TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
440 ተጠርጣሪዎች በነፃ ተለቀቁ‼️

#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናበተ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በአሶሳና በባምባሲ ወረዳዎች እንዲሁም በማዖና ኮሞ ልዩ ወረዳ ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸዉ ያላቸዉን 528 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ከታህሳስ 11 2011 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካከል 440 የሚሆኑት ማስረጃ ያልተገኘባቸዉ በመሆኑ በነፃ መለቀቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላምና ፀጥታ ግንባታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ብርሃኑ_አየለ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ከተለቀቁት መካከል 33ቱ ሴቶች ሲሆኑ የተቀሩት ወንዶች መሆናቸዉን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡

በነፃ የተለቀቁት ተጠርጣሪዎች በህገ መንግስት ዓለማዎች፣ መርሆችና ዕሴቶች እንዲሁም በአብሮነትና የሰላም ግንባታ ላይ የተሃድሶ ስልጠና ወስደዉ የተለቀቁ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

ቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች 21 የሚሆኑት ማሰረጃ የተጠናቀቀባቸዉ ሲሆን 67 የሚሆኑት ተጠርጣሪዎች ደግሞ ጉዳያቸዉ በሂደት የሚጣራባቸዉ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia