TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እባክዎ #የአምቡላንስ ሳይረን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ቦታ በመልቀቅ ወይም ጥግ በመያዝ የሰው ህይወት ያትርፉ!

©ዳግም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በመስጂድ፣ ቤተክርስቲያናት እና ሌሎች የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ያለውን ህጋዊነት እንዲሁም ለቤተ ዕምነቶች የመሬት አሰጣጥና የካርታ ህጋዊነት ዙርያ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አመራሮች ጋር እየተወያየ ባለበት በዚህ ሰዓት የከተማ አስተዳደሩን ስም ለማጠልሸት የሚደረግ ሙከራ አግባብነት እንደሌለው እና አስተዳደሩ ዕርምጃ እንደሚወስድም አስታውቀዋል፡፡ በመጨረሻም ለዚሁ ስራ የተዋቀሩት ኮሚቴዎች ውሳኔ ላይ እስኪደርሱ ድረስ የአከባቢው ነዋሪ መስጂዱን መጠቀም እንደሚችልም አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AMH-Addis-Deridewa-!-27-2019
መንግሥት የድሬዳዋ ነዋሪዎችን አወያየ‼️

#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ተፈራ ደርበው እና አቶ መለሰ አለም በመሩት መድረክ ላይ ነዋሪዎች አሉ ያሏቸውን ጥያቄዎች አንስተው መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተሳታፊዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወላጆች ልጆቻችን ይፈቱ ብለው ፖሊስ መምሪያ መጠየቃቸውንና መምሪያውም ተጠርጣሪዎች #ተጣርተው መፈታት ያለባቸውን በአፋጣኝ እንደሚፈቱ ገልፀውልናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ VOA 24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ‼️

በኢትዮጵያ #የመጀመሪያው አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ ዕውን ሊሆን ነው። በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።

ከአስተባባሪዎቹ አንዱ #ውባለም_ታደሰ (ዶር) እንዳሉት የተለያዩ ታዋቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ #ምሁራን የተካተቱበት ይህ ፓርቲ በሀገሪቱ የሚታየውን ስር የሰደደ ድህነትና ማህበራዊ ፍትህ ዕጦት ለመቅረፍ አረንጓዴ ፓርቲ መፍትሄ አለው ብሎ ያምናል።

ፓርቲው #ብሄርም ሆነ #አካባቢ የማይገድበው ሁሉን አቀፍ መሆኑንና ለማናቸውም ኢትዮጵያውያን በሩ ክፍት መሆኑን አስተባባሪዎቹ ለዋዜማ ሬድዮ ገልፀዋል።

ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በቅርቡ መስራች ጉባዔ እንደሚያደርግና በምርጫ ቦርድም #የመመዝገብ እቅድ አለው።

አረንጓዴ ፓርቲ በታዳጊ ሀገሮች እምብዛም የተሳካለት ባይሆንም ባደጉት ሀገሮች በተለይ በጀርመን አናሳ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን ይታወቃል። ብዙውን ጊዜም ከሌሎች አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በማበር አጀንዳውን ያስፈፅማል። 

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ እና በአካባቢው ለብዙ ዓመታት በስደት ላይ የነበሩ 168 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳውዲ ኢምባሲ ቪዛ መስጠት ጀምሯል‼️

ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አስፋው ይርጋለም እንዳስታወቁት ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ለሚመጡት ህጋዊ ተጓዦች የሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በትላንትናው ዕለት የቪዛ አገልግሎ መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ፣8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ፣በሚሄዱበት የስራ መስክ ስልጠና ወስደው የብቃት ማረጋገጫ ያገኙ፣ የጤና ኢንሹራንስ የተገባላቸው፣ ሙሉ የጤና ምርምራ ያደረጉና ከወንጀል ነጻ የሆኑ ሰራተኞች በአስቀጣሪ ኤጀንሲ በኩል ቪዛውን አግኝተው መሄድ እንደሚችሉ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት የውጭ ሀገር ሰርተው የተመለሱና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ ግን ስልጠናውን ለመውሰድ አይገደዱም፤ የብቃት ማረጋገጫ ግን ይወስዳሉም ብለዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ሰራተኞች ወደ ሳውዲ ሲሄዱ መብቶቻቸውን የሚያስጠብቁ አዳዲስ ስምምነቶች መደረጋቸውንም አቶ አስፋው ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ለስራ በሄዱበት አካባቢም የአካል ጉዳት ወይም በስራ ላይ እያሉ ሞት ቢያግጥም ኢንሹራንስ ተገብቶላቸው እንዲሄዱም ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት ወደ ሳውዲ የሄዱ ሰራተኞች ስልክ የማያገኙበት አጋጣሚ ነበር ያሉት አቶ አስፋው ፣አሁን ላይ የስልክ አገልግሎትም እንዲያገኙ ስምምነት መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የሰራተኛና የአሰሪ ግንኙነቱን የተሻለ ለማድረግ በኮምፒውተር በታገዘ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ደመወዝ መከፈል አለመከፈሉን የሚያረጋግጥ ስርዓትም ተዘርግቷል ተብሏል፡፡በዚህም በአሰሪው በኩል ቅጣት የሚያስከትል የቁጥጥር ስርዓት መኖሩ ተመልክቷል፡፡

ከ200 በላይ የሚሆኑ ህጋዊ ኤጀንሲዎች ፈቃድ ወስደው ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር በመስራት እንሆኑም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በቅርቡ ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው ስምምንት ወደ አገሪቱ ለስራ የሚያመሩ ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛው ክፍያ 1ሺህ የሳውዲ ሪያል እንዲሆን ከስምምነት መደረሱም ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር 79780/00054 በሆነ ተሳቢ መኪና ተጭኖ ሊወጣ ሲል ቶጎጫሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጉምሩክ ባለሙያዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት የጋራ ጥረት ሊያዝ ችሏል፡፡ በተያያዘም በቀን 20/05/11 ከምሽቱ 3፡30 ላይ በሌላ ተጠርጣሪ 2 ግራም የሚሆን ሜርኩሪ መሰል ማዕድን በሶማሌ ክልል አድርጎ ወደ ሶማሌ ላንድ ሊያስወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል፡፡

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቀቀ። በዚህም መሰረት ወጣት አስፋው ተክሌን በሠብሳቢነት እንዲሁም ወጣት አክሊሉ ታደሰን በምክትል ሰብሳቢነት መምረጡን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvagethiopia
#update ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታወቀ። በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

via ELU

•በጅግጅጋ የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሟች ቁጥር 2 እንደሆነ ገልፀው መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ!!

ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጻድቁ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያገለግል መተግበሪያ የተጫነባቸውን ሁለት ኮምፒተሮች አበርክተዋል።

በቀጣይም 20 ተጨማሪ ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ኮምፒዩተሮችን ለመስጠትም ቃል የገቡት ቀዳማዊት እመቤቷ በርካታ መጻሕፍትንም ለትምህርት ቤቱ አበርክተዋል።

ባለፈው መስከረም ወር ላይ በዚሁ ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ60 በላይ የዓይነ ስውራን መፃፊያ መሳሪያ (ብሬይል)፣የብሬይል ወረቀት፣ የዓይነ ስውራን መምሪያ ዱላ፣ ልዩ ልዩ እስክሪብቶዎች፣ ደብተሮችንና ቦርሳዎችን ማበርከታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ሎዛ ማሪያም አካባቢ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስገንባት መጀመራቸን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስጠንቀቂያ‼️

#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቀቀ።

via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia