TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤጂንግ እና የዋሽንግቶን ውጥረት ? አሜሪካ እና ቻይናን ውጥረት ውስጥ የከተታቸው የታይዋን ጉዳይ ነው። ቻይና ታይዋን #ወደ_እናት_አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ነው የምታስበው ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች።  አሜሪካ ደግሞ ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ ከታይዋን ጋር ግን “ይፋዊ ያልሆ ጠንካራ” ዲፕሎማሲያዊ…
" ሀሰተኛ ዜና ነው " - ታይዋን

የታይዋን መከላከያ የቻይና የጦር ጄቶች PLA Su-35 " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ተብሎ በኦንላይን ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ_ዜና ነው አለ።

በታይዋን ያለውን ጉዳይ የሚከታተሉ ትክክለኛው የመከላከያ ድረገፅ ብቻ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃዎች ለሌሎች እንዳያጋሩ አሳስቦ " ይህን እኩይ ተግባር በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።

CGTNን ጨምሮ ሌሎችም ሚዲያዎች የቻይና Su-35 ተዋጊ ጄቶች " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ሲሉ ዘገባዎችን አውጥተው ነበር።

ቻይና " ታይዋን " #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባት ብላ ታምናለች ፤ ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

ለዛም ነው በአሜሪካ የስልጣን እርከን ሶስተኛዋ ሰው ፔሎሲ ታይዋን መግባታቸው ያስቆጣት እና እርምጃ እንደምትወስድ በተደጋጋሚ እየዛተች የምትገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሀሰተኛ ዜና ነው " - ታይዋን የታይዋን መከላከያ የቻይና የጦር ጄቶች PLA Su-35 " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ተብሎ በኦንላይን ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ_ዜና ነው አለ። በታይዋን ያለውን ጉዳይ የሚከታተሉ ትክክለኛው የመከላከያ ድረገፅ ብቻ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃዎች ለሌሎች እንዳያጋሩ…
#Update

ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በሀገሪቱ የስልጣን እርከን ሶስተኛ ሰው የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ጎብኝተዋል።

ትላንት ታይዋን ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ብዙ ሲባልለት የነበረ እና በአሜሪካ እና ቻይና መካከል የፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ዓለምን ያሰጋ ነበር።

ቻይና ፔሎሲ ወደታይዋን እንደሚመጡ ከሰማች ጊዜ አንስታ ስታስጠነቅቅና እስከወታደራዊ እርምጃ ድረስ እንደምትወስድ ፤ አሜሪካም ትልቅ ዋጋ እንደምትከፍል ስትዝት ነበር።

ነገር ግን ፔሎሲ ወደ ታይዋን ገብተው ጉብኝትም አድርገው ፤ ማግኘት ያለባቸውን አካላት ባለስልጣናት አግኝተው ዛሬ ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል።

ቻይና ጉብኝቱን ለማስቆም የወሰደችው ምንም እርምጃ ባይኖርም በአካባቢው ላይ ግን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ታውቋል።

ትላንት የቻይና የጦር ጄቶቿ ወደ ታይዋይን የአየር ክልል ዘልቀው መግባታቸው በኦንላይ ሚዲያ ቢሰራጭም መረጃው ውሸት እንደነበር የታይዋን መከላከያ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቻይና " ታይዋን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት ፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopia
የቻይና አቋም ምንድነው ?

ቻይና ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት አለች።

ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር አላማዎችን እና መርሆዎችን ለማስከበር መቆሟን ገልጻለች።

የሀገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን እደግፋለሁ ብላለች።

" ሶማሊላንድ የሶማሊያ አካል ነች። " ያለችው ቻይና፤ የሶማሊያን ብሄራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ የሶማሊያን ፌዴራላዊ መንግስትን እንደግፋለን ስትል አሳውቃለች።

" የቀጠናው ሀገራት በዲፕሎማሲያዊ ውይይት ቀጠናዊ ጉዳዮችን በጥሩ ሁኔታ እንደሚይዙ እና ወዳጃዊ ትብብር በማድረግ የጋራ እድገትን እንደሚያሳኩ ተስፋ እናደርጋላን  " ብላለች።

ቻይና ፤ ሶማሊያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለው አይነት ሁኔታ ከታይዋን ጋር ያለባት ሲሆን " ታይዋን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopua
#ቻይና

ኢትዮጵያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ አሁንም አቋሟ ያልተቀየረና የፀና መሆኑን አሳውቃለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአንዲት ቻይና ፖሊሲን ለረጅም ዓመታት ስታራምድ መቆየቷን አስታውሰው ይህ አቋሟ በዘመናት መካከል መንግስታት አፅንተው የያዙት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከሰሞኑን ራሷን ከቻይና ነጥላ እንደ ነፃ ሀገር በምትቆጥረው ታይዋን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተደርጎ ነበር።

በዚህ ምርጫ ቻይና አትወዳቸውም የሚባሉት፣ አስቸጋሪና አደገኛ ሰው ብላቸው የምትጠራቸው በሙያቸው ሐኪም የሆኑት ዊሊያም ላይ ማሸነፋቸው ተዘግቧል።

ዶክተሩ " ለቻይና አንንበረከክም !! " በሚል አቋማቸው ነው የሚታወቁት።

ቻይና ከምርጫው በፊት አምርራ ለምትጠላው ለገዢው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ (ዲፒፒ) ህዝቡ ድምጽ እንዳይሰጡ አሳስባ የነበረ ቢሆንም የዚሁ ፓርቲ አባል የሆኑት የሕክምና ዶክተሩ ዊሊያም ላይ ቺንግ አሸንፈዋል።

ሰውየው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " ታይዋን ነጻ አገር መሆኗን ማወጅ አያስፈልጋትም፣ ምክንያቱም ታይዋን ሉአላዊና ነጻ አገር ስለሆነች " ብለዋል።

ይህንን ምርጫ ተከትሎ ሀገራት አቋማቸውን እና አስተያየታቸውን ሲሰጡ ነበር።

አሜሪካ በምርጫው ላሸነፉት ፕሬዜዳንት በይፋ የ" እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት አስተላልፋ ፤ ከታይዋን እና ከገዢው ፓርቲ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር አሳውቃለች።

ከምርጫው በኃላ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ፤ " እኛ ነፃነትን አንደግፍም ... " የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሜሪካ ከታይዋን ጋር ይፋዊ ያልሆኑ ግንኙነቶች ያሏት ሲሆን ታዋይም የአሜሪካ ድጋፍ እንዳላት በተለያየ ጊዜ ተናግራለች ፤ የአሁኑን ምርጫም ተከትሎ የቀድሞ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ስቴፋን ሃድሌይ ጭምር ያሉበት ይፋዊ ያልሆነ ልዑክ ወደ ታይዋን ልካ ከአሁኑ ተመራጭ ፕሬዜዳንት እና ከቀድሞ ጋር ውይይት አድርጋለች።

ከአሜሪካ በተጨማሪ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ የአውሮፓ ህብረት፣ እንዲሁም ካናዳ ፣ ጃፓን ለገዢው ፓርቲ ደስታ መልዕክት አስተለልፈዋል።

በሌላ በኩል፤ ሩስያ ምርጫውን ተከትሎ ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗን ገልጻለች። ኢራን ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቬትናም ፣ታጃኪስታን " የአንድ ቻይና " ፖሊሲን እንደምትደግፍ አረጋግጣለች።

ከአፍሪካ ደግሞ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሶማሊያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ድጋፍ በማሳየት ፤ ታይዋን የቻይና ግዛት ናት ስትል መግለጫ አውጥታለች። ከቀናት በፊት ቻይና " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት " ማለቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ስለምርጫው ምንም ባትልም አሁንም " የአንድ ቻይና " ፖሊሲዋ እንዳልተቀየረ አሳውቃለች።

ቻይና ታይዋንን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopia