TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትራንስፖርት ታሪፍ  ጭማሪ አልተደረገም‼️

ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ።

የአዲስ አበባም ሆነ የክልሎች የትራንስፖርት ታሪፍ ባለበት እንደሚቀጥልም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የፖሊሲ ጥናትና የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ መብራቱ እንደገለፁት፥ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ተከትሎ ምንም አይነት የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም።

በህዳር ወር የነዳጅ ማስተካከያ በተደረገበት ወቅት የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ስለተደረገና የአዲስ አበባውም የዛሬ አመት አካባቢ መሰረታዊ ማስተካከያ ያደረገ ስለሆነ የሚኖር ማስተካከያ አለመኖሩን ነው ያስታወቁት።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት ይህንን አውቀው ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደሌለባቸው ባለስልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ህብተረተሰቡ በቀድሞው ታሪፍ መሰረት የአገልግሎት ክፍያውን እንዲፈፅም አሳውቀዋል።

የንግድ ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ቴፒ‼️በቴፒ ከተማ በትናንትናው ዕለት ያገረሸው #ግጭት ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ🗓ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ በነገው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የምክር ቤት አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች #ማብራሪያ ይሰጣሉ።

Via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተቃውሞ ሰልፉ ሳይካሄድ ቀረ‼️

በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የጸደቀውን የስደተኞች አዋጅ #በመቃወም በጋምቤላ ክልል ተወላጆች ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ሰልፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ ሳይካሄድ ቀርቷል። ረፋድ 3፡30 ገደማ ከ35 እስከ 40 የሚሆኑ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች በመስቀል አደባባይ ቢሰባሰቡም ፍቃድ ያገኙበትን ደብዳቤ ለጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የጸደቀው አዋጅ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ እና፣ ህዝቡ ተወያይቶ #መግባባት ላይ ያልደረሰበት መሆኑ ሰልፍ ለማድረግ እንዲነሳሱ እንዳደረጋቸው በቦታው የጀርመን ድምፅ ራድዮብያነጋገራቸው ወጣቶች ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ሊካሄድ የነበረው ሰልፍም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለው የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ባለመሆኑ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ አለመከናወኑን የጀርመን ድምፅ ራድዮ በስልክ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ #አረጋግጠዋል

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ፕሬዚዳንት #ኢስማኤል_ኡመር_ጌሌ ለልዑካን ቡድኑ በጅቡቲ ቤተ መንግስት አቀባባል አድርገውላችዋል። ልዑካኑ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታም በሁለተዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ነው የተገለፀው። ከጥር 21 ቀን እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በጅቡቲ ሲካሄድ የቆየው15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በዚህ ስብሰባም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ የሚመሩ ከአስር በላይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተሳትፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል‼️

በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ዶክተር #ቢቂላ_ሁሪሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ ያላቸውን #አቅም#እውቀት እና #ስነ_ምግባርን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአዲስ መልክ በተዋቀሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥም ሁሉም ሰራተኞች በሚመጥናቸው ስራ ዘርፍ ላይ ተወዳድረው እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑንም ሀላፊው ገልፀዋል።

ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በመግለጫቸው፥ በፖለቲካው መስክ የመጣው ለውጥ ብቻ በሁሉም ደረጃ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ስለማይችል የህዝቡ ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስትን አደረጃጃት ከመሰረቱ ማስተካከል ለአንድ ዓመት በተደረገ ጥናት የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደ አዲስ እንዲደራጁ መደረጉን አንስተዋል።

አዲሱ አደረጃጀትም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ #መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እቅድ ተይዞበት እየተሰራ ነው ብለዋል ሀላፊው።

በዚህም የመንግስት እና የህዝብን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም እንደ አዲስ በተደራጁ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ አቅምን፣ እውቀትን ፣ ችሎታን እና ስነ ምግባርን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ግልጽ እና ተአማኒ በሆነ መልኩ የሰራተኞች ምደባ እየተካሄደ መሆኑንም ዶክተር ቢቂላ አስታውቀዋል።

እየተካሄደ ባለው የሰራተኞች ምደባ ማንኛውም ሰራተኛ ከመንግስት ስራ ውጭ #እንደማይሆን የገለጹት ሀላፊው፥ ሰራተኞች በአግባቡ እንዲሰሩና እና ውጤታማ በሚያደርጋቸው የስራ መስክ ላይ እንደሚመደቡን ገልፀዋል።

“ማንኛውም ሰራተኛ ከስራ ውጭ ልሆን እችላለሁ የሚል #ስጋት_ሊገባው_አይገባም” ያሉት ዶክተር ቢቂላ፥ ምደባው እስኪጠናቀቅ ድረስም ባሉበት ሆነው በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ እስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልፀዋል።

በአዲሱ ምደባ መሰረት የሚመደቡ የመንግስት ሰራተኞችም በአዲስ መንፈስ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ቦታ ላይ አቅጣጫና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
440 ተጠርጣሪዎች በነፃ ተለቀቁ‼️

#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናበተ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በአሶሳና በባምባሲ ወረዳዎች እንዲሁም በማዖና ኮሞ ልዩ ወረዳ ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸዉ ያላቸዉን 528 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ከታህሳስ 11 2011 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካከል 440 የሚሆኑት ማስረጃ ያልተገኘባቸዉ በመሆኑ በነፃ መለቀቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላምና ፀጥታ ግንባታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ብርሃኑ_አየለ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ከተለቀቁት መካከል 33ቱ ሴቶች ሲሆኑ የተቀሩት ወንዶች መሆናቸዉን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡

በነፃ የተለቀቁት ተጠርጣሪዎች በህገ መንግስት ዓለማዎች፣ መርሆችና ዕሴቶች እንዲሁም በአብሮነትና የሰላም ግንባታ ላይ የተሃድሶ ስልጠና ወስደዉ የተለቀቁ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

ቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች 21 የሚሆኑት ማሰረጃ የተጠናቀቀባቸዉ ሲሆን 67 የሚሆኑት ተጠርጣሪዎች ደግሞ ጉዳያቸዉ በሂደት የሚጣራባቸዉ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሱማሌ ክልል ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ የአደባባይ ስብሰባም ተከልክሏል፡፡ ገደቡ የተጣለው ከትናንት ወዲያ ከጅግጅጋ ከተማ ወጣ ብሎ በኦርቶዶክስ ሐይማኖት በዓል ላይ በተነሳ #ግጭት ሁለት ሰዎች #መሞታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ጸጥታ ሃይሎች ግጭቱን የቀሰቀሱትን ግለሰቦች እስከሚያድኑ ድረስ ገደቡ #ለሦስት_ቀናት እንደሚቆይ የክልሉን ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ #አብዱላሂ_ሞሃመድ_አብዲን ጠቅሶ የዘገበው ብሉምበርግ ነው፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሂርጳ 'ዳግም' ሞቱ‼️

ከሁለት ወራት በፊት የሞትን ብርቱ ክንድ አሸንፈው ተነሱ የተባሉት አቶ #ሂርጳ_ነገሮ ሞተው ሳሉ የገጠማቸውን ለቢቢሲ አጫውተው የነበረ ሲሆን ከ70 ቀናት በኋላ ትናንት 'ዳግም' ማረፋቸውን ከሁለት ጊዜ ገናዣቸው ተሰምቷል።

መቃብር ፈንቅለው ከወጡ በኋላ ጤናማ የነበሩት አቶ ሂርጳ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግን በፅኑ ታመው ከፈሳሽ ውጭ ምንም ነገር ይወስዱ እንዳልነበር BBC ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል። እሳቸው አይሆንም ቢሉም ቤተሰቦቻቸው ነቀምት ሆስፒታል ወስደዋቸው ነበር። ቤተሰቦቻቸው አቶ ሂርጳ ዳግም መቃርብር ፈንቅለው ይነሳሉ የሚል #ተስፋ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 1 ሚሊዮን 55 ሽህ 286 ብር በላይ ግብይት ይካሄድበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገር አቀፍ አነስተኛና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽንና ባዛር ትናንት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ 129 አቅራቢዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ እንደገለጹት፤ በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ የተከፈተው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ አነስተኛና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽንና ባዛር‹‹የተቀናጀ የገበያና የግብይት ድጋፍ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ውጤታማነት›› በሚል መሪ ቃል ከጥር 23 እስከ 30 ድረስ ይካሄዳል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዎድሮስ በእስር ላይ ይገኛል‼️

#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዎድሮስ አዲሱ ከሀምሌ 28-30 ቀን 2010ዓ.ም በጀጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ #ፍትሃዊ አለመሆኑንና የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን በማመን መዝገቡ እንዲዘጋ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በ80 ሺህ ብር ዋስ #እንዲወጣ ፈቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ግለሰቡ በሌላ ወንጀል ከቀድሞው የሱማሌ ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊና ከኒያላ ኢንሹራንስ የጅጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር #በተጭበረበረ የኢንሹራንስ ዋስትና አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ቦንድ ከኢንሹራንስ እንዲጻፍ በማድረግ በውሉ ላይ ከተጠቀሰው ቅድመ ከፍያ ላይ ብር 15,306,303.3 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ወጪ በማድረግ የወሰደ በመሆኑ ለትምህርት ቤቱ መፀሐፍቱን ሳያቀርብ ገንዘቡን ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በቴዎድሮስ አዲሱ ላይ #በከባድ የሙስና ወንጀል የጀመረውን ምርመራው ለማከናወን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት ተጠርጣሪው በእስር ቤት እንዲቆይ እና ለየካቲት 5 ቀን 2011 እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ በአውሮፕላን ማረፊያው እስከ ከ6 እስከ 8 ሰዓታት ቆይታ ላላቸው መንገደኞች አየር መንገዱ ከነገ ጀምሮ በራሱ አስጎብኝ ድርጅት አማካኝነት አዲስ አበባ ከተማን በነጻ ያስጎበኛል፡፡ ብሄራዊ ሙዚዬም ለጉብኝቱ ከተያዙት ቦታዎች ቀዳሚው ነው፡፡

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል። በፍቅርና በመቻቻል በምትታወቀው ጥንታዊቷ ከተማ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሕግና ሥርዓት የማይከበርባት፣ ሥርዓተ አልበኝነትና መንግሥት አልባ ተደርጋ በነዋሪዎቿና በጎብኚዎቿ ስትቀርብም ነበር።

via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia