TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ለከተሞች ቀን ክብረ በዓል ያስተላለፉት መልዕክት።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ወለጋ🔝

ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ከኦሮምያ ርዕሰ መስተዳድር #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን በምዕራብ ወለጋ የቄለም ወለጋ ዞን ካሉ ወረዳዎች አንዷ የሆነችው ቤጊ ወረዳ የማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ🔝

ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ስለማስጠበቅና በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴ በበኩላቸው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣናው ውሕደት የወሰዷቸውን ርምጃዎች በማንሣት አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይብልጥ ተቀራርቦ አብረው እንዲሠሩ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ ተስማምተዋል። ሲያጠቀልሉም ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በአሁኑ ሰዓት ከአፋር፣ ከሶማሌ፣ ከሐረሪ፣ ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከጋምቤላ ክልል አጋር ፓርቲዎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር #ውይይት እያካሄዱ ነው።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከአጋር ፓርቲዎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በመደመር እሳቤ የመለወጥና አብሮ የማደግን አስፈላጊነት አሥምረውበታል። ተሳታፊዎቹም ለግል ዕድገት፣ እምነት፣ ርኅራሄ እና በተለይም ማኅበረሰባቸውን ለመምራት ገንቢ ዕሴቶችን እንዲያበለጽጉ አበረታተዋቸዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ገበታ_ለሸገር

እራቱን ለመታደም የምትፈልጉ...

ለቢዝነስ ባለቤቶች፣ የኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፦

ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ለመደገፍና ከጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ ጋር ገበታ ለመቅረብ [email protected] ላይ ፍላጎትዎን እንዲገልፁ ጥሪ ቀርቧል።

የእራቱ ዋጋ በሰው -- ብር 5ሚሊዮን!

ሙሉ ስምዎን፣ ድርጅትዎን፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥርዎን ሲልኩ በሸገር ገበታ ለመታደም የመመዝገቢያ ቅጽ ይላክሎታል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Adwa123 - ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ 123ኛው የዐድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በተመለከተ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መልእክት::

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ጠዋት ለአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡትን የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት #መሐመድ_አብዱላሂ_መሐመድን በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተቀብለዋቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ(ናይሮቢ)🛫

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር #ለመወያየት በአሁኑ ወቅት ወደ #ናይሮቢ ኬንያ አቅንተዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ በሶማሊያና ኬንያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀ መንበርነታቸው በቅርበት በመከታተል ወደ #ዕርቅ የሚመጡበትን መላ እያፈላለጉ ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኬንያታና የሶማሊያው አብዱላሂ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት በዘለቁ ወቅት ከሁለቱም ጋር ባደረጉት ምክክር፤ ይህንን የኬንያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት ለማመቻቸት ወስነው ነበር። ይህ የውይይት መድረክም በሁለቱ መካከል ያለውን የተካረረ ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይታመናል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia