TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረማያ ዩኒቨርስቲ‼️

የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ ነው ተብሏል፡፡ በዩኒቨርስቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ትምህርት መጀመራቸውን ተሰምቷል፡፡ የዋና ጊቢ ተማሪዎች ግን እስካሁን ወደ ክፍል አልገቡም ነው የተባለው፡፡

ለትምህርት መቋረጡ ምክንያት የሆኑ ተማሪዎችንም ዩኒቨርሲቲው በማጣራት ላይ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ሕዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ለሸገር ገልጿል፡፡ ባስመዘገቡት ውጤት ምክንያት ተባርረው ጊቢ ውስጥ ቆይተው የነበሩ ተማሪዎችም ዩኒቨርስቲውን ለቅቀው እንዲወጡም ተደርጓል ተብሏል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም ቅዳሜና እሁድ ተማሪዎችን በማወያየት ዛሬ የትምህርት አሰጣጡ በተረጋጋ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንም ተሰምቷል፡፡

Via #ሸገር_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia