TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ?
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል።
የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ?
- ነሃሴ 13 / 2015 ዓ/ም በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአፍሪካ ፣ በኤስያ ፣ በሩቅ ምስራቅና በሌሎች የሚኖሩ ዳያስፓራ በጋራ ያከብራሉ ይህንን ከመቐለ ከሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት ይተሳሰራል።
- ነሃሴ 15 የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።
- ከነሃሴ 16 እስለ ነሃሴ 24 በሁሉም የትግራይ አከባቢዎች የኣሸንዳ ልጃገረዶች የጎደና ጨዋታ ይካሄዳል።
- ነሃሴ 28 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበር ሲሆን ፤ የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚታወቅ ይሆናል።
- ከአገር ውጭ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ይከበራል።
ከዚህ ውጭ የሚካሄድ የኣሸንዳ በዓል ዝግጅት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና የሌለው መሆኑን የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በይፋ አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፤ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ ቢሮው ከነሃሴ 18 በፊት የኣሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ እንዲከበር እውቅናና ድጋፍ የሰጠው ድርጅት የለም ብለዋል። " እውቅናና ድጋፍ ተሰጥቶኛል " በሚል በቢሮው ስም የሚንቀሳቀስ ካለ ህዝቡ ለቢሮው ጥቆማ እንዲሰጥ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia