TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጅማ አባጅፋር ደጋፊዎች ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች ያስተላለፉት መልዕክት...⬇️

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች።

#ውድ የኢትዮጵያ ሚድያዎች በያላቹበት የጅማ አባጅፋርን ውድቀት የምትመኙ እንደምን አላቹ እኛ ጅማዎች በመጣን በአመታችን እንደዚህ ታላላቅ ቡድኖች የሚያስጨንቅና ሌሎችን የሚያሳስቅ ቡድን ገንብተን ይኸው ድፍን ዓመት ሊሞላን ነው

#እናንተ ሚድያዎች ግን ምን ያክል አድሎ በቡድኖች ላይ እንደምታደርጉ ያየንበትን ዓመት አሳልፈናል የኛ ጅማ አባጅፋር ዓመቱን በሙሉ እንደዚህ የሚገርም እንቅስቃሴ እያደረገ አንድም ግዜ ስለክለባችን ድንቅ ብቃትና ጥንካሬ ዘገባ ሳትሰሩ ውጤቱንና ደረጃውን ከመግለፅ ባልዘለለ ዓመቱን ዘለቃቹት

#እኛ ጅማዎች ስለ ክለባችን እንድታወሩ ለማድረግ ቢራ ፋብሪካ🍺 የለንም ነገር ግን ድንቅ የሆነ የፍቅር መገለጫ ቡና☕️ አለን ፍቅር ማሳየት እና ቡና በነፃ ማጠጣት እንጂ እንድታወሩልን መቼም ገንዘብ አንሰጣቹም ነገር ግን ለሙያቹ ታማኝ ሆናቹ ሁሉንም አገልግሉ

#ይህን ስንል ግን በየቦታው እየተጓዙ ጫወታውን በቀጥታ በRadio ለጅማና ወዳጆቿ የሚያስተላልፉትን እና OBN, Fano እና ጅማ ማህበረሰብ ሳናመሰግናቹና ሳናደንቃቹ አናልፍም

#በስተመጨረሻም ገና ቻምፒዎን እኖናለን ገና አንድ ነጥብ ስንጥል ምን እንዳላቹ እናውቃለን እኛ በልጆቻችን ትልቅ እምነት አለን በወሬያቹ ቢሆንማ እነ....... ቻምፒዮንስሊግ ሁላ ባነሱ ነበር

#እኛ ግን ፍቅር ነን እንወዳቹዋለን ማብራርያም ከፈለጋቹ ኑ ቡና እየጠጣን እንጨዋወት

#የኛ ጅማ አባጅፋር ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል
#ይህን መረጃ በየSocial ሚድያው Share በማድረግ እየተሰራብን ያለውን ለሰው እናሳውቅ።

@tsegabwolde @tikahethiopia
ስሙኝማ!

እዚህች ሀገር ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭት እሳት ቢለኮስ እሳቱ ቀድሞ አፈፍ የሚያደርገው ምስኪኑን ድሀውን ህዝብ ነው። ያለውማ ኮሽ ሲል የሚሄድበት አለው! ችግር ቢፈጠር መሸሺያ እና መጠጊያ አለው! ...የችግሩ ተጋፋጮች #እኛ ነን! ስለሆነም ጥዋት ማታ ስለሰላም፣ ስለፍቅር፣ ስለአንድነት እናስብ። ማንም እንዲያታልለን ልንፈቅድለት አይገባም። እኛ ከኢትዮጵያ ውጪ ምንም ሀብት የሌለን ሰዎች በሰላማችን ጉዳይ ከማንም ጋር ልንደራደር አይገባም። የምንወዳቸውን ሰዎች ስንከተልም ከምንም ነገር በፊት #ለሰላም የሚሰጡትን ቦታ ለይተን ልናውቅ ይገባል።

~ፀጋአብ ወልዴ ኢትዮጵያ~
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስተር

#በትምህርት_ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ’#እኛ_ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።
ትምህርት ሚኒስተር

በትምህርት ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ #እኛ_ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ👇