TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CARD

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያረቀቀው አዋጅ ላይ ዛሬ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በCARD አዘጋጅነት የማህበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች አዋጁን ይዘት እንዲተዋወቁትና ከባለሞያ ጋር እንዲመክሩበት በመሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) ጹሑፍ አቅራቢነት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም በመድረኩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፤ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD

የመብቶችና ዲሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል (CARD) አዘጋጅነት ዛሬ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያረቀቀው አዋጅ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ውይይቱ የማህበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች አዋጁን ይዘት እንዲተዋወቁትና ከባለሞያ ጋር እንዲመክሩበት አልሞ የተዘጋጀ ሲሆን ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ውይይቱ በመሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) ጹሑፍ አቅራቢነት ተጀምሮ በተሳታፊዎቹ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከህጉ አስፈላጊነት ጀምሮ አተገባበር ላይ ስለሚገጥሙት እንከኖች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉት የጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ወቅት የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብዓትነት ይዘዋቸዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የምክክር መድረኩን ካዘጋጀው CARD ኤክስኪዊቲቭ ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ እንደ አቶ በፍቃዱ ገለጻ የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በሦስት መሰረታዊ ነገሮች ላይ መሰራት አለበት ብለው ይመክራሉ እነዚህም ሀቅን ማረጋገጥ(Fact checking )፣ የሚዲያ አጠቃቀም (Media literacy) እና የመንግስት ግልጸኝነት (Transparency ) ናቸው ይላሉ፡፡

ተጨማሪ ከላይ ባለው ፋይል አድምጡ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
#CARD

"በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች ዋነኛው ሰበብ የፖለቲካ ልህቃን በውይይት አለማመን ነው" -አቶ አወት ሃለፎም

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ብልፅግና ማዕከል (CARD) የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለሚነሱ ግጭቶች መንስኤ እና መፍትሄዎቻቸው የፓናል ውይይት አካሂዶ ነበር።

በፕሬግራሙ ላይ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ለውይይት ካቀረቡት መካከል አቶ አወት ኃለፎም ይገኙበታል።

አቶ አወት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና የደህንነት ጥናት ተቋም የPHD ተማሪ ናቸው። በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚነሱ ግጭቶችን ባህሪዎችና መፍትሄዎችን ጠቁመዋል።

🎧የድምፅ ፋይሉን ያድምጡ🎧

(VOICE OF AMERICA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#CARD

በመብቶች ዴሞክራሲ ብልፅግና ማዕከል (CARD) አማካኝነት ሶሻል ሚዲያ ላይ ንቁ ተሳታፊ ከሆኑና መረጃዎችን እንዲሁም ኃሳቦችን በማቅረብ ከሚሳተፉ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ጋር በምርጫ ህጉ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የCARD ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አጥናፉ ብርሃኔ እንደገለጹት ሌሎች ሚዲያዎች የራሳቸውን ሰው የማሰልጠን አቅሙ ይኖራቸዋል ነገር ግን ሶሻል ሚዲያው ላይ ላሉ አዘጋጆች ታስቦ የሚዘጋጅ ባለመኖሩ ማዕከሉ ይህንን መሰረት አድርጎ ዝግጅቱን እንዳዘጋጀ ገልጸዋል፡፡

ለተሳታፊዎቹ ስለአጠቃላይ ህጉ መግለጫ የሰጡትና ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ የሰጡት የምርጫ ቦርድ የኮሚውኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ሲሆኑ ከዚህ በፊት የነበረውን አዋጅ ጨምሮ በአዲሱ የተቀየሩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከተሳታፊዎችም ወቅታዊ እና በምርጫ ጊዜ ሊከሰቱ ይችላሉ የተባሉ አንኳር ነጥቦች ከሕጉ አንጻር ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በቀጣይም ተመሳሳይ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ማዕከሉ ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CARD

የመብቶችና ዲሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል ባለፉት ስድስት ወራት ባደረገው የማህበራዊ ሚዲያዎች ቅኝት አስተውሏል፡፡ በዚህም የተዛቡ መረጃዎችን የሚሰራጩ ሰዎች የመጀመሪያ ምክንያታቸው በተመልካች ብዛት የገቢ ምንጭ ቢሆንም ለፓለቲካዊ ዓላማ፣ ለተራ ዝናና ግላዊ ብሽሽቅ እንዲሁም ባለማወቅ እና እንደመዝናኛነት በመቁጠርም ጭምር እንደሆነ ቅኝቱ አመላክቷል ተብሏል፡፡

በቅኝቱ መሰረት የጥላቻ ንግግሮች የሚበራከቱባቸው የተለያዩ ጊዜያት መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡ እነዚህም የተቃውሞ ሰልፎችና ግጭቶች በሚከሰሰቱባቸው ወቅቶች፣ ሃይማኖታዊ በዓላትና ፌስቲቫሎች በሚኖሩበት ሰዓት፣ በዩኒቨርሲቲዎች በሚነሱ ግጭቶች፣ የፓለቲካ መሪዎች የገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርጉና ምርጫዎችና ህዝበ ውሳኔዎች ሲካሄዱ ይጨምራል፡፡

ይህ ደግሞ ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ የሚጨምር ይሆናል፡፡ ከወዲሁም በቅኝቱ በተደራጀ መልኩ የስም ማጥፋትና የማጥላላት ዘመቻዎች እየተካሄዱ መሆኑን ማየት ተችሏል፡፡ ይህም ዜጎችን በተሳሳተ መረጃ ለማይፈልጉት አካል ድምጻቸውን እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል ሲል ፍራቻውን ይገልጻል፡፡

በመጨረሻም ማዕከሉ የህዝብን አረዳድ በመጨመር ግንዛቤ መፍጠር ላይ አተኩሮ የሚሰራ እንደሆነና በቀጣይ በሚኖሩ መግለጫዎች አጥፊዎችን በግልጽ በመለየት የሚያሳውቅ ይሆናል ተብሏል፡፡ ከዚህ ባሻገር ጋዜጠኞች የሐቅ ማረጋገጥ ሥራ በመስራትና ዜጎችም የጥላቻ ንግግር ባለማጋራት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaabot
CARD FoE and Legitimate Restrictions.pdf
1.2 MB
7ቱ የተዛቡ መረጃ ዓይነቶች!

1ኛ - ስላቅ ወይም ቀልድ (Satire or Parody) - እነዚህኞቹ አንባቢውን ለመጉዳት ወይም ለማሳሳት የተፈጠሩ ሳይሆን ለማስገረም፣ ለማዝናናት ወይም ባለታሪኩ ላይ ለማላገጥ የተዘጋጁ መረጃዎች ናቸው፤ ነገር ግን በተደራሲዎቹ እንደ እውነት ሊቆጠሩ ይችላሉ።

2ኛ - አሳሳች ይዘት (misleading content) - እነዚህኞቹ መረጃዎቹ ስህተት ባይሆኑም የቀረቡበት መንገድ ግን ተደራሲያኑን በማሳሳት ሌላ ነገር እንዲገምቱ ወይም እንዲያምኑ የሚያደርግ ነው።

3ኛ - የተፈበረከ ይዘት (fabricated content) - ጉዳት ለማስከተል በማሰብ ሙሉ ለሙሉ የተፈጠረ የሐሰት መረጃ።
4ኛ - ለምድ ለባሽ ይዘት (Imposter content) - መረጃው ከታማኝ ምንጭ ወይም ቢሮ የተገኘ ለማስመሰል የተደረገ ነገር ግን የተፈበረከ የሐሰት መረጃ።

5ኛ - የውሸት ግንኙነት (False connection) - ሁለት የማይገናኙ ነገሮችን (ፎቶ እና ታሪኩ፣ ርዕሱና ዝርዝሩ…) እንደሚገናኙ አስመስሎ ማቅረብ።

6ኛ - የውሸት ዐውድ (False context) - እውነተኛ ታሪኮችን እና ምስሎችን እየተጠቀሙ ነገር ግን ከአገባቡ ውጪ በመጥቀስ መረጃ ማዛባት።

7ኛ - አላግባብ የተተረጎመ ይዘት (manipulated content) - መረጃው ብዙ ተመልካች እንዲያገኝ ሲባል ብቻ አዛብቶ ማቅረብ።

[ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትና ቅቡልነት ያላቸው ገደቦች]

#CARD
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#CARD

የጥላቻ ቃላትን እና ዓረፍተ ነገሮችን ለመለየት እና ለመረዳት የሚደረግ ሰርቬይ ነው። ሰርቬዩ የጥላቻ ቃላትን ዝርዝር በተጠና መንገድ በማዘጋጀት የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲያስወግዷቸው ይረዳል። 

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe2vnd9oVr9iL1TA_Q8T6q9AXpUKNklWrPOkvH5yB_uxLH-SA/viewform?usp=send_form

Qorannoo sarara irraa Itiyophiyaa kessatti tamsaasa jechoota jibbaa fi balaa uumuu dandaa'an ilaalchise godhame.

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdh2N-lwmZBNlKV2jcAB1tEz_9LEIU4krsUzxJKL0ZaN5xg7w/viewform?usp=send_form

This survey intends to identify and understand hate and inflammatory words and terms in Ethiopian local languages. The result will help us develop a lexicon of hate speech terms and phrases to help social media users to avoid the use of them and the social media platform moderate them effectively. 

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScRCF9rDhOQYTf6m7mizLBjUQsjJCYycRjWcUBsHlqp9Tbr0Q/viewform?usp=send_form
ዛሬ ዓርብ (ግንቦት 28/2012 ዓ/ም) በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ያለውን አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ - #CARD #TIKVAH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ከኮቪድ-19 እንጠብቅ!

አስከፊውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመግታት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ #ዋነኛው የመከላከያ መንገድ ነው።

የበሽታው ስርጭት ፦

- ሠዎች እርስ በእርስ ባላቸው ቅርበት
- አብረው በሚያሳልፋበት ጊዜ
- በሚያደርጉት የሰው ንክኪ ቁጥር ይወሰናል።

#CARD #TIKVAH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 55 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ከነዚህ መካከል 18 ሰዎች ከለገጣፎ፣ 14 ሰዎች ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል።

- በትግራይ ባለፉት 24 ሰዓት 37 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 18ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 12 ሰዎች ንክኪ ያላቸውና 7 ሰዎች የውጭ የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 115 ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል ፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 292 ደርሰዋል።

- በደቡብ ክልል ከተደረገው 578 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጣል ፤ ከነዚህ መካከል 13 ሰዎች ከወላይታ ዞን ናቸው።

- በሱማሌ ክልል ከተደረገው 42 የላብራቶሪ ምርመራ 19 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 10 ከጅግጅጋ እንዲሁም 9 ከጎዴ ናቸው።

- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሃያ (20) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል 9 ሰዎች ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ናቸው።

#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia