TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 የደመቀችበት የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። ዛሬ በተካሄደ የ3000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል። የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል። ሁሉንም የስፖርታዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethsport…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ከዓለም #1ኛ ሆና አጠናቀቀች።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም አንደኛ ሆና አጠናቀቀች።

#አሜሪካ ሁለተኛ ፤ #ቤልጂየም ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ፦

🥇4 ወርቅ፣
🥈3 ብር፣
🥉2 ነሃስ፣ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎች ማግኘት ችላለች።

እንኳን ደስ አላችሁ !

@tikvahethiopia
"ደህንነት ያለበት፣ ሰላማዊ የሆነ፣ የሚያስተማምን ቦታ የመጣን መስሎኝ ነበር ግን ልጄ በጥይት ተመቶ መገደሉ ከማስበው በላይ ሆኖብኛል" - ወላጅ እናት

በፖሊስ እና መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በተደጋጋሚ ሰው በሚገደልባት ሀገረ #አሜሪካ ከሰሞኑን በርካቶችን ያስቆጣ ግድያ በፖሊስ ተፈፅሞ ነበር።

ግድያው በሚቺጋን ግዛት የተፈፀመ ሲሆን በነጭ ፖሊስ የተገደለው የ26 ዓመቱ ወጣት የኮንጎ ስደተኛ ፓትሪክ ልዮያ ነው።

ፖሊስ፤ ወጣቱ ስደተኛ የሚነዳው መኪና ታርጋው ከመኪናው አይነት ጋር ባለመገናኘቱ ትራፊክ እንዳስቆመው ገልጿል፤ በኃላም በነጭ ፖሊስ ተተኩሶ ተገድሏል።

የፓትሪክ ወላጅ አባት ፒተር ልዮያ ሁኔታው እጅጉን እንዳሳዘናቸው ገልፀው ፤ " እዚህ አሜሪካ ውስጥ ሰው ባለበት የሚገደልበት አይነት ግድያ እንዳለ ፤ጥይት በያዘ ሰው እና በፖሊስ ሰው እንደሚገደል አላውቅም ነበር ፤ እኔ የማውቀው አሜሪካ ውስጥ ፖሊስ ስታገኝ ደህንነት እንደሚሰማህ ነበር " ብለዋል።

ወላጅ እናት ዶርካስ ልዮያ በመሪር ሀዘን ውስጥ ሆነው ፤ " ኮንጎን ጥለን የወጣነው የምንኖርበት አካባቢ ደህንነቱ አስተማማኝ ስላልነበረ ነው። ጦርነት ነበር ስለዚህ ደህንነት ያለበት ሰላማዊ የሆነ የሚያስተማምን ቦታ የመጣን መስሎኝ ነበር ግን ልጄ በጥይት ተመቶ መገደሉ ከማስበው በላይ ሆኖብኛል " ብለዋል።

ወጣቱን የኮንጎ ስደተኛ የገደለው ስሙና ማንነቱ ይፋ ያልተደረገው ፖሊስ ደሞዝ እየተከፈለው እረፍት እንዲወስድ ተደርጓል።

የሚቺጋን ፖሊስ ሁኔታውን "እያጣራ" ነው የተባለ ሲሆን የፓትሪክን ቤተሰቦች የወከለ ጠበቃ ፖሊሱ ላይ ክስ እንዲመሰረትና ህግ ፊት እንዲቀርብ እንደሚፈልግ ማሳወቁን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

➡️ #አሜሪካ - በኒውዮርክ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፉ በመሳሪያ የገዙ ጥቃቶችን ለማውገዝ የተካሄደ ነው። ሰልፉ የተካሄደው አንድ ወጣት በቴክሳስ ሮብ በሚሰኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 19 ህፃናት ተማሪዎችን እና 2 መምህራንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ ከቀናት በኃላ ነው።

➡️ #ስፔን - በሰሜናዊ ስፔን ላ ሪዮጃ ክልል በባዮዲዝል ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 2 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

➡️ #የመን - በየመን አደን ከተማ ሰዎች በሚበዙበት በተጨናነቀ ገበያ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 4 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል፤ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዳለሁ ብሎ ብቅ ያለ የለም።

➡️ #ሱዳን - ከወራት በፊት በሱዳን የተካሄደውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም ያልበረደ ሲሆን ትላንትና በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል። የጥቅምቱ መፈንቅለ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካዊ ቀውስ አስገብቷል።

➡️ #ጣልያን - የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የሩሲያው ፕሬዜዳንህ ፑቲን አሁን ላይ በዓለም የሚየው የምግብ ችግር "በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ነው " ብለው እንደነገራቸው ተናግረዋል። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ አንስቶ ምዕራባውያን ሀገራት ሩስያ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሚባሉ ማዕቀቦችን እየጣሉ እንደሆነ ይታወቃል። ለእነዚህ ማዕቀቦችም ሩስያ ምላሽ ከመስጠት ወደኃላ አላለችም።

➡️ #ቱርክ #ፈረንሳይ - የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የስውዲን እና ፊንላንድ ለNATO አባልነት ባቀረቡት ማመልከቻ፣ በዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 📣

➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።

➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።

➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።

➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።

➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።

#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል። ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…
#አሜሪካ

በአሜሪካ ኦክላሆማ ግዛት ቱልሳ በተሰኘች ከተማ ሆስፒታል ውስጥ በተከፈተ ተኩስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ትኩስ እንደከፈተ የተጠረጠረው እና ጠመንጃ እና ሽጉጥ ታጥቆ የነበረው ግለሰብ መሞቱንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ፖሊስ ጥቃቱ በተሰነዘረበት ቅዱስ ፍራንሲስ ሆስፒታል በሦስት ደቂቃ የደረሰ ሲሆን በጥቃቱ የሚጎዱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በስፍራው በአስቸኳይ መድረሱ ተገልጿል።

ትላንት ረቡዕ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በርካቶች መቁሰላቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።

የቱልሳ ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ ኤሪክ ዳላግሊሽ " አሁን ላይ አራት ሲቪል ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ጥቃት አድራሹም ሞቷል " ብለዋል።  

እስካሁን ማንነቱ ያልተለየው ጥቃት አድራሽ እራሱ ሳያጠፋ እንዳልቀረ ተገምቷል።

ተጠርጣሪው ሁለት መሳሪያዎችን ታጥቆ የነበረ ሲሆን " አንደኛው ረዝም ያለ፣ ሌላኛው ደግሞ የእጅ ሽጉጥ ነው በስፍራው የተገኘው " ብለዋል የፖሊስ ኃላፊው። 

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #አሜሪካ #ሩስያ

በመጪዎቹ ቀናት ኢትዮጵያ የሩስያ እና የአሜሪካ ባለስልጣናትን ታስተናግድለች።

ነገ ማክሰኞ የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

ለቭሮቭ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ነገ አዲስ አበባ የሚገቡት።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ፦
- በኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፤
- ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ላይ ይመክራሉ፤
- ከአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ላቭሮቭ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እ.ኤ.አ 2018 ላይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ነበር።

(ሰርጌ ላቭሮቭ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ #በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል)

#US የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከሐምሌ 17- ሐምሌ 25 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ በግብፅ፣ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት ያደርጋሉ።

በኢትዮጵያ ግብኝታቸው የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ሊደረግ የታሰበው የሰላም ድርድር ላይ ይወያያሉ።

በተጨማሪ ፦
- የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ያለበትን ሁኔታ ይገመግማሉ።
- በጦርነቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ ማድረግን በተመለከተ ይመክራሉ።

ሐመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ ወደኢትዮጵያ ሲመጡ ሁለተኛቸው ይሆናል ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው ከምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም።

(ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት #በግብፅ ጉብኝት ያደርጋሉ)

@tikvahethiopia
#አሜሪካ #ቪዛ

" አንዳንድ ተጓዦች የቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ድረስ ይፈጅባቸዋል "

ለጉብኝት ፣ ለሥራ ወይም ለመኖር ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚጠይቁ አመልካቾች ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ " እጅግ የተራዘመ " ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው ሰሞኑን ከወጡ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃዎች እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

አንዳንድ ዓለምአቀፍ ተጓዦች የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚፈጅባቸው ተናግረዋል።

በካቶ ኢንስቲትዩት የስደተኞች ፖሊሲ ኃላፊ ዴቪድ ቤየር ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤ " በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለ2 ዓመታት መዘጋታቸውና ቪዛ ‘መስጠት ማቆማቸው የፈጠረው ችግር ነው’ " ብለዋል።

“ በወረርሽኙ ምክንያት የተከማቸ ሥራ አለ፤ ከአንድ ዓመት በላይ ቀጠሮ ያስፈለገውም ለዚሁ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

የቀጠሮ ርዝመት ከኤምባሲ ኤምባሲ ቢለያይም ‘አሁን ያለው ሁኔታ ግን ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ የከፋ ነው’ ሲሉ ቤየር ገልፀዋል።

ከጥቃቱ ሁለት ዓመታት በኋላ ጉዳይ ለማስፈፀም የሚወስደው ጊዜ ሦስት ሳምንት ያህል እንደነበር አንድ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ በወቅቱ ለአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ለአንዳንድ ቪዛ አመልካቾች ቃለ መጠይቅ ለማደረግ ከ1 ዓመት በላይ ሲወስድ የንግድና የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ደግሞ ከ6 ወራት በላይ እንደሚጠብቁ ተገልጿል።

አሜሪካ ለ40 ሃገሮች ተጓዦች ያለ ቪዛ ገብተው ለዘጠና ቀናት እንዲቆዩ እንደምትፈቅድ የአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#USAirstrike

የአሜሪካ አየር ጥቃት - በጎረቤት ሶማሊያ !

በጎረቤታችን ሶማሊያ ሂራን ክልል የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ኃይል የፀረ ሽብር ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን ጦሩን ለመደገፍ #አሜሪካ የአየር ጥቃት መሰንዘር መጀመሯ ተገልጿል።

አሜሪካ የአየር ላይ ጥቃቱን እንድትሰነዝር የተጠየቀችው በሶማሊያ መንግስት መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

በክስተቱ ንፁሀን ዜጎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም የተባለ ሲሆን አሜሪካ ለሶማሊያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር። በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ…
#TanaForum

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ፦

" ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል፤ ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን የነበረንን ስልጣኔ ተመልከቱ፤ በግብጽ የነበረንን የቀደመ ስልጣኔ አስቡ፤ ችግራችን የነበረንን ጥንታዊ ስልጣኔ እና ታሪክ በተገቢው መንገድ ለልጆቻችን አለማስተማራችን ነበር። አሁን ግን ለልጆቻችን ከማስተማራችን በፊት ስለራሳችን የተሳሳተውን እይታችን ማረም ይገባናል።

አዎ ! ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት #አሜሪካ ለሀገሬ ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ምግብ እረድታ ይሆናል፤ ነገር ግን አሜሪካ የረዳችን ከችግራችን በምንወጣበት መንገድ አልነበረም።

ግብርናችን እንዲሻሻል፣ ቴክኖሎጂ እንድንጠቀም እና የተሻሻለ አሰራርን እንድንተገብር ተደጋጋሚ ድጋፍ የጠየቅናት አሜሪካ በፖሊሲ ሰበብ ፈቃደኛ አልነበረችም።

ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሻግራ እንደ ሀገር ንጉስ ሰለሞንን ስትጎበኝ አሜሪካ እንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አትታወቅም ነበር።

ከኋላ እየመጡ ለሚቀድሙን ሁሉ እርግጥ ነው ኅላፊነቱን መውሰድ ያለብን ራሳችን ነን።

የጣና ፎረም መንፈስም ችግርን በግልፅ ተናግሮ በጋራ እና በትብብር መፍትሔ መፈለግ ነው። "

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ 500 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባች እንደሆነ ፕሬዜዳንቷ ገልፀዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደራቸው በመላ አገሪቱ 500,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሆነ አሳውቀዋል። በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀገሪቱም ይህንን በእጅጉ እያበረታታች ነው። በአሜሪካ…
#EV

አሁን ላይ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።

ከዓለማችን ሀገራት መካከል #አሜሪካ በ2050 ከካርቦን-ነፃ እንድትሆን አሽከርካሪዎች በነዳጅ ኃይል ከሚሰሩ ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ታምናለች።

በ2030 ከአዳዲስ የመኪና ሽያጭ ግማሹ የኤሌክትሪክ/ ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ግብ አላት፤ እ.ኤ.አ. በ2030 ግማሹ ኤሌክትሪክ ከሆኑ፣ በ2050 በአሜሪካ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መኪኖች ከ60-70 በመቶ የኤሌክትሪክ / ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ሊሸፍኑ ይችላሉ።

ለዚህም የመኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች በስፋት እየተገነቡ ይገኛሉ (እስከ 2030 ደረስ 500,000 የመገባት እቅድ አላት) ።

አሁን ላይ አሜሪካ ምን ያህል ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች አሏት ?

(እንደ ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ መረጃ)

- 126,500 ደረጃ ሁለት (የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በ5 ሰዓት ሙሉ የሚያደርጉ) ጣቢያዎች፤

- 20,431 ደረጃ 3 (ከ15-20 ደቂቃ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን 80% የሚያደርጉ)  ጣቢያዎች፤

- 16,822 የቴስላ ሱፐርቻርጀር እና የቴስላ ቻርጅ ማድረጊያ መዳረሻዎች አሉ።

ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ፤ በ2025 እስከ 7.8 ሚሊዮን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ሊኖሩ እንደሚችሉ ተንብዮ ለዚህም 700,000 ደረጃ ሁለት እና 70,000 ሶስት የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ሊኖሩ ይገባል ብሏል።

በ2030 ደግሞ 28.3 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም 2.13 ሚሊዮን የደረጃ 2 እና 170,000 ደረጃ 3 የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ያስፈልጋሉ።

ይሄ የመኪና ባለቤቶች በቤታቸው ከሚገጥሙት የቻርጅ ማድረጊያ ተጨማሪ ነው።

@tikvahethiopia