TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦሮሚያ ክልል‼️

በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ዶክተር #ቢቂላ_ሁሪሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ ያላቸውን #አቅም#እውቀት እና #ስነ_ምግባርን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአዲስ መልክ በተዋቀሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥም ሁሉም ሰራተኞች በሚመጥናቸው ስራ ዘርፍ ላይ ተወዳድረው እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑንም ሀላፊው ገልፀዋል።

ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በመግለጫቸው፥ በፖለቲካው መስክ የመጣው ለውጥ ብቻ በሁሉም ደረጃ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ስለማይችል የህዝቡ ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስትን አደረጃጃት ከመሰረቱ ማስተካከል ለአንድ ዓመት በተደረገ ጥናት የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደ አዲስ እንዲደራጁ መደረጉን አንስተዋል።

አዲሱ አደረጃጀትም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ #መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እቅድ ተይዞበት እየተሰራ ነው ብለዋል ሀላፊው።

በዚህም የመንግስት እና የህዝብን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም እንደ አዲስ በተደራጁ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ አቅምን፣ እውቀትን ፣ ችሎታን እና ስነ ምግባርን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ግልጽ እና ተአማኒ በሆነ መልኩ የሰራተኞች ምደባ እየተካሄደ መሆኑንም ዶክተር ቢቂላ አስታውቀዋል።

እየተካሄደ ባለው የሰራተኞች ምደባ ማንኛውም ሰራተኛ ከመንግስት ስራ ውጭ #እንደማይሆን የገለጹት ሀላፊው፥ ሰራተኞች በአግባቡ እንዲሰሩና እና ውጤታማ በሚያደርጋቸው የስራ መስክ ላይ እንደሚመደቡን ገልፀዋል።

“ማንኛውም ሰራተኛ ከስራ ውጭ ልሆን እችላለሁ የሚል #ስጋት_ሊገባው_አይገባም” ያሉት ዶክተር ቢቂላ፥ ምደባው እስኪጠናቀቅ ድረስም ባሉበት ሆነው በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ እስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልፀዋል።

በአዲሱ ምደባ መሰረት የሚመደቡ የመንግስት ሰራተኞችም በአዲስ መንፈስ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ቦታ ላይ አቅጣጫና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

ሁለተኛ ዙር አለም አቀፍ የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ተጀመረ። “ቀጣይነት ያለው #እውቀት መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ መገንባት”በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ኮንፍረንሱ በአምስት ቀናት ቆይታው አምና ተመርጠው ጥናት በተካሄደባቸው ዘርፎች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia