TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

የ15ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት የ3 ወራት ስልጠና ዝግጅቱን አጠናቆ ቀጠናውን ለመረከብ በድሬድዋ ኤርፖርት አሸኛኘት ተደረጎለታል።

በተመሳሳይ በዩኒሚስ ሚሽን የተሰማራዉ የ12ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ከ18 ወራት ቆይታ በኋላ በደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ግዳጁን አጠናቆ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

በተጨማሪ በዩናሚድ ዳርፉር ሚሽን የተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃም ከ 6 ወራት ቆይታ በኋላ በሱዳን ዳርፉር ግዳጁን አጠናቆ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

ሁለቱ የሞተራይዝድ ሻለቆች አመራርና አባላቱ በድሬዳዋ ኤርፖርት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ወቅት በሀገር መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቴንጀንት ዝግጅትና ስምሪት ቡድን መሪ ኮ/ል ጌታቸው አስማረ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...የግድቡን 2ኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባል" - የሰራዊቱ አባላት

የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገሪቱ ሰላም እና ለህዳሴው ግድብ ዕውን መሆን የማንከፍለው መስዋዕትነት የለም ብለዋል።

ይህንን ያሉት በቀጣናው ላይ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ናቸው።

የሰራዊት አባላቱ የሀገሪቱ ሰላም ሆነ ልማት በውጪ ኃይሎች ፍላጎት እና በውስጥ ባንዳዎች ተላላኪነት አይደናቀፍም ብለዋል።

የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባልም ሲሉም ተናግረዋል።

መላው ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበትን የህዳሴ ግድብ ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል ተልዕኮ ተቀብለው በቀጣናው መሰማራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለስኬታማነቱም ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን 528 ቤቶች በዚህ አመት ለዕጣ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ይህን ያሳወቁት የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሜ/ጀ ኩምሳ ሻንቆ ናቸው።

ፋውንዴሽኑ ሲመሰረት የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት እና ሰራዊቱን የቤት ባለ ቤት ለማድረግ ታስቦ መሆኑን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት 3 ሺ12 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ 528 ቤቶች ደግሞ በዚህ አመት ለዕጣ ተዘጋጅተዋል።

ሜ/ጀ ኩምሳ እንዳሉት ፦ በቃሊቲ ቁጥር 1 ሳይት 584 ቤቶች ፣ ቃሊቲ ቁጥር ሁለት 504 ቤቶች በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ 1ሺ88 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ ፣ ግንባታቸው 56% ደርሷል።

በቢሾፍቱ አካባቢ 2 መቶ ባለ 1 እና ባለ 2 መኝታ ቤቶች እየተገነቡ ነው። አፈጻጸማቸው 76 በመቶ ደረሷል፤ በአሁኑ አመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዳማ ሳይት ፣ 2 ብሎክ 80 ቤቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውንና አፈጻጸሙ 73% በመድረሱ በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በሀዋሳ ሳይት አራት ኮንራክተሮች መኖራቸውን ገልጸው ፣ 320 ቤቶች በግንባታ ላይ መሆኑንና 95% መድረሱን ተናገረዋል።

በመቐለ ሳይት 11 ብሎክ 440 ቤቶች ከ1 እስከ 3 መኝታ ቤቶች ግንባታ ላይ መሆኑን ገልፀው 'ህወሓት' በፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የግንባታ ስራው ተጓቷል ፤ የማቴሪያል ዝርፊያና አንድ ተሸከርካሪ ተወስዷል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ፋውንዴሽኑ ግንባታው 60 በመቶ የደረሰውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚጠናቀቅ አሳውቀዋል።

በባህርዳር ሣይት በ2012 ዓ/ም 312 ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ ቤቶች ተጀምረው በአሁኑ ሰኣት 52% መድረሱን ተናግረዋል፡፡

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

"የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ዓመታት ለህዳሴ ግድቡ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል" - የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኀይሉ አብርሃም እንደተናገሩት መከላከያ ሠራዊት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለግድቡ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ለግድቡ የጀመረውን ድጋፍም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድቡ 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መደገፋቸውን ያስታወሱት አቶ ኃይሉ መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነትን እና ሰላም ከማረጋገጡም ባሻገር ባለፉት አስር ዓመታት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት የግድቡን አካባቢ ከሌሎች የሰላም ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመጠበቅ ሀገራዊ አደራውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ግድቡ በአሁኑ ላይ ከ80% በላይ ደርሷል፤ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተርባይኖችም የሙከራ ምርታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ መግለፃቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀዋል።

ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀልከ ውስጥ እና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በአሚሶም ሴክተር 6 የሚገኘው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዓመታዊ የሜዳሊያ በዓሉ አከበረ።

በፕሮግራሙ ላይ የጁባ ላንድ ምክትል ፕሬዝዳት የሆኑት አቶ መሃመድ ሰይድ ተገኝተው ነበር።

ም/ፕሬዝዳት አቶ መሃመድ በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል አልሸባብን ለማጥፋት ያደረገው የግዳጅ አፈፃፀም ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለው ፤ ሰራዊቱ በድስፕሊኑ የታነፀ ከህዝቡ ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት ያለውና በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ላሳየው ቁርጠኝነት ሜዳሊያው በክብር እንደተሰጠው ግልፀዋል።

የሴክተር 6 አዛዥ የሆኑት ብ/ጄ አበባው ሰይድ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ፣ የኬንያና የሴራሊዮን የፖሊስ ሃይል እንዲሁም የUN አጋዥ ሃይሎች ዓመቱን ሙሉ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ሰላም በማስከበር ረገድ ስመ ጥር ሃገር እንደሆነች እና በተለይ በሶማሊያ የአልሸባብን ሃይል በማጥፋት እንዲሁም የገንዘብ ምንጩን በማዳከም የሶማሊያን ሰላም በማጠናከር ትልቁን ሚና እየተወጣች መሆኑን አሳውቀዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አመራሮች እና የየመስተዳድር አካላት የተካተቱበት ልዑክ ተፈናቃዮች በሚገኙበት አራት የጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ወገኖች ጋር የጋራ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል። ውይይቱ በግዜያዊ መጠለያ ጣቢያው የሚያጋጥሙ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ አተኩሮ የተካሄደ ነበር።

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት ብ/ል ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ተፈናቃዮችን ቋሚ ተፈናቃይ አድርጎ በማቆየት በግላቸው የሚጠቀሙ ሀይሎች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን የእነዚህን ሀይሎች ሴራ መረዳትና በጋራ መታገል አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለህዝቡ የሚቀርበውን የምግብ እህሎችን ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በህዝቡ ተሳትፎ በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉንም አስታውሰዋል። ይሄ ተግባር በቀጣይነት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ልዩ ልዩ የመመገቢያ ቁሳቆሶች እና ሰብአዊ እርዳታዎች መድረስ ከሚገባው ግዜ መዘግየቶች ማጋጠማቸውን የጠቆሙ ሲሆን አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ይገኛል።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ወቅት ለውትድርና ሙያ ብቁ የሚያደርጋቸውን የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ወስደው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

በምርቃት ስነስርቱ ላይ የተገኙት የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ለተመራቂ ወታደሮቹ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ጀኔራል መኮንኖች፣ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮ/ል አዲሱ ተርፋሳ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል ፤ ከሀገር መከላከያ እና ለኢዜአ እንደተገኘው መረጃ።

NB : የሁርሶ የሰላም ማስከበር ማዕከል በምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ እና አንጋፋ ከሚባሉት ማሰልጠኛዎች መካከል ተጠቃሽ ነው።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ማስለቀቁን አስታወቀ።

የመከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው እርምጃ፦ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ ጎብጎብ፣ ሳሊና ንፋስ መውጫ ነፃ ማውጣቱን ገልጿል።

የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ህወሓት በንፋስ መውጫ ከተማ ንፁሃንን መግደሉንና በርካታ ውድመት ማድረሱን የተናገሩ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደከተማቸው ሲገባ አቀባበል አድርገዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፤ ከሰሞኑን ህወሓት ህዝቡን በጣም እንደጎዳው፤ የቀረ ነገር ሳይኖር ዘርፊያ እንደፈፀመ ገልፀው፥ "ህዝባችን እንዲህ ያለ ወራዳ ተግባር ማየቱ የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑ ዋጋውን እያገኘ ነው" ብለዋል።

ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ፥ "ህወሓት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በሙሉ የማስለቀቅ እና የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ከመኪና ወርዶ እየተበታተነ ነው እሱን የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው፤ የሚሸሽበትም መንገድ ተዘግቷል፤ ትግራይ ውስጥ ያየውን ጉድ እዚህም ያየዋል፤ እዚህ ገብቶ መውጣት የሚባል ነገር እንደሌለ ያየዋል" ብለዋል።

አዛዡ ፥ ህወሃት ስርዓት መቀየር ነው ፍላጎቴ ይላል እንጂ ተግባሩ ሀገር ማፍረስ እና ሀገር ማውደም ነው ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው የማፍረስ ምልክቱም ህዝቡን ምን እያረገው እንዳለ ማየት በቂ ነው ፤ የከተማውን ህዝብ ጠይቁ ምን አድርጓቸው እንደሄደ፤ እነሱ የስርዓት አራማጅ አይደሉም ፤ ድሆች ናቸው ፤ ከድሆቹ አፍ ነጥቆ ሽሮ ሳይቀር እየጫነ እየወሰደ ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENDF-08-23

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ የጦር ፍርድ ቤት በሀገር እና በሀገሪቱ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ባላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የተከሰሱበት ክስ ዋና ጭብጥ ምንድናቸው ?

- ከሀገር አፍራሽ አሸባሪዎች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል፣
- ክህደት በመፈፀም ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ለመቀላቀል በማሴር፣
- ሽብርተኛ ተብሎ ለተፈረጀው የ "ሸኔ" ቡድን መረጃ ማቀበል፣
- ከግዳጅ ቀጠና በመሸሽ የወገን ጦርን ለአደጋ ማጋለጥ፣
- ያለ በቂ ምክንያት ሲቪሎችን በመግደል፣
- የበላይን ትዕዛዝ ችላ በማለት ለንፁሐን ሞት ምክንያት መሆን
- የመንግሥትና የህዝብን ወታደራዊ ንብረትን ይዞ ለመሸሽ ሙከራ ማድረግ የሚሉ ክሶች ዋነኛ ጭብጥ ሆነው ቀርቧል፡፡

ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ሲመረምር ቆይቶ ተከሳሾች እራሳቸውን መከላከል ባለመቻላው የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

1. ሻለቃ ክፍሌ ካሳይ በ17 አመት ፅኑ እስራት
2. ኮሎኔል ክፍሌ ፍሰሃዬ በ14 ከ 2 ወር ፅኑ እስራት
3. ሀምሳ አለቃ መብራቱ ጥላዬ በ18 አመት ፅኑ እስራት
4. መሰረታዊ ወታደር መኮንን ክንፈ በ13 አመት ፅኑ እስራት
5. ሀምሳ አለቃ ፈረደ ይባስ በ11 አመት እስራት
6. ምክትል አስር አለቃ ሀጎስ በርሄ በ11 አመት ፅኑ እስራት
7. ምክትል ክፍሌ ንጉስ በ9 አመት ፅኑ እስራት
8. ኮሎኔል ካሱ ሀብቱ በ11 አመት ከ2 ወር
9. ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋ በ8 አመት ፅኑ እስራት
10. ሌተናል ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ በ10 አመት ከ2 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወታደራዊ ፍ/ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopia