TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #ቅዳሜ ነሕሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰዓት ከ9:00ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን #ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሊሰረዝ ነው⬇️

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የታቀደው ኮንሰርት #ሊሰረዝ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹልኝ ብሏል።

እንደ ዘ-ሀበሻ ምንጮች ዘገባ #ቴዲ ለአዘጋጆቹ "በዚህ የሃዘን ወቅት መድረክ ላይ ወጥቼ የመዝፈን አቅም የለኝም - አልችልምም" ብሏቸዋል ተብሏል።

ድምጻዊው ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሊደረግ የነበረ ሲሆን ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ፊታችን #ቅዳሜ ተዘዋውሮ ነበር።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይኸው ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ የማይካሄድ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ እንደማይታወቅ ታውቋል።

ሰው እየሞተ መዝፈን አልችልም ያለው ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ጠዋት በመድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት በቡራዩና በአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን እንደሚጎበኝ በተጨማሪም የገንዘብ እርዳታ እንደሚያደርግ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

@tsegabwklde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጉባኤ‼️

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው #ቅዳሜ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ ጉባኤው አቶ #ላክደር_ላክባክ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት አስቸኳይ ጉባኤው የሚካሄደው የክልሉን መንግስት የሚመራው ጋህዴን በቅርቡ ባካሄደው ግምገማ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው።

ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች ያቀረቡት የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

በምትካቸውም አዲስ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመቀለ ሰልፍ ሊካሄድ ነው‼️

በመቀለ ከተማ የፊታችን #ቅዳሜ የሚከበረው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህግ የበላይነትና ህገ-መንግስቱ ይከበር የሚል መልዕክት የሚተላለፍበት መሆኑን የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ በበአሉ አከባበር ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ #ዘመንፈስቅዱስ_ፍስሃ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የዘንድሮ የብሔሮች ፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በክልል ደረጃ የፊታችን ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ በህዝባዊ ሰልፍ ይከበራል።

“በህዝባዊ ሰልፉ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ይቁሙ፤ የህግ የባላይነትና ህገ-መንግስቱ ይከበር የሚሉ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ነው” ብለዋል።

“የትግራይን ህዝብ ለማምበርከክ የሚደረጉ ሴራዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው በሰልፉ መልዕክት ይተላለፋል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“በማንነት ጥያቄና በአዋሳኝ አካባቢዎች ምክንያት በማድረግ የክልሉን ህዝብ የሚነኩ ትንኮሳዎች ተቀባይነት የላቸውም” ያሉት ኃላፊው በውጭ ጣልቃ-ገብነትና የውስጥ ሴራዎች እንዲቆሙ የሚያስገነዝቡ መልዕክቶች በሰልፉ እንደሚተላለፉ አመላክተዋል።

“ህዳር 29 ህገ-መንግስቱ የፀደቀበት በመሆኑ የህገ-መንግስቱ ልዕልናን የሚያጎሉ መልዕክቶች በሰልፉ ጎልተው ይወጣሉ” ብለዋል።

በዓሉን በህዝባዊ ሰልፉ በ”ባሎኒ” ስታድዮም በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ኃላፊው በሰልፍ ላይ ከ200 ሺህ በላይ የከተማውና አካባቢው ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

ዜናው: መቀለ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንዲታደሙ የተጠሩት አቶ #በረከት_ስምዖን ወደ ከተማዋ ሊበሩ ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች መብረር እንደማይችሉ ተነግሯቸው ተመለሱ(ተያዙ)።

የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ማረጋገጥ እንደቻለው፦

ግለሰቡ ከደቡብ አፍሪካ የተመለሱት #ቅዳሜ ምሽት (የሰልፉ እለት) ነበር። ከትግራይ ክልላዊ መንግስትም የተሳተፉ ጥሪ #አላቀረበላቸውም ነበር። በመጨረሻም የጉዞ ክልከላ እስካሁን #አልተደረገባቸውም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ‼️

በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል የሚባለው ሰላማዊ ሰልፍ #ዕውቅና_የሌለው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለfbc በላከው መግለጫ፥ አንዳንድ ግለሰቦች #ቅዳሜ እና #እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰልፉ በከተማ አስተዳድሩም ሆነ በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑ ነው የተገለፀው።

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እና የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ሊካሄድ የታሰበው ሰልፍ ምንም ዓይነት እውቅና የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ አካላት የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር አስታውቋል።

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የተያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ስለሆነም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው በመሆኑ ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፎ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ባለፈው #ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ #ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭትም በአንዲት ሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደምትገኝና 17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም የ10 መኪናዎች መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሰባበረ ሲሆን ፥ አንድ ግሮሰሪ ላይም ዘረፋ ተፈጽሟል ነው ያሉት።

ግጭቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በመቀናጀት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉንም አንስተዋል።

ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የተከሰተውን ችግር ከማጋነንና #የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት #እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech
#ከጥላቻ_ንግግር_እንቆጠብ!!
የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ከልዩ ልዩ ጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አማካኝነት በግቢያችን ይካሄዳል።

#ፕሮግራሞች

#ቅዳሜ

☞ ብዙ ኪ.ሜ አቆራርጠው ለፍቅር እና ለሰላም ለሚመጡት የTIKVAH-ETH
ቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፣ ጥበባዊ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

#እሁድ

√የደም ልገሳ ፕሮግራም
√በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ስለጥላቻ ንግግር ፅሁፎችን ይቀርባሉ ፤ ልዩ ልዩ
ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
√በግቢያችን የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል

#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (ዩኤኢ) ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ከኬንያ፣ #ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን አገደች። እግዱ ከታህሳስ 16 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው። እግዱ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከመምጣታቸው 14 ቀናት በፊት በአራቱ ሀገራት የነበሩ ተጓዦችን እንዳይገቡ ማገድን የሚያካትት ነው። ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ…
#Update

ዩኤኢ ጥላው የነበረው እገዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ይነሳል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከ " ኦሚክሮን " ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ከተወሰኑ የአፍሪካ አገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ እገዳ ጥላ እንደነበር ይታወሳል።

እገዳው ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኬንያ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች ስምንት የአፍሪካ አገራት ወደ ግዛቷ የሚጓዙ ተጓዦችን ያካትት እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን እገዳ ከተጠቀሱት አገራት የሚነሱትን ብቻ ሳይሆን ከጉዟቸው ቀደም ብለው ባሉት 14 ቀናት ውስጥ እዚያ የቆዩትንም ያካትት ነበረ።

አሁን ግን ለሳምንታት ተጥሎ የነበረው እገዳ ከሚቀጥለው #ቅዳሜ አንስቶ እንደሚነሳ በአገሪቱ የብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ቀውሶችንና አደጋዎችን የሚከታተለው ተቋም አስታውቋል።

ነገር ግን ከተለያዩ አፍሪካ አገራት ወደሀገሪቱ የሚጓዙ ሰዎች ከጉዟቸው 48 ሰዓታት በፊት ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን የሚያመለክት የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እና ከሚነሱበት አየር ማረፊያ ፈጣን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ መንገደኞች የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እንደደረሱ ሌላ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ይገባቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ነገ እና እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት መታወቂያ ማሳደስ ትችላላችሁ "

#መታወቂያ_ለማሳደስ እየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም ህዳር 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ በየአካባቢው ባሉ የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ  ፅ/ቤቶች ይሰጣል።

ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየአቅራቢያቸው ባሉ ፅ/ቤቶች ተገኝተው መስተናገድ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች #ቅዳሜ እና #እሁድን ጨምሮ #በበዓላት ቀናት መስራት ግዴታ ሊደረግ መሆኑን ተዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ፤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ፤ " የአገልግሎት መስጫ ጊዜን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት ይፈልጋል የሚል እምነት አለን " ማለታቸውን ዘግቧል።

በከተማው የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠር አለበት ብለዋል።

አቶ ጥራቱ የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን አገልግሎት በአሰራር ተዘርግቶ መተግበር አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር ከመደበኛዉ 8 ሰዓት ተጨማሪ መስራት ያለባቸዉ መስሪያ ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ ? የሚለዉ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

በከተማዋ ባለዉ የትራንስፖርት መጨናነቅ እና በተለያዩ ጉዳዮች ሰራተኛዉ ቢሮ ገብቶ የሚሰራበት ሰዓት ዉስን በመሆኑ ሰዉ ማግኘት ያለበትን ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ማንሳታቸውን የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

" 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል " -የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተገልጋዮች ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ነው አለ።

ይህን ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ " የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር " መሆኑን ገልጸዋል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርም ለቅሬታዎቹ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።

ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቀጥታ (online Visa) አገልግሎት ይጀመራል ብለዋል።

የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈበት ሰው ዘወትር #ቅዳሜ ቀን እየመጣ መስተናገድ ይችላልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች ፣ እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ተቋም ውስጥ አለ ባለው ሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት በርካታ ዜጎች ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል። ፓስፖርት ለማግኘትም ያለው የጊዜ ርዝመት እና እንግልት እጅግ በርካቶችን ያማረረ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።

በአዲስ አበባ ' መስቀል አደባባይ ' ነገ #ቅዳሜ ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መንገዶች እንደሚዘጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከንጋቱ 11፡00 ሰአት ጀምሮ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦

- ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ እና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ

- ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ  ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት

- ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ   ለሚጓዙ ለገሀር መብራት

- ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA ሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

አሽከርካሪዎች መንገዶቹ እንደሚዘጉ አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ባለፈ በተጠቀሱት መንገዶች ከዋዜማው ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ወይም ማሳደር ተከልክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገው የመስቀል አደባባይ ሰልፍ #መንግሥትን የሚደግፍ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም እጅግ በጣም…
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።

ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር።

ነገ ማለትም
#ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው።

ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት ዩሮ ነው ዛሬ 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መግዣ ፤ መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም ሆነ ነበር የዋለው።

በነገው ምንዛሬ ግን የአንዱ ዩሮ መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም ፤ መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም ሆኖ ይውላል።

ብዙም የምይነገርለት
#የኩዌይት_ዳናር ደግሞ የአንዱ መሸጫ ከ315 ብር አልፏል።

በነገ ምንዛሬ አንዱ ዲናር በ298 ብር ከ8463 ሳንቲም እየተገዛ በ316 ብር ከ7771 ሳንቲም ይሸጣል ተብሏል።

ይህ መረጃ በ ' ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ' ያለውን ምንዛሬ የሚያሳይ ሲሆን የግል ባንኮች ደግሞ ምን ይዘው እንደሚመጡ ጥዋት ይታያል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት…
#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia