TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሱት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለዕድለኞች መተላለፍ ጀመሩ፦
.
.
የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በነበሩት አቶ ጃንጥራር ዓባይና በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋላ፣ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሮ የነበረው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ማስተላለፍ ተጀመረ፡፡

ከ18 ሺሕ በላይ በሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከወጣ በኋላ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በገቡት ውል ምክንያት በወቅቱ እንደ ቤቱ ስፋት ተተምኖ የነበረውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ (መቶ በመቶ) የፈጸሙ በርካታ ሰዎች የዕጣውን መውጣት ተቃውመው ነበር፡፡ ተቃውሟቸው ‹‹ለምን ዕጣው ወጣ?›› በሚል ሳይሆን፣ ከንቲባው የቤት ግንባታ ፕሮግራም ዓላማና መመርያ ከ40 በመቶ በላይ የተገመተውን ዋጋ የቆጠበ በሙሉ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ መካተት አለበት ብለው ዕጣው በመውጣቱ ነበር፡፡

በመሆኑም መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙት በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት ነበር፡፡ ከ200 በላይ የሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መቶ በመቶ ከፋዮች፣ በተለያዩ መዝገቦች የዳኝነት በመክፈል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ መሥርተው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝን የከሰሱት ግለሰቦቹ፣ ባንኩ ውል በመፈጸም ሚኒስቴሩ ያወጣውን መመርያ ባለማስፈጸሙና ኢንተርፕራይዙ ደግሞ ሕግ ተላልፎ ዕጣ በማውጣቱ፣ በአንድ ላይ በመክሰሳቸው ፍርድ ቤቱ ዕጣ የወጣባቸውና ዕጣ ያልወጣባቸውም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች እንዳይተላለፉ ዕግድ ጥሎ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ክስ ከመረመረ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ በተለይ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች የተመዘገቡት የቤት ዓይነት ከየሳይቱ ታግዶ እንዲቆይ በማለት፣ የቀሪዎቹን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ አንስቷል፡፡

ሌሎችም አመልካቾች በተመሳሳይ ሁኔታ ክስ መሥርተው ጉዳያቸው እየታየ ቢሆንም፣ ዕግዳቸው የተነሳላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ከሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ውል የሚዋዋሉበት ፕሮግራም በየክፍላተ ከተሞቹ ወጥቶላቸው በመዋዋል ላይ ይገኛሉ፡፡

አስተዳደሩ 32,653 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ያወጣ ቢሆንም፣ ለዕድለኞቹ መቼ እንደሚተላለፉ ያለው ነገር የለም፡፡   

Via #reporter
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia