TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በብሄር ግጭት 890 ሰዎች ተገደሉ‼️

የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በምዕራብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #በብሔር_ግጭት ሳቢያ ቢያንስ 890 ሰዎች ተገድለዋል።

#ባኑኑ እና #ባቴንዴ በተባሉ ማኅበረሰቦች መካከል ግጭት የተከተሰተው ዩምቢ በሚባለው አካባቢ በሚገኙ አራት መንደሮች ውስጥ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው #ተፈናቅለዋል። ዩምቢ አካባቢ ባለው ግጭት ሳቢያ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ የሚሰጡት መጋቢት ላይ ይሆናል።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ 465 ቤቶችና ህንጻዎች ተቃጥለዋል፤ ፈራርሰዋልም። ከነዚህ መካከል ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋም፣ ገበያ እና የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቢሮ ይገኙበታል።

ከተፈናቀሉት ሰዎች 16,000 የሚሆኑት የኮንጎ ወንዝን ተሻግረው በኮንጎ ብራዛቪል ተጠልለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባቼት፤ "ይህ አስደንጋጭ ግጭት ተመርምሮ ጥፋተኞቹ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ብለዋል። ኮሚሽኑ ምርመራ መጀመሩም ተመልክቷል።

ዩምቢ ለወትሮው ሰላማዊ ግዛት ነበር። በማኅበረሰቦቹ መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው፤ የባኑኑ ማኅበረሰብ አባላት ባህላዊ መሪያቸውን በባቴንዴ መሬት ለመቅበር በመሞከራቸው ነበር።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫን ፌሊክስ ቲስኬዲ ማሸነፋቸው ቢነገርም ሌላው ተቀናቃኝ ማርቲን ፋያሉ "አሸናፊው እኔ ነኝ" ማለታቸው ይታወሳል።

ማርቲን ፋያሉ እንደሚሉት ከሆነ፤ ፌሊክስ ቲስኬዲ ምርጫውን ያሸነፉት ከቀድሞው ፕሬዘዳንት #ጆሴፍ_ካቢላ ጋር #ተመሳጥረው ነው። ሕዝቡ የሰጠው ድምጽ ዳግመኛ ይቆጠር ሲሉም ለፍርድ ቤት አቤቱታ አሰምተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጉዳይ በተመለከተ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ መክሯል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች #ተፈናቅለዋል፡፡›› የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
.
.
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ክልሉ 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲደረግ ቢቆይም አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጻል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልልም ከክልሉ ውስጥና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንዳሉት ከክልሉ ውጭ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ደግሞ በተለይም በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች ዜጎች በስፋት ተፈናቅለዋል፡፡

የመፈናቀል አደጋው ከተከሰተበት በተለይም ከሕዳር ወር ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በጋራ ተፈናቃዮችን በጊዜያዊና በዘላቂነት ለማቋቋም 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አሰማኸኝ ‹‹አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ሆኗል›› ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለሰፋ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ዘላቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፤ ‹‹ድጋፉ በተደራጀ እና በአንድ አግባብ እንዲሆን ይፈለጋል›› ሲሉም አሳበዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በዕውቀት ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት አቶ አሰማኸኝ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#የገንዘብ_ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000258250811 እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት በስልክ ቁጥሮች 0582180196፣ 0582181096፣ 0582181151፣ 0918701136፣ 0918340128 ወይም 0953600333 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ ያውቃል⁉️

በረሐ እና ባሕር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚተሙት ኢትዮጵያውያን በየመን ጦርነት እንዳለ እንኳ አያውቁም። አንድ ወደ #ጅቡቲ የተሰደደ #የመናዊ በመንገድ ያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን «ወዴት ነው የምትሔዱት? በመንገዳችሁ ጦርነት አለ ስንላቸው ፈጣሪ ያውቃል» የሚል መልስ ሰጡን ሲል ለኢኤንኤን ተናግሯል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድረ-ገፅ እደሚጠቁመው በየመን የርስ በርስ #ጦርነት

•5,900+ ሰላማዊ ሰዎች #ተገድለዋል

•9,400+ ሰላማዊ ሰዎች #ቆስለዋል

•3 ሚሊዮን ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል

•22.2 ሚሊዮን ሕይወታቸውን ለማቆየት የለት ደራሽ ዕርዳታ #ጥገኛ ናቸው

•2.5 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ እርቀዋል፤ ቢሆንም #ኢትዮጵያውያኑ ፈጣሪ ያውቃል እያሉ መንገድ ላይ ናቸው።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia