#update በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሄዱ። በልምምዱ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል። እንደዚህ ያሉ መድረኮች ለልምድ ልውውጥና መማማር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስምረውበታል። የጋራ አገራዊ ራዕይን በተቀናጀ መልኩ ለማሳካት ግለሰቦችንና ተቋማትን ተጠያቂ ማድረግ ያስፈልጋል። ጠ/ሚር ዐቢይ ለውጥ ያሳዩ ሚኒስትርና ተጠሪ ተቋማትን በመጥቀስ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነጥቦች ላይ ቀጣይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
#100DaysEvaluations
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#100DaysEvaluations
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ እንደሚፈልግ አስታወቀ‼️
.
.
"ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ያደርጋል"
"መልዐክ ሆኖ ቢመጣ ሰው #ሰይጣን በሚል እንደሚያነበው አውቆ ስሙን ይቀይራል"
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታወቁ፡፡
ብርጋዴር ጀነራል አህመድ ሀምዛ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንገለጹት፤ ሜቴክ ከሥራ አጋሮቹ ጋር የነበረው ግንኙነት የተበላሸና በጸብ የተሞላ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ይፈጽማል፤ ተቋሙም የህዝብ እንደመሆኑ ከዚህ በኋላ ሚስጢር አይኖረውም፤ እቅዶች ድረ ገጾች ላይ ይቀመጣሉ፤ ለመገናኛ ብዙኃንም ክፍት ይሆናል ብለዋል።
ተቋሙ አብረውት ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹አገልግሎት ሰጪ እስከ ሆንን ድረስ ከአገልግሎት ፈላጊው ዝቅ ብሎ ነው መታየት ያለብን›› ብለዋል፡፡ ደንበኞች ለከፈሉት ገንዘብ እንኳን አገልግሎት ሲጠይቁ ይሰጣቸው የነበረውምላሽ በጣም አደገኛና በጸብ የተሞላ እንደነበር በማስታወስ ይህንን ሁኔታ ለመቀየርም እንደሚሰራ አብራርተዋል።
ስኳር ኮርፖሬሽንን ለአብነት በመጥቀስም ከኮርፓሬሽኑ ጋር የነበረው ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኮርፖሬሽኑ በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሏል፤ ተቋሙ ግን ጨርሶ ያስረከበው አንድም ፕሮጀክት የለም፡፡ ፕሮጀክቶቹን ካለማጠናቀቅም በላይ አንዳንዶቹን ወገብ ወገባቸው ላይ እያደረሰ ነው በሀይል እንዲረከቡ ያደረገው›› ሲሉ ያብራራሉ።
በሌላ በኩል መልካም ስምን ከመገንባት አንጻር አደረጃጀቱን መቀየር ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዲዬር ጀነራል አህመድ ፣ ‹‹ሜቴክ ከአሁን በኋላ መልዐክ ሆኖ ቢመጣ እንኳ ሰው ሰይጣን ብሎ ስለሚያነበው ስሙን መቀየር አስፈልጓል››ብለዋል፡፡ ይህንን ለማከናወንም መረጃዎችን የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
መረጃ የማሰባሰብ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላም በጥቂት ጊዜ ውስጥ አደረጃጀቱንና ስሙን በመቀየር በአዲሱ ስሙም አዲስ ሆኖ እንደሚቀርብና እንደ ማንኛውም የልማት ድርጅት ህግን ተከትሎ መስራት እንደሚጀምር አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በስድስት ወራት ውስጥ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የሪፎርም እቅድ መዘጋጀቱን ገልጸው፣ ይህ እቅድ ሲዘጋጅ ይሳካሉ ተብለው ከተቀመጡ ግቦች መካከል ዋናው የተቋሙን የጠፋ ስም መመለስ፣ በህግና ስርዓት ብቻ ተከትሎ እንዲሰራ ማድረግ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን

ስልክ ሻጮቹ ተያዙ‼️
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተያዙ፡፡
.
.
‹‹ሦስት ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ #የሞባይል_ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ይዣለሁ።›› የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት
‹‹ፓኪስታናውያኑ የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው።›› ገዥዎች
.
.
ከሁለት ቀናት በፊት በሰቆጣ ከትመው ‹‹መንገደኞች ነን፤ ገንዘብ #አጥሮን›› በማለት አገልግሎት የማይሰጡ ሞባይል የሚሸጡ ሦስት ፓኪስታናውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ አስታወቁ።
ፓኪስታናውያኑ ተጠርጣሬዎች የተያዙት በሰቆጣ ከተማ ነጋዴዎች ሱቅ ድረስ በመሄድ ‹‹ገንዘብ አጥሮን ነው፤ ግዙን›› እያሉ ሲዘዋወሩ ነው። ነዋሪዎችም የገዙት ሞባይል የማይሠራ በመሆኑ ‹‹ይጣራልን›› ማለታቸውን ተከትሎ ሕጋዊ ፍተሻ መደረጉ ታውቋል። በፍተሻውም 26 ስማርት ስልኮች፣ 52 ሺህ የኢትዮያ ብር፣ መጠኑ ያልተገለፀ የፈረንሳይ ገንዘብ እና 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላሮችን ይዘው ተገኝተዋል።
ተጠርጣሬዎች ስልኮችን ከገንዘብ በተጨማረ በወርቅ እየቀየሩም በመያዛቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ሲመረመሩም ግንበኞች እንጂ ተንቀሴቃሽ ነጋዴዎች እንዳልሆኑ ተረጋግጧል።
ኢንስፔክተር ደጀን ‹‹ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ያገኘውን ጥቆማ እና ቅሬታ ተከትሎ ተጠርጣሬዎችን በሕግ እንዲጠየቁ የማድረጉን ሥራ ጀምሯል›› ሲሉ ለአብመድ ተናግረዋል።
አብመድ ያነጋገራቸውና ስማርት ስልኩን ገዝተው እንደማይሠራ ለፖሊስ ካመለከቱት መካከል አቶ መርሻ ገብረኪዳን እና ታደሰ መልኩ ‹‹በየሱቃችን መጥተው ግዙን እያሉን ነበር›› ብለዋል።
‹‹ሦስቱ ፓኪስታናውያን የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው። ‹20 ሺህ ብር የሚሸጥ ሞባይል ነው፤ ገንዘብ ስላጠረን ግዙን› ብለው 5 ሺህ ብር ገዛን፤ ግን አይሠሩም ነበር፡፡ በኋላ ላይ በየሱቁ ሌሎችንም ግዙን ሲሉ ለፖሊስ አመልክተናል›› ብለዋል።
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ‹‹ድርጊቱ ‹ነጭ ስለሆንን አንጠረጠርም› ብለው አስበው እንደነበር ያመላክታል፤ ይሁን እንጂ ደሴ እና መቀሌ ተመሳሳይ ሥራ መሥራታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ›› ብለዋል።
ኢንስፔክተር ደጀን ወንጀሉ ወደሌሎች ከተሞች እንዳይስፋፋ ኅብሰተሰቡ ያደረሰው መረጃ የሚመሠገን እንደሆነም ገልጸዋል።
ምንጭ፦ አብመድ

Alert‼️ጅግጅጋ ከተማ 06 አካባቢ እየሆነ ያለውን ጉዳይ መንግስት በልዩ ትኩረት እንዲከተካከተለው የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ!
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚስተዋለውን ህገወጥነት እና ሃሰተኛ የመታወቂያ አገልግሎት ለማስቀረት የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪነት መታወቂያን በዲጂታል መታወቂያ እየቀየረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከመታወቂያ ስራው በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር Troy Security Solutions group ከተባለ የአሜርካ ኩባንያ ጋር የትምህርት ማስረጃዎችን በተለይም የ8ኛ ክፍል ውጤትሰርተፊኬት (ሚኒስትሪ) ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት(ካርታ) ፣ የልደት ሰርተፍኬት ፣ የሞት ሰርተፍኬት ፣ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና የፍቺ ሰርተፍኬቶችን በዘመናዊ ዲጂታል ሰርተፍኬት ለመቀየር ተስማምቷል፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከድርጅቱ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት "መረጃዎቹን በዲጂታል ሰርተፍኬት መለወጥ የህገወጥ(ፎርጂድ) ማስረጃ አገልግሎትን ከማስቀረቱ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጠውን አገልግሎት ምቹ እና ዘመናዊ ያደርገዋልም" ብለዋል ፡፡
ምንጭ:- የከንቲባ ፅህፈት ቤት

#update ኑሮአቸውን በጎዳና ያደረጉ ወገኖቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሠረተው የማህበራዊ ትረስት ፈንድ የቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሠረት:-
1. ዶ/ር ደበበ ኢሮ- ሰብሳቢ
2. ኡስታዝ አቡበከር አህመድ - ም/ሰብሳቢ
3. ዶ/ር ሜሎን በቀለ- ዋና ፀሃፊ
4. አርቲስት ቤቲ ጂ - አባል
5. አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ - አባል
6. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል - አባል
7. ብፁዕ (ዶ/ር) አቡነ አረጋዊ - አባል
8. ዲያቆን ብርሃን አድማስ - አባል
9. ፓስተር ፃዲቁ - አባል
10. ወ/ዊ ዮናታን አክሊሉ - አባል
11. አትሌት ደራርቱ ቱሉ - አባል
12. አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም - አባል
13. ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ - አባል
14. ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ - አባል
15. ረዳት ፕ/ር ነብዩ ባዬ - አባል ሆነዋል።
ምንጭ:- የከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህም መሠረት:-
1. ዶ/ር ደበበ ኢሮ- ሰብሳቢ
2. ኡስታዝ አቡበከር አህመድ - ም/ሰብሳቢ
3. ዶ/ር ሜሎን በቀለ- ዋና ፀሃፊ
4. አርቲስት ቤቲ ጂ - አባል
5. አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ - አባል
6. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል - አባል
7. ብፁዕ (ዶ/ር) አቡነ አረጋዊ - አባል
8. ዲያቆን ብርሃን አድማስ - አባል
9. ፓስተር ፃዲቁ - አባል
10. ወ/ዊ ዮናታን አክሊሉ - አባል
11. አትሌት ደራርቱ ቱሉ - አባል
12. አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም - አባል
13. ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ - አባል
14. ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ - አባል
15. ረዳት ፕ/ር ነብዩ ባዬ - አባል ሆነዋል።
ምንጭ:- የከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia