መከላከያ ሰራዊት🔝
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰባተኛ ጊዜ "ህገ-መንግስታዊ ስርአታችንን ለማክበርና ለማስከበር #የሰላም ደውል እናሰማለን" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በተለያዩ መረሀ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡ በትላንትናው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ ከሀይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌ የህብረተሰብ ተወካዮች የሰራዊቱ ቤተሰብ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ችግኝ ተካለ እና የምስራቅ እዝ ሶስተኛ ደረጃ ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ #ህሙማንን ጉብኝተዋል፡፡
Via Dire ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

እሁድ ጥር 26 በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ወይም ከዋናው ፖስታ ቤት ፊት ለፊት በዕለቱ በምናደርገው የካንሠር ግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ ላይ በመገኘት አብረውን ያክብሩ።
Join us by attending our cancer awareness walk this Sunday, January 3 at Ethio-Cuba Friendship Memorial Park / In front of the Main Post office.
For More Information:
+251 118 12 2838 / +251 923 79 7899
[email protected]
https://www.facebook.com/events/356524791744641/
#WorldCancerDay
#IamAndIWill

#update የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡ መልካም ግንኙነት የተፈጠረበት አዲስ ጎረቤት ሃገር እና ሌላ አዲስ ሀገር (ደቡብ ሱዳን) መኖሩም ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ!
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
#ታላቁ_ሩጫ_በኢትዮጵያ በተሰጠው መግለጫ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው "እኔም የመሪነት ድርሻዬን እወጣለሁኝ" በሚል መሪ ቃል እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
በዘንድሮ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ላይ 13 ሺህ የሚደርሱ ሴቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም 200 አትሌቶች እና ከ30 በላይ በተሰማሩበት የስራ መስክ ስኬታማ ሴቶች ተካፋይ ይሆናሉ፡፡
ለውድድሩ የሚሆኑ ቲሸርቶችም ከመጪው ሰኞ አንስቶ መሸጥ እንደሚጀመርም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል #በሐዋሳ ከተማ የሚካሄደው ዓመታዊ የማራቶን የ2011 ዓ.ም ውድድር የካቲት 3 እንደሚከናወን ታላቁ ሩጫ በኢትዩጵያ አያይዞ ገልጿል።
ምንጭ፦ EBC

ጉዞ ሉሲ ለአንድነት እና ለፍቅር!
ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን የአንድ #የሉሲ ልጆች መሆናችንን በማሳወቅ #ሰላምና #ፍቅር በኢትዮጵያ እንዲነግስ የማድረግ ዓላማን የያዘ ነው፡፡ ሀገራችን የዓለም ዘር መገኛ መሆኗን በመገንዘብ ለትውልዱ የተመቸች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን መፍጠር ያለመ ነውም ተብሏል፡፡ ያለፈውን ቂምና ጥላቻ በመተው በመደመር እና እርቀ ሰላም እንዲመጣ በሁሉም ክልሎች ሉሲን በአስታራቂነት እና በሰላም አምባሳደርነት በመጠቀም በሀገሪቱ ሰላምና ፍቅርን በመስበክ አንድነትን በማጉላት የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠርም ሌላው ዓላማ ነው፡፡
ምንጭ፦ AMMA

ጥቆማ‼️
ጀሞ 1 አካባቢ ያሉ #ቤት_አልባ ውሾች ከአቅም በላይ ሆነውብናል፤ የሚመለከተው የአስተዳደር ክፍል አፋጣኝ እርምጃ ይውሰድ ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

#update የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ በሰጠበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ሀገሪቱ የብድር ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ በማድረግ የበጀት ጉድለትን በማስተካከል ያከናወነችው ተግባር ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ባለፉት 15 አመታት የዋጋ ግሽበት 14 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው፥ የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ አሁን ላይ ወደ 10 ነጥብ 3 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
via fbc
@tsegabwolde @tikvahiopia
via fbc
@tsegabwolde @tikvahiopia
ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል‼️
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
ወይዘሮ እየሩሳሌም ብርሃኑ፣ ወይዘሮ ቤተልሄም ብርሃኑ፣ ወይዘሮ አይናለም ሀይለልዑል እና አቶ ግርማቸው ዘውዱ በባህርዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ቀርበዋል።
ወይዘሮ እየሩሳሌም ብርሃኑ፣ ወይዘሮ ቤተልሄም ብርሃኑ እና ወይዘሮ አይናለም ሀይለልዑል ላፓልማ አክሲዮን ማህበር መስራች ሲሆኑ፥ ከጥረት ኮርፖሬት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመመሳጠር አክሲዮን ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከነበረው 30 ሚሊየን ብር መካከል 16 ሚሊየን ብሩን በማውጣት ያለአግባብ ተጠቅማወል ሲል የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ከላፓልማ አክሲዮን ማህበር ሲወጡ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው በመጠቀም የህዝብና የመንግስት ሀብትን በማባከን እንደጠረጠራቸውም የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል፡፡
ሌላኛው ተጠርጣሪ አቶ ግርማቸው ዘውዱ በበኩላቸው ከጥረት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመመሳጠር ከባህርዳር ሞተርስ በ24 ነጥብ 7 ሚሊየን የአክሲዮን ግዥ ፈፅመዋል በሚል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ጉዳዩን የተያያዙ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው በተለይ ወይዘሮ እየሩሳሌም ብርሃኑ፣ ወይዘሮ ቤተልሄም ብርሃኑ እና ወይዘሮ አይናለም ሀይለልዑል፥ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና ጠበቆቻቸውን እንዳላማከሩ በመጥቀስ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ተቃውመዋል።
የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤትም በጉዳዩ ላይ ብያኔ ለመስጠት ለሰኞ ጥር 27 ቀን 2011 አመተ ምህረት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ በየነ ጉዳይ በጊዜ እጥረት ለሰኞ ተላልፏል፡፡
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።
ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።
ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።
"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።
በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።
በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።
አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።
በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል።
በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።
ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።
እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።
ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።
ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።
ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።
በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።
በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።
መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።
እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።
አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ BBC አማርኛ

#update የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
“ከተማሪዎች የሚጠበቀዉ ሀሳብ እና ሀሳብ እያጋጩ አዲስ ሀሳብ ማፍለቅ እንጂ ድንጋይና ድንጋይን አጋጭቶ እሳት መፍጠር አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️
ሰው #የገደለው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 ክልል ልዩ ቦታው አክሱም ሆቴል ጀርባ ከምሽቱ 4፡00 በሽጉጥ ሰው የገደለው የጥበቃ ሰራተኛ በፈፀመው ወንጀል በእስራት ተቀጣ፡፡
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሐ የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል በማሰብ በጥበቃና በአትክልተኛነት የሰራ መደብ ተቀጥሮ በሚሰራበት ኤም ኤስ ኮንሰልታንት ድርጅት ውስጥ በዕለቱ ድርጅቱ የሚከፍለውን ወራዊ ደመወዝ ከወሰደ በኋላ ብዙ የድርጅቱ ሰራተኞች ደመወዛቸውን እንዳልወሰዱ ስለተረዳ ገንዘቡን ከተቀመጠበት ለመውሰድ የድርጅቱን አጥር ዘሎ እና ቢሮ ፈልቀቆ በመግባት ገንዘቡ የተቀመጠበትን ካዝና በዶማ ለመክፈት ሲሞክር የዕለቱ ተረኛ ጥበቃ የነበረው ማነው ብሎ ሲጮህ እንዳይለየውና እሱ መሆኑን እንዳይረጋገጥ በማሰብ በያዘው ሽጉጥ ወደ ሰማይ በመተኮስ ዝም እንዲል ካደረገው በኋላ ዘሎ በመውጣት መሮጥ ሲጀምር ከሚሰራበት ድርጅት ጎን የሴቶችና ህጻናት ልማት ጥበቃ የሆነው ሟች ቁም ሲለው የፈጸመው ወንጀል እንዳይገለጽ ለማድረግ ሲል ይዞት በነበረው ሽጉጥ ተኩሶ በመምታት ጨካኝና አደገኛ መሆኑን በሚገልጽ ሁኔታ የገደለው በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የሰው ግዲያ ወንጀል ተከሷል፡፡
ዐቃቤ ህግም ከዳግማዊ ምኒሊክ የአስከሬን ምርመራ ውጤትን በማስመጣት እና ሌሎች የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

#update የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡ የምስረታ በዓሉ በሃገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተከፈተ ሲሆን ለረጅም ዘመናት በነዋሪው ዘንድ ሲነሳ የነበረ በዞን የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ መመለሱ ሀገራዊ ለውጡን ህዝባዊ ያደርጋል ተብሏል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia