TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እና የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ዛሬ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል።

አሁን ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የቀድሞ ምክክሮችን በማስከተል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች በማቅረብ ላይ ናቸው።

#TikvahFamilyAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው።

እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉንም የማኅበረሰብ አካላት የሚያሳትፍ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ (የሰላም ኮንቬንሽን) ተመቻችቶ የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ ጊዜ እና የረዥም ጊዜ ግጭትን የመከላከል፣ የመፍታት እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የሚጠናከሩበት አገራዊ ፍኖተ ካርታ እንዲዘጋጅ ይፋዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ የሲቨል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ  ፤ ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት እንዲሰፍን አበክረው ጠይቀዋል።

ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ (victim centered) የተጠያቂነት ስርዓት መስፈን በሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ፍትሕ የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር፥ የበቀል እዙሪትን ለመግታት እና ለፍትሕ ተቋማት ተዓማኒነትም ዋልታ እንደሆነ ገልጸዋን።

- ለነውጥ አዘል ግጭቶች መንስዔ የሆኑ፣
- ሕዝባዊ እና ብሔራዊ ጥቅምን የሚጎዱ እና ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው ውሳኔዎችን ያሳለፉ፣
- በነውጥ አዘል ግጭቶች ውስጥ በመሳተፍ ንፁኃንን ያጠቁ፣
- የጥላቻ ንግግሮችን እና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችን በአደባባይ ያደረጉ እና ንፁኃንን ለጥቃት ያጋለጡ አካላት በነጻ እና ገለልተኛ የፍትሐዊ የምርመራ እና የዳኝነት ሒደት ተጠያቂ እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሐቀኝነት እና ሕዝባዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ ወደ ተግባር እንዲገባና በሒደቱም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ዓለም ዐቀፍ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም ዘንድ ጠይቀዋል።

" የጥላቻ ንግግሮች እና ግጭት ቆስቋሽ መልዕክቶች ነውጥ አዘል ግጭቶችን የሚያዋልዱ እና የሚያፋፍሙ መሆናቸውን ባለፉት ዓመታት አስተውለናል " ያሉ ሲሆን " የፖለቲካ ልኂቃን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የብዙኃን መገናኛተቋማት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች እና ሌሎችም የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት፣ ብሎም ሕዝብን በጅምላ ከሚፈርጁ ወይም ግጭቶችን ከሚቆሰቁሱ እና ከሚያባብሱ የቋንቋ አጠቃቀሞች እና መልዕከቶች ራሳቸውን እንዲቆጥቡ " አሳስበዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ። ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው። እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። …
የአዲስ አመት የሰላም ጥሪ !

35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ፦

- አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ይመቻች
- ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት ይስፈን
- ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸው
- የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ ይዘርጋ
- ሕዝባዊ ተሳትፎ ይረጋገጥ
- የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት (Early warning System) ይኑር
- የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሳይስተጓጎል ይቀጥል
- የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም
- የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ ይደረግለት
- ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ይወጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ጥሪያቸውን ያቀረቡት ዛሬ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ነው።

35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዲስ አበባ ተመሳሳይ " የሰላም ጥሪ " ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ከመንግስት መጣን ባሉ አካላት መከልከላቸውና መግለጫቸውን በኦንላይን ለመስጠት መገደዳቸው ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት…
#Update

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ " ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል " የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንድ ስማቸውን እንዲገለፅ ላልፈለጉ የዩኒቨርስቲው አካል ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚህ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ በትላንት በስቲያ ምሽቱ ተኩስ ተማሪ ላይ ያተኮረ / ተማሪ ላይ ታርጌት ያደረገ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጸዋል።

" ተማሪዎች እንጠራ ብለው በተደጋጋሚ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀዋል። ትምህርት ሚኒስቴርም ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ነው ዩንቨርሲቲው ሊጠራ የቻለው " ሲሉ አስታውሰዋል። 

" ዩንቨርሲቲው አሁን ላይ እያስተማረ ነው። ተማሪዎችም ትምህርት ጀምረዋል። በርከት ያሉ ተማሪዎች መጥተዋል። በዚህ መንገድ ደግሞ ተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ነገሮች አሉ። ዩንቨርሲቲው አቅም እስከፈቀደለት ድርስ ትምህርቱን ይቀጥላል። በመካከል ተማሪዎች ለራሳቸው የሚፈሩት፣ የሚሰጉት ነገር ካለ አይገደዱም " ሲሉም አክለዋል።

" ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማንም አይገምትም። ማንም ለማንም ዋስትና መሆን አይችልም። By theway በዚህ ጊዜ ላይ ከባድ ነውና ሁሉም ተማሪ ለራሱ ዲሳይድ ማድርግ መቻል አለበት " ያሉት እኚሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ " ሲመጡም ያንን ተገቢ ግምት ውስጥ ያስገባሉ ተብሎ ነው የሚታሰበው። ተማሪዎች  መማር አለብን ብሎ የሚያስብ ከሆነ ማስቀጠል እስከተቻለ ድረስ ይማራሉ " ብለዋል።

አክለውም " ይህንን ዓመት Withdraw ማድልግ እፈልጋለሁ የሚል (ተማሪ) አይከለከልም። ተማሪ በራሱ አምኖበት የሚያደርገው ስለሆነ በዩኒቨርስቲ በኩልም አይጠየቅም " ያሉ ሲሆን " ሁኔታው ግን እስከመቼ እንደዚህ ይቀጥላል ? የሚለው ነገር እንዲህ ነው ብዬ ማለት አልችልም/አላውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የጸጥታው ሁኔታ አጠቃላይ በአገሪቱም፣ በክልሉ አግሪቬት እያደረገ በሄደ ቁጥር ዩኒቨርሲቲዎች ሴንተር ሊሆኑ ይችላሉ። እከባለፉት ዓመታት ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ካየነው ሁኔታ አንጻር፣ ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰቡ ነፀብራቅ ስለሆኑ እዚያ (ውጭ ላይ) የተፈጠረው ነገር እዚህም (ዩኒቨርሲቲ ውስጥ) ይፈጠራል " ብለዋል።

የሁኔታውን አሳሳቢነት በተመለከተ በሰጡት ቃልም፣ " Risk free የሆነ Environment የለንም። ምንም ስጋት የሌለበት ሁኔታ የለም። አሁን ከሚታዩት ነገሮችም አንጻርም፣ ከዚህ በኋላም ማለቴ ነው ፤ Risk free zone ስለሌለን ተማሪዎች መወሰን አለባቸው " ብለዋል።

ተማሪዎች በበኩላቸው " የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ውይይት እያደረጉ ነበር " ቢባልም የመፍትሄ ሀሳብ እንዳልተነገራቸው፣ ቢያንስ ሰላም ወዳለበት ካምፓስ እንዲያዘዋውሯቸው ጠይቀዋል።

ይህን ተከትሎም ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርጋችሁ ? ሲል ጠይቋል።

" እንኳን እንዲህ አይነት ነገር ተፈጥሮ ሁሌም አስቸኳይ ስብሰባ አለ " ሲሉ ገልጸው፣ " ችግር ተፈጥሮ በጉዳዩ ዙሪያ ሳይወራ አይቀርም። ካምፓስ ተቀይሮ የሚመጣ ለውጥ አለ ወይ? Through time long run ምን ይፈጠራል ? የሚለውን analaysis ሲሰራ ካምፓስ መቀየር ዘላቂ የሆነ Problem solve mechanism ነው ? የሚለው ነገር ላይ ያጠራጥራል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለው፣ " እስከመቼ ድረስ ቀይረህ ትችለዋለህ ? ደግሞስ ካምፓስ ተቀይሮ ምን ያህል ይችላል ? አንድ ካምፓስ ምን ያህል ይችላል ? የሚሉት ጉዳዮች አሉ በዚያው ልክ። ለተማሪዎቹ imidate የሆነ መፍትሄ እየተፈለገ ነው። ግን ዘላቂያዊነቱ ላይ ነው ትንሽ ጥያቄ ያለው " ሲሉ አስረድተዋል።
#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ አጎና (የጎተራ ኮንዶሚኒየም መግቢያ) በሚገኝ ህንፃ ላይ ምሽቱን የእሳት አደጋ መነሳቱን የአካባቢው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የእሳት ደጋው ከተነሳ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዳለፈውና የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እሳቱ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን በህንፃውን አንደኛው ጎን ውስጥ የነበሩ ንብረቶች እየወደሙ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
#ዎላይታ

“ ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው ” - አንድ የጤና ባለሙያ

“ ዞኑም፣ ከተማ አስተዳደሩም ሆስፒታል ቢኖር የሚል ሀሳብ አለው ” - የወላይታ ሶዶ ዞን ጤና መምሪያ።

በወላይታ ዞን የሚገኙ አንድ የጤና ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ የመንግሥት ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው " ብለዋል።

" እንደ አገር የሚተገበረው የሕዝብ ጤና ተቋማ ጥምርታ ሌሎች አካባቢዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ያለ ቢሆንም ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ግን ተግባራዊ አልሆነም " ሲሉ ወቅሰዋል።

" የሕዝብ ብዛት ከ1 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ከሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ተሰርቶ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት ይገለጻል። የቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ ከ1 ሚልዮን እንደሚበልጥ ይገመታል። ህዝቡ ግን ይህንን ሰብአዊ መብት ለማግኘት አልታደለም " ብለዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ አነጋግሯል።

ምን መለሱ ?

አረካ እና ቦሎሶ ሶሬን አማክሎ አገልግሎት የሚሰጥ ዱቦ የመጀመሪያ ደረጃ የግል ሆስፒታል አለ። የሕዝቡ ቅሬታ ‘የመንግሥት ሆስፒታል ለምን አይኖርም’ የሚል ነው ቅሬታው አግባብነት ያለው ነው።

ሌሎችም ምንም አይነት ሆስፒታል የሌለባቸው አካባቢዎች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየገነባ ነው የቆየው ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይኼኛውም አካባቢ (ቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ) በመንግሥት ሆስፒታል ተደራሽ ቢሆን ጥሩ ነው የሚለውን እንደ ዞን መግባባት ላይ እየደረስን ነው።

እንደ ዞን፣ የከተማ አስተዳደርም ይሄ ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ተቀብሏል። ጥያቄው እንደ ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን፤ ለግንባታው የሚያስፈልገው በጀት እንዲታቀድበት፣ በመደበኛ የመንግሥት በጀት እንዴት መስራት እንደሚቻል እየታሰበበት ነው።

በሌላ በኩል ቅሬታ አቅራቢ ጤና ባለሙያው በበኩላቸው፣ “ ለህዝብ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሠሩ ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም ብዙዎቹ #ዝግ_ናቸው” ብለዋል።

አንድ የግል ሆስፒታል ቢኖርም ለመታከም የዋጋ መናር እንደሚስተዋልበት፣ የብቁ ቀዶ ጥገና ችግር እንዳለ፣ በዚህም አንዲት እናት ችግር እንደደረሰባቸው፣ የጤና ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት ሙያ ውጪ ስለሚሰሩ ከዚህ በፊት ሁለት እናቶች እንደሞቱ አስረድተው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ትክክል ነው። ያለው ሂደት አጠቃላይ ዝርዝሩን እኛም ይዘናል። ሕዝቡም ያነሳል፣ ትክክል ነው። የሕክምና ባለሙያዎች (የዱቦ ሆስፒታል) አሁን በቂ እውቀት ያላቸው ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ነው። አጋጣሚ የተፈጠሩ ክፍተቶች ለምን ተፈጠሩ የሚለውን እናያለን።

በእኛ ደረጃ ዝግ የሆነ ጤና ጣቢያ የለም። ጤና ባለሙያ ተመድቦ ሁሉም ጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው በሥራ ሰዓት። ግን አልፎ አልፎ ከትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት ‘አልተከፈለም’ በሚል ሥራ ቦታ ላይ የባለሙያ አለመገኘት ሁኔታዎች አሉ።

የጤና ባለሙያው በበኩላቸው ፦
- የትርፍ አበል አለመከፈል፣
- በደመወዝ መቆራረጥ ምክንያት ቅሬታ ስላለ፣ ሌጋማ፣ ዎይቦ፣ ጋራ ጎዶ፣ ባንጫ እና ሌሎች ጤና ጣቢያዎች በቀን አንድ ባለሙያ ገብቶ የሚመጡ ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ መረጃ ከመስጠት ውጭ የሚሰጠዉ አገልግሎት የለም " ብለዋል።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

“ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን። 2.8 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ አልተለቀቁም ” - እምባ የሚተናኘቃቸው የታጋች እህት

መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ባቱ (ዝዋይ) እየተጓዙ የነበሩና በ “ ሸኔ ” ታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ሁሉም እንዲለቀቁ 2.8 ሚሊዮን ብር ተዋጥቶ ቢላክም 3ቱ ተለቀው 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ የታጋች ቤተሰብ በእንባ እየተናነቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል “ ከአቅሜ በላይ ” ነው እንዳላቸውና በከፋ ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑም እንባ አስረትድተዋል።

አንዲት የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ “ ከታጋቾቹ ሥም ዝርዝር የወንድሜም ስም ዝርዝር እንደነበረ ከእገታ የተለቀቁት ነግረውኛል። ብር አምጡ ብለው የመብራት ኃይል ሠራተኞች ሁሉ አዋጥተው 2.8 ሚሉዮን ብር ለ6ቱም ተብሎ ከተላከ በኃላ 3ቱ የኢሬቻ ዕለት ተለቀቁ፣ 3ቱ ግን አልተለቀቁም ” ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል የስራ ኃላፊዎችን ሲጠይቁ “ ከአቅማችን በላይ ነው ” ብለው “ ለፌደራል ፓሊስ አስተላልፈናል ” እንዳሏቸው፣ የፌደራል ፓሊስም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልሰጣቸው ጠቁመዋል።

በቤተሰብና ወዳጀ ዘመድ በኩል ለታጋቾች ተብሎ 300 ሺህ ብር እንደተላከ፣ ወንድማቸው፣ ሹፌሩ እና አንድ ሌላ ሠራተኛን ጨምሮ ከታገቱ 6 ወራት እንዳስቆጠሩ፣ ቤተሰብም በከፋ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።

“ ወንድሜ ሁለት ልጆች አሉት ፣ ሚስቱ የስኳር ታማሚ ናት። ሹፌሩም 2 ልጆች አሉት፣ ሚስቱ ሞታለች ” ያሉት የታገቹ እህት፣ “መለቀቅ እንኳ የማይቻል ከሆነና በሕይወት ካለ፣ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን " ሲሉ ተማጽነዋል።

ምንም እንኳን ለማስለቀቂያ 2.8 ሚሊዮን ብር ቢከፈልም ከታገቱት 6 ሰራተኞች ውስጥ 3ቱ ሲለቀቁ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ ያልተለቀቁ ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን አሁን 6 ወራት እንደሞላቸው የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በሀዘን ስሜት ሆነውም መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል ካለ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የጠየቅን ሲሆን ምላሹን እናቀርባለን። #TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት

በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣ ከ3 ጊዜ በደብዳቤ ቢጠይቁትም መፍትሄ እንዳልሰጣቸው፣ በመሆኑም መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ኃላፊዎቹ እና እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢዎች ጠይቀዋል።

ኃላፊዎቹና በእንባ የታጀቡት ቆጣቢዎቹ ይህን ያሉት ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ የተፈጠረውን ቅሬታ መነሻና ሂደትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ለማኀበሩ ጥያቄ አቅርቧል።

የቱሪስት ታክስ ማኀበራት ኃላፊ አቶ ግዑሽ መብራህቶም ምን አሉ ?

➡️ “ ከ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ በሚባል ድርጅት መኪና ያስገባል ወይም ገጣጥሞ ይሰጠናል በሚል ነው የነበረን ሂደት። ነገር ግን በዚህ መሠረት መኪናውን ማስረከብ አልቻለም። ይህም ብቻ አይደለም ‘መኪናውን ካላስረከበ ገንዘባችን ይመለስን’ ብለው የሚሄዱ አባላት ለሦስትና አራት ወራት እየተጉላሉ ነው። ”

➡️  “ በ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካበቢ መኪና እናስመጣለን ብለው ማኀበራት ሲመዘግቡ እንሰጣለን ብለው ያሰቡትን ዋጋ በአማካኝ ብጠቀስ፣ 520 ሺሕ ብር ነበር። 520 ሺሕ ብር የነበረው መኪና አሁን ወደ 2 ሚሊዮን ብር አካባቢ ደርሷል። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ለኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የጻፈው ደብዳቤ ምን ይላል ?

- የቱሪስት ታክስ ማኀበራት በሄሎ ታክስ መዝጋቢነት፣ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ መኪና አቅራቢነት የመኪና ሽያጭ ውል እንደተፈራረሙ፣ 

- የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲግ በውሉ አንቀጽ 2 የውል ትርጉም መሠረት የመኪና አቅራቢ በመሆን ውሉ እንደተፈረመ፣ 

- በውሉ መሠረት እያንዳንዱ አባል ቅድመ ክፍያ እንደዬ መኪናዎቹ ሞደል 60 ሺሕ ብር እንደተከፈለ፣ በተጨማሪ ከውሉ ጋር የመኪናውን የ25% በመክፈል ከኦክሎክ የመኪናውን የቻንሲና የሞተር ቁጥር በውሉ መሠረት እንልተረከቡ ያስረዳል።

ቆጣቢዎች ምን አሉ ?

ኦክሎክ ትሬዲንግ ቢበዛ በአንድ ዓመት ውስጥ መኪናውን እንደሚያስረክባቸው በወቅቱ ገልጾላቸው እንደነበር፣ ይሁን እንጂ “ ከዛሬ፣ ነገ ይመጣል” እየተባለ በወቅቱ ሳይመጣ ዓመታት እንዳስቆጠረ፣ “ይባስ ብሎ” መኪናውን በማስረከብ ፋንታ “አዲስ ውሎ ፈርሙ” እያለ መሆኑን በቁጣ ገልጸዋል።

የቱሪስት ታክስ ማኀበር ኃላፊ በበኩላቸው ኦክሎክ ፈርሙ ያለውን አዲሱን ውል በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያብራሩ ፦ “ የማኀበራት ኃላፊዎች ባሉበትም አይደለም አዲሱን ውል እንዋዋል የተባለው። ዝም ብለው በዬማኀበራት ግለሰቦችን እየጠሩ ነው። በወሬ ወሬ ሰማነው፣ ከዚያ የሆነ አካል ፓስት አድርጎ በቴሌግራም አደረሰን። ከዚያ ሕዝቡ/ቆጣቢው ተንጫጫ። ስናየው አዲሱ ውል ከ85 በመቶ በላይ ለድርጅቱ የሚያደላ ነው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ እውነትም አቅም ካለው ውሉ መሠረት መኪናውን ያስረክብ። አቅም ከሌለው በሚመጥን ዋጋ ገንዘቡን ኳልኩሌት አድርጎ ይመልስ ” ሲሉ በአባላቱ ሥም ጥሪ አቅርበዋል።

“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው?” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናትን ጨምሮ የሌሎቹን ቆጣቢዎች የቅሬታ ቃል በቀጣይ እናቀርባለን። #TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia