TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደብረ ታቦር‼️

በደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን የደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት ትላንት ከቀኑ 11፡00 አካባቢ #አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር።

ከቀኑ 11፡00 አካባቢ መደበኛው የታራሚዎች ቆጠራ የሚያደርጉ የመምሪያውን የፖሊስ አባላት #በማፈን እስረኞች #ለማምለጥ በመሞከራቸው ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው።

የፖሊስ አባላቱን በማፈን ግርግር ፈጥረው ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉት ደጋጋሚ እስረኞችና ከባድ ፍርደኞች መሆናቸውን የደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር መንጌ ከበደ ተናግረዋል፡፡

የመምሪያ ኃላፊው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል በመጨመር የማረሚያ ቤቱን ሰላም የማረጋጋት ሥራ ተሰርቷል።

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱል በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

ባለፉት ወራት በቤኒሻንጉል ክልል እየተንቀሳቀሰ ማሕበራዊ ሰላም #ሲያደፈርስ የነበረውና ከጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በርካታ ወንጀሎችን በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ ከትላንት በስቲያ #በፌደራል_ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ጉለሌ ፖስት ከምጮቼ ሠማሁ ብሎ ዘግቧል።

#አብዱል_ወሃብ የተባለውና የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ግንባር ሊቀ መንበር የነበረው ይህ ግለሰብ ቀደም ሲል በኤርትራ ይንቀሳቀስ የነበረውን ግንባር ሲመራ ቢቆይም፤ በአገሪቱ በተፈጠረው ለውጥ ወደክልሉ ከተመለሰ በኋላ ለውጡን ለመቀልበስ ከሚፈልጉ ሃይሎች ጋር
በመቀናጀት በበርካታ ወንጀሎች ሲፈለግ መቆየቱን የጉለሌ ፖስት ምንጮች ጠቁመዋል።

አብዱል ወሃብ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በፌደራልፖሊስ አባላቱ ላይ ተኩስ ከፍቶ ለማምለጥ ጥረት ያደረገ ሲሆን በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ተመቶ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

እንደጉለሌ ፖስት ምንጮች ገለጻ ተጠርጣሪው #ለማምለጥ ባደረገው ጥረት የክልሉ ልዩ ሃይል የተወሰኑ አባላት ስልታዊ ድጋፍ ሲያደርጉለት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ...

በያዝነው ዓመት መጀመርያ ላይ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን እንግልት ለመከላከል ቄሮዎችን አደራጅታችኋል በሚል በቤኒሻንጉል ክልል እስር ቤት የሚገኙት ዘጠኝ አዛውንቶች እስካሁን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን የመረጃ ምንጮቼ ገልጸዋል ሲል ጉለሌ ፖስት ዘግቧል። በተለይ ኦቦ #ተስፋዬ_አመኑ እና ኦቦ #መላኩ_ቀጄላ የተባሉት አዛውንቶች በሕመም ላይ የሚገኙ መሆኑ በጣም አሳሳቢ እንደሆነባቸውና መንግስት አስቸኳይ እልባት እንዲሰጣቸው እኒሁ ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ጉለሌ ፖስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጥቁር ገበያ ሽያጭ ሊቀርብ የነበረ #ነዳጅ ተያዘ‼️

ለጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ «ትዕግስት ብሩክ ቶታል ማደያ» ውስጥ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ/ም በ44 ጀሪካን 995 ሊትር ቤንዚን ከማደያው በመቅዳት ላይ እንዳሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተቀዳውን ከ11 ሺ ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ ቤንዚን እና ሌላ ሊቀዳበት የነበረ 44 ባዶ ጀሪካን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 29642 ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችም ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ እንደገለፁት የማደያው ሰራተኞች ቤንዚን በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ድርጊቱን ፈፅመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ልዩ ቦታው አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ ኮድ 3-47453 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከላይ ሲሚንቶ በማድረግ ከስር 63 ጀሪካን ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም ምዕራብ ሆቴል አከባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 80502 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በኮንትሮ ባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ እቃዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዘዟል፡፡

ፖሊስ መምሪያው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪው ቢያዝም አሽከርካሪው ግን ለጊዜው እንደተሰወረ እና ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር ጌታነህ ገልፃዋል፡፡

ተሽከርካሪው ሲያዝ በርከታ ጣቃ ጨርቆች፣ 2ሺህ የሞባይል ቻርጀሮች፣ 3480 አይነቱ « ኑር ሴላ» የሆነ ሲጋራ እና 1ሺ የሪሲቨር ሪሞት ኮንትሮል ይዞ #ለማምለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia