TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016…
#Oromia

ኢሰመኮ ፦

- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።

- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤ 
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።

- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። 

- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።

ለምሳሌ ፦

👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።

👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።

👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።

👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

#Oromia #Ethiopia #EHRC

@tikvahethiopia