TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የWFP_ማጠንቀቂያ

የተመድ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረኀብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት እንደሚጀምር አስጠንቅቋል።

የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቤስሊ ባለፈው ዐርብ  ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።

ቤስሊ ምን አሉ ?

- ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ #በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረሃብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት ይጀምራል።

- ባለፈው ዓመት፣ ከአሜሪካና ከጀርመን የተገኘውን ተጨማሪ ድጋፍ ይደነቃል ፤ ቻይና፣ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት፣ ቢሊየነር ባዕለ ጸጋዎች እና ሌሎችም ሀገራት፣ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ድጋፋቸውን ሊያፋጥኑ ይገባል።

- በ49 ሀገራት ውስጥ አስቸኳይ የሆነ #የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 350 ሚሊዮን ሰዎች ለመርዳት 23 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ይህ ገንዘብ ላያገኝ ይችላል ፤ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ኹኔታ አስጨንቆኛል።

- አሜሪካ የምትሰጠውን የገንዘብ ርዳታ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 7.4 ቢሊዮን አሳድጋለች፤ በተመሳሳይ ጀርመንም ከ350 ሚሊየን ዶላር ወደ 1.7 ቢሊዮን ከፍ አድርጋለች ፤ በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የሆነውን ኢኮኖሚ የያዘችው ቻይና ባለፈው ዓመት ለተቋሙ የሰጠችው ገንዘብ 11 ሚሊየን ዶላር ብቻ በመሆኑ ድጋፏን ልታሳድግ ይገባል።

- #የነዳጅ_ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ጋራ ተያይዞ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት የበለጠ እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ። በተለይ ከምሥራቅ አፍሪካ፣ ከሰሐራ እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጋራ ግንኙነት ያላቸው የሙስሊም ሀገራት የተሻለ አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላሉ።

- ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው በአፍሪካ የሳሕል ክልል የሚገኙ ሀገራትና ምሥራቅ ሶማሊያ ፣ ሰሜናዊ ኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣  #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ይገኙባቸዋል።

- የዓለም መሪዎች፣ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋትን ሊያስከትሉ የሚችሉ የሰብአዊ ርዳታ ክፍተቶች ለአሉባቸው ሀገራት ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።

ዴቪድ ቤስሊ በዓለም ትልቁ ሰብአዊ ርዳታ ሰጪ በሆነው ተቋም የነበራቸውን ሥልጣን በመጪው ሳምንት ለአሜሪካ አምባሳደር ሲንዲ ማኬይን ያስረክባሉ።

#VOA

@tikvahethiopia