TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,500 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 75 ወንድ እና 54 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት…
#TikvahEthiopia #AtoKanGalwak

በጋምቤላ ክልል የተመዘገበው የመጀመሪያው ኬዝ !

የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካን ጋልዋክ ዛሬ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ28 ዓመት እድሜ ያለው ደቡብ ሱዳናዊ መሆኑን ነገረውናል።

ድንበር ከተዘጋ በኃላ ደንበሩን አቋርጦ ወደ ጋምቤላ ክልል የገባና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ነው።

ግለሰቡ ወደ ማቆያ እንዲገባ የተደረገው የዛሬ ሁለት ሳምንት ሲሆን በተደረገለት ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። ወደ ህክምና ማዕከልም እንዲገባ ተደርጓል።

ከእሱ በተጨማሪ ወንድሙ አብሮት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን በተደረገለት ምርመራ ከቫይረሱ #ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ደንበር በማቋረጥ ተደጋጋሚ ምልልሶች የነበሩት ሲሆን ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎችን ወደ ኳራንቲን ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia