TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sport ሰበር ዜና‼️

የሌስተር ሲቲ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሂሊኮፍተር በኪንግ ፓወር ስታዲየም የመኪና ማቆሚያ ስፍራ #መከስከሱ ተሰማ። የአደጋው መንስኤ እና በውስጡ ስለነበሩ ሰዎች ማንነት ለጊዜው የተሰማ ነገር የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ‼️

በኢንዶኔዢያ #ጃካርታ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን ለበረራ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ባህር ውስጥ #መከስከሱ ተነግሯል።

የላየን አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን 188 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር በጃካርታ ባህር ወስጥ የተከሰከሰው።

ከአደጋው እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም ብለዋል የአካባቢው ባለስልጣናት።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢራን ቦይንግ 707 የተሰኘ የጭነት አውሮፕላን ትላንት በሀገሪቱ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ አካባቢ #መከስከሱ ተገልጿል። አደጋው የተከሰተውም አስቸጋሪ የአየር ንብረት በመኖሩ ምክንያት መሆኑ ነው የተገለፀው። አንዳንድ ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ አውሮፕላኑ 10 ሰዎችን አሳፍሮ ነበር፤ #የሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወት ሳያልፍ እናዳልቀረም በስፋት እየተነገረ ነው።

ምንጭ፦ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking ባለቤትነቱ የትራንስፖርት ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ #መከስከሱ ታውቋል።

Via #reporter
ፎቶ-የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia