TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መንገድ

“ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት 4 ጊዜ ያንን አስፓልት ያሰራል ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ ግብዓቶች ፣ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ፣  ዘይት እና ሌሎች ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ግብዓቶችን የምታከናውንበት የጂቡቲ መንገድ ጥገና ካሻው ከ10 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ባለመጠገኑ በተሽከርካሪዎች ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- “ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ውስጥ እያለች ጂቡቲ ድረስ መጥታ መንገዱን አይታ የተፈራረመችው ሰነድ ነበር ከ4 ዓመታት በፊት። ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ከውሃ ልማት ዲኬል እስከሚባል ቦታ ድረስ ያለው መንገድ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ፣ የአገሪቱ ንብረት የሚወድምበት ነው። ”

- “ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት አራት ጊዜ ያንን አስፓልት ይሰራል። መንገሥት ያን መንገድ እንዲጠገን ማድረግ አለበት። ”

- “ ስምምነቱ ያለው በኢትዮጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግሥት በኩል መንገዱ መጠገን እንዳለበት ነው፣ የተሰራው 20 ኪ.ሜ ብቻ ነው። በቀሪው 80 ኪ.ሜ ብዙ ኤክስፖርት የያዙ ተሽከርካሪዎች ይወድቃሉ። ለኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክት ማሽን የጫኑ ተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆኖባቸው አንዳንዴ ማሽኑ የሚወድቅበት ሂደት አለ። ”

- “ የመንገዱን መፈራረስ ተከትሎ በከፍተኛ Currency የሚገቡ Spare parts በቶሎ ይበላሻሉ ይህም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አለው። የዚህ ችግር ዋነኛ ምክያት ደግሞ የመንገዱ አለመጠገን ነው። ”

-  “ የ80 ኪ/ሜ መንገድ #ከ10_ሰዓታት_በላይ ጉዞ ይወስዳል። ከዓመት ወደ ዓመት ችግሩ እየተባባሰ ነው የመጣው። መንገዱ የተቆፋፈረ፣ አቧራማ፣ አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ከተጠቀሱት ችግሮች በተጨማሪ ለጤናም ጠንቅ ነው። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ቶሎሳን አነጋግሯል። እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር ቶሎሳ ፦

° “ ግንባታው የዘገየገው ከዚህ በፊት በጂቡቲ በኩል በነበረ አለመግባባት ነበር፡ በኋላ ላይ ግን መግባባት ላይ ተደርሶ ጥገናው ተጀምሯል። ”

° “ የጩኸቱ መንስኤ ስላላቀ ነው እንጂ አሁን መግባባት ላይ ተደርሶ መንገዱ እየተሰራ ነው ለ2 ኮንትራክተሮች ተሰጥቶ (በእኛ እስከተወሰነ ድረስ በእነርሱ እስከተወሰነ ድረስ ያለው) ። ”

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ እውነትም አሁን በመሰራት ላይ ያለ አለ ? ብሎ ጠይቋል።

° “ Exactly አሁን በመሰራት ላይ ነው ያለው። ከጋላፊ እስከ ዲኬሌ ድረስ (ወደ ጂቡቲ ማለት ነው) ለቻይና ኮንትራክተር ተሰጥቶ እርሱ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። በሳዑዲ መንግሥት ነው የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገው። ከዲኬሌ እስከ ጂቡቲ ድረስ ደግሞ በእኛ (በኢትዮጵያ) በኩል አንድ የእኛ አገር ኮንትራክተር ይዟል። ”

° “ ትንሽ ችግሩ ያለበት እርሱ ላይ ነው። ለችግሩ መንስኤው የፋይናንስ አጥረት ነው። በአጠቃላይ የግንባታውን ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል። ”

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia