TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሻሸመኔ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች!

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ።

በአደጋውም እስካሁን በደረሰን ሪፖርት የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱም ታዉቋል። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።

ከአደጋው ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ህገወጥ ቡድኖች ከተማዋ ላይ ህገወጥነት፣ ብጥብጥ እና ግጭት ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል። በዚህ ሂደትም ቦንብ ይዞ ተገኝቷል በሚል #ሀሰተኛ_ወሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በቡድን ጥቃት በማድረስ የግለስቡ ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ይህ ድርጊት አስነዋሪና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ሰላም ወዳዱን የሻሸመኔ ከተማ ህዝብም ሆነ የሻሸመኔን ቄሮ የማይወክል የክፋት ተግባር ነዉ።

ግለሰቡ ላይ የተፈፀመዉን ግድያም አጥብቀን #እናወግዛለን። በተጨማሪም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሽከርካሪ በእሳት ጋይቷል። ተሽከርካሪው ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል #የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ ነዉ። ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጥ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ሰላም ወዳዱ የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥረት ከተማዋ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች።

በዛሬዉ ዕለት በተፈጠረዉ ችግር በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦችንም ህዝቡ እና ፖሊስ በመቀናጀት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

©አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሻሸመኔ ከተማ በተፈፀመ #የወንጀል ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስታውቀዋል።

ዶክተር ነገሪ ከኦ.ቢ.ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በሻሸመኔ ከተማ ቦምብ ተገኝቷል በሚል #የተሳሳተ መረጃ ግርግር እንዲፈጠር መደረጉን ገልፀዋል። ሆኖም ግን ፖሊስ እስካሁን ባደረገው ማጣራት ቦምብም ይሁን ምንም አይነት ከቦምብ ጋር የሚመሳሰል ነገር እንዳልተገኘ አስታውቀዋል።

@tseagbwolde @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ ወሬዎች ተጠንቀቁ‼️

በአሐዱ ሬዲዮ ከአቶ #ጃዋር_መሃመድ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተብሎ #በፌስቡክ የተሰራጨው መረጃ #የተሳሳተ መሆኑን አሐዱ ራድዮ በዛሬው ዕለት ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨው #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት የላከው ደብዳቤ!
ኢሳት‼️

የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ #የዘር_ግጭት የሚጭር ቪድዮ #አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ኦሮምኛ ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ማስተካከሉን አስታውቀዋል።

በማስተካከያውም የተባለው ቪድዮ የተዘጋጀው በሌላ አካላት እንደነበርና ኢሳት ወዲያውኑ ቪድዮውን ማውረዱንና #ይቅርታ መጠየቁን በቢሲ በማስተካከያው ላይ ጨምሯል።

ዳይሬክተሩ ቢቢሲ ማስተካከያ ለማድረግ በመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀው በዚሁ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተሰራ ያሉትን የተሳሳተ ዘገባ ኢሳትን ለመጉዳት ያለመ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት በሰላም ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን በማህበራዊ ድረገፅ የሚራገበው #የተሳሳተ መረጃ ትክክል እንዳልሆነ እየገልፅን ዩኒቨርሲቲው በአሁን ወቅት ፍፁም ሰላማዊ እና በተረጋጋ መንገድ የትምህርት እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።" የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ነው!!

"በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት በሰላም ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን በማህበራዊ ድረገፅ የሚራገበው #የተሳሳተ መረጃ ትክክል እንዳልሆነ እየገልፅን ዩኒቨርሲቲው በአሁን ወቅት ፍፁም ሰላማዊ እና በተረጋጋ መንገድ የትምህርት እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።" የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃ‼️

አርቲስት #ኤፍሬም_ታምሩ ከጀርመን ራድዮ ጋር ቃለ ምልልስ አላደረገም። ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ ከጀርመን ራድዮ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል በሚል የተሰራጨዉ መረጃ #የተሳሳተ ነዉ።

አርቲስቱ በምንም ዓይነት ጉዳይ ላይ ከጀርመን ራድዮ ጋር በቅርቡ ቃለ ምልልስ ያልሰጠ መሆኑን የዝግጅት ክፍሉ ገልጿል። አርቲስት ኤፍሬም #የአገውን_ሕዝብ አስመልክቶ ሰጠ የተባለዉ መረጃ የጀርመን ራድዮ በሚያሰራጫቸዉ የሬዲዮ፣ የፌስ ቡክ፣ የዋትስ አፕ እና የቲዩተር ገጾች ላይ ፈፅሞ ያልቀረበ መሆኑንም አድማጮች ተከታታዮች እንዲረዱለት አሳስቧል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሳሳተ ፎቶ ነው‼️

በሶሻል ሚድያ ላይ የካፒቴን #ያሬድ_ጌታቸው #እጮኛ እየተባለ በፎቶ የተለቀቀው ሁሉ #የተሳሳተ መረጃ ነው። ቤተሰቡም ሆነ ጏደኞቹ የሚያውቋት እጮኛው ካፒቴን #ቃልኪዳን ትባላለች።

(ከካፒቴን ያሬድ የቅርብ ጓደኛ የተላከልኝ!)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አብራሪዎቹን ለማሰልጠን የሚያስችሉ የተሟሉ ሰባት ምስለ በረራዎች ወይም የበረራ ማሰልጠኛዎች አሉት።

•በአሁን ወቅት ብቁና የተሟሉ ኪው 400፣ ቢ737 ኤን ጂ፣ ቢ 737 ማክስ፣ ቢ 767 ፣ ቢ 787 ፣ ቢ 777 እና ኤ 350 የተሰኙ ሰባት ምስለ በረራዎች አሉት።

•በዋሽንግተን ፓስት የወጣው መረጃ በመረጃ ላይ ያልተደገፈና #የተሳሳተ ነው።

•ማነነታቸው ካልታወቁ አካላት ተገኙ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ከበረራ ስለታገደው #ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ትኩረት ለማስቀየር ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት...

ባሳለፍነው ሳምንት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው ተብሎ የተሰራጨው ዜና #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል የናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ገለፀ፡፡

እንደ ተቋሙ ገለፃ የተቋሙ ባለቤት #ናፍያድ_ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም በከፈቱት አካውንት ከሳሽ ለተባሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ ምንም አይነት ቼክ እንዳልሰጡ እና ከግለሰቡ ጋርም በስራ ዘርፍም ሆነ በሌላ ጉዳይ የማይገናኙ እንደሆኑ ጠቅሶ ተሰጠ የተባለው ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ መሰረቁን ቀደም ተብሎ ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገ ገልጾአል።

በጉዳዩ ላይ ክስ ተመስርቶ እየታየ እንደነበር የገለፀው የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለዚህም ድርጅቱ ከሚገኝበት ከኦሮምያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፖሊስ የደረሰበትን ውጤት የሚያሳይ ለተቋሙ የተፃፈን ደብዳቤን አቅርቧል፡፡

ፖሊስ ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ ከወጋገን ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ስለመሰረቁ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው የወንጀል ምርመራ በሚመለከት የፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ነኝ ያሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ የተባሉት ግለሰብ በጠፋው ቼክ ጉዳይ ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮምያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ እና በዋስ መብት የተለቀቀቁ" ናቸው ያለው የህዝብ ግኝኑነት ክፍሉ “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኃል እንዲሉ በተገላቢጦሽ ግለሰቡ ከሳሽ ሆኖ መቅረባቸው አስገራሚ ሆኖብናል” ያለ ሲሆን ጉዳዩ በህግ የተያዘ መሆኑን አስታውሶ "ክሱ ሆን ተብሎ የድርጅቱን ባለቤት እና የተቋሙን መልካም ስም ለማጉደፍ የተቀናባበረ" መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

Via ሸገር ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጦላይ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሥልጠና ላይ ያሉ ከ150 በላይ የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች መመረዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ችግሩ የተከሰተው ትናንት በቁርስ ሰዓት በሚጠጡት ሻይ ነው፡፡ 129ኙ ትናንቱን ለሕክምና ወሊሶ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን 20ዎቹ ደሞ ዛሬ እንደገቡ የሆስፒታሉን ሐኪም ተናግረዋል፡፡ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት እንደታየባቸውም ተገልጧል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ዛሬ ከቀትር በኋላ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ታማሚዎች በጥሩ ጤንነት ሁኔታ እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ የህመማቸው መንስዔ እየተጣራ ቢሆንም የምግብ መመረዝ እንደሆነ የተወራው ግን #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና ...

ዛሬ ማለዳ የወሊሶ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ የአድማው መንስዔ ጦላይ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሉ የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመርዘዋል የሚል ዜና መሰራጨቱ ነው፡፡ በአድማው ሳቢያ ከወሊሶ-አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ-ወሊሶ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ ወጣቶች መንገዱንም ዘግተዋል፡፡ በከተማዋ የመንግሥት ተቋማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም አገልግሎታቸውን አቋርጠዋል፡፡

Via #BBC(#WAZEMA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ባለፈው #ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ #ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭትም በአንዲት ሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደምትገኝና 17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም የ10 መኪናዎች መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሰባበረ ሲሆን ፥ አንድ ግሮሰሪ ላይም ዘረፋ ተፈጽሟል ነው ያሉት።

ግጭቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በመቀናጀት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉንም አንስተዋል።

ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የተከሰተውን ችግር ከማጋነንና #የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት #እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews "ይህ መረጃ ፈፅሞ #የተሳሳተ እንደሆነ እንገልፃለን።" የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

#የተሳሳተ_ዜና_ጥቆማ - #MisinformationAlert
ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል፡፡ ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ኮሮና ቫይረስ ሁሉንም የእድሜ ክልል ነው የሚያጠቃው!

(በዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር)

በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የእድሜ ስብጥር ብንመለከት እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 272 ሰዎች ከህፃናት እስከ አረጋዊያን ድረስ በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ተይዘዋል።

ትልቁ ቁጥር 99 ሰዎች ከ15-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው ፤ ከዛ የሚቀጥለው ከ25-34 የእድሜ ክልል ውስጥ (75 ሰዎች) የሚገኙ ሲሆን ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥርም 19 ነው። በህፃናት ላይ አነስተኛ ቁጥር ቢታይም ህፃናትም በሽታው እንደሚይዛቸው ያሳያል።

ይህ በሽታ የማያጠቃው የእድሜ ክልል የለም። በዓለም አቀፍ ደረጃ #ወጣቶች አይጠቁም የሚል #የተሳሳተ ግንዛቤ አለ ፤ በተለይ በእኛ ሀገር ያለው ስርጭት ትልቁ ቁጥር በወጣቶች ላይ የታየ ነው። ስለዚህ እያንዳንዳችን የምንወስደው ጥንቃቄ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የዚህ በሽታ ስርጭት #እየጨመረ የሚሄድ ሊሆን ቢችልም ምን ያህል ይጨምራል የሚለውን የምንወስነው በየዕለቱ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ፣ በየዕለቱ በምንመርጣቸው ምርጫዎች እንዲሁም በምንወስዳቸው እርምጃዎች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መንግስት በኮቪድ-19 ዙሪያ እርምጃዎችን እያላላ ነው ?

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት በቅርቡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያው ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎች መንግስት በኮቪድ-19 ዙሪያ እርምጃዎችን እያላላ ነው የሚል #የተሳሳተ ግንዛቤ በማህበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ማሻሻያዎቹ የተደረጉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙ #እየጨመረ በመምጣቱ መንግስት ያለውን ውስን ሃብት የት ላይ ማፍሰስ አለበት የሚል ለወረርሽኙ ምላሽ የስትራቴጂክ ለውጥ አስፈላጊ በመሆኑና ይበልጥ ለወረርሽኙ ጠንከር ያለ ምላሽ ለመስጠት የተደረጉ እንጂ እርምጃዎችን የማላለት እቅድ እንደሌለ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia