድ ማቅረብና መደመጥ መቻል በራሱ የዴሞክራሲ መብት አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ይሁን እንጂ ዞን ወይም ክልል የሚለው ጥያቄ ከመመለሱ በፊት የጥያቄዎቹ ዋና ዓላማ፤ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱን መታየት አለበት ብለዋል።
የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥም ይኖርበታል ብለዋል።
ይሁን እንጂ የክልልና የዞን ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው፤ የጥያቄው አግባብነት እስከሚታይ #መታገስ እንጂ በህገ-ወጥ መንገድ ይመለሳል ብሎ መንቀሳቀስ #አዋጭነት_የለውም ብለዋል።
መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ጥናት ላይ ተመስርቶ በህጋዊ መንገድ ለመፍታት የምናየው ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።
“የሚወሰነው ውሳኔም የሚያዋድደን፣ አንድ የሚያደርገን እንጂ የሚያጣላን መሆን የለበትም” ሲሉም ተናግረዋል።
“ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ጫፍ ከሌላው ጋር ተሳስሮና ተደጋግፎ መሄድ ካልቻለ #መቀጠል አይችልም፣ ህይወታችን በራሱ #ተደጋግፈን እንድንቀጥል ያደርገናል” ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ🔝
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተነሳው #እሳት ጉዳት ሳያደርስ #ጠፍቷል፡፡ ደብረ ብርሐን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ ቃጠሎው የተነሳው በግቢው ውስጥ ከተከማቸ ቆሻሻ ላይ መሆኑን አብመድ ዘገቧል። ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባደረጉት ጥረትም ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

#update ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በከተማ አስተዳድሩ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የከተማ ግብርና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አሰግድ ኃ/ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት በከተማዋ እየተበራከቱ የመጡ ባለቤት አልባ ውሾችን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለማስወገድ በጋራ እየሰራ ነው። ባለቤት አልባ ውሾቹ በህብረተሰቡ ላይ የሚደርሱትን የጤና ስጋት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑንም አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡
via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ዞን ፖሊስ‼️
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ኤፌሶን¥ላካይቶ እንደገለጹት በዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት በተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀል የተጠረጠሩና እጅ ከፍንጅ የተያዙ በቁጥር 50 የሚሆኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ለማድረግና የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማስቻል መምሪያው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለውጡን የማይቀበሉ አንዳንድ አካላት በሚፈጥሩት የፀጥታ መደፍረስ የተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀሎች እየተበራከቱ በመሆናቸው ችግሮችን ለመቅረፍ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የሚፈጸሙ #የስርቆትና #የንጥቂያ ወንጀል #በዘላቂነት ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማወያየትና በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በጉኑኖ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሌሊት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ፖሊስ ያደረገውን ጥረት ጥቂት የሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ‹‹እኛን መቆጣጠር አትችሉም›› በማለት ሁከት ፈጥረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ሁከት ፖሊስ ከከተማው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት #በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
በከተማው ሁከት የፈጠሩ፣ የተሳታፉና የመሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ የምርመራ ሂደት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
በሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ በቡድን ተደራጅተው #በስርቆት ወንጀል የተሰማሩ 9 ግለሰቦች ለህግ ቀርበው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በዋዱ አከባቢም በተመሳሳይ ወንጀል ተሰማርተው የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማሽከርከር እንደሌለባቸው ያሳሰቡት ምክትል ኮማንደር ኤፌሶን ሌሊት ማሽከርከር ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
በየአካባቢው ህብረተሰቡ ከወትሮው የተለየ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም ለዞኑ ፖሊስ በ046-551-21-26፣ ለሶዶ ከተማ ፖሊስ 046-551-01-46፣ ለሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ 046-551-00-22 የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office

Fake News‼️
"በጅግጅጋ ከ59 ሰዎች በላይ ተገደሉ። 7 ከፍተኛ ባለስልጣት በቁጥጥር ስር ዋሉ።" በሚል በፌ ቡክ እና በዩትዩብ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው።

#update 24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታወቀ፡፡ የአየር ድብደባው በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ሸቢሌ አካባቢ በሚገኝ የመጠለያ ጣቢያ ላይ መሆኑን የአሜሪካ-አፍሪካ ኮማንድ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፦ /አል-ጀዚራ/~AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ /አል-ጀዚራ/~AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት‼️
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
ለቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት መመስረት በነበራቸው ታላቅ የመሪነት ሚና የመታሰቢያ ኀውልት እንዲቆምላቸው መወሰኑ ይታወቃል።
የኀውልቱ ግንባታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላመ የስነ ጥበብ ባለሙያዎች መከናወኑን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት በ32ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ይመረቃል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው እንደገለፁት የኀውልቱ መቆም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት መመስረት ላመረከቱት ጉልህ አስተዋፆ መታሰቢያነት ነው።
አፍሪካውያን አንድ ሆነው በመቆም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ፤ ህብረቱ እንዲመሰረት በማድረግ ላደረጉት ትግል እውቅና ለመስጠት የተሰራም ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ በሚካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በርከት ያሉ የተለያዩ አገራት መሪዎችና ድፕሎማቶች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ‼️
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው።
መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለፖለቲካ ጥቅም የማዋል ዝንባሌ እንደሚኖር ቀድሞ ተረድቶ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ውይይት ቢያደርግም በተወሰኑ ተቋማት ግጭቶች ተከስተው የተማሪዎች ህይወት መጥፋቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታሰዋል።
“በመሆኑም ተማሪዎች የማንም ፖለቲካ ኃይል ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ እራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው” ሲሉ ምክር ሰጥተዋል።
“ተማሪዎችን እሳት እያስጨበጡ የፖለቲካ የበላይነት ለማምጣት የሚፈልጉ ሃይሎች፤ ተግባራቸው ህገ-ወጥና ጊዜው ያለፈበት መሆኑን በመገንዘብ እጃቸውን ይሰብስቡ” ሲሉም አሳስበዋል።
ከተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም ህብረተሰብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመሰል ሁኔታዎች ጸድተው የስልጠናና ምርምር ማዕከል እንዲሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቀርበዋል።
መንግስት #አጥፊዎችን #ለህግ ከማቅረብ በተጨማሪ የህግ የበላይነን ለማስፈን ከመቸውም ጊዜ በላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ena