TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉምዝ
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ #አሰማኸኝ _አስረስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በነበረው ግጭት ዙርያ ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተናገሩት፦

"በቤንሻንጉል ሰሞኑን በነበረው ሁከት በአማራ ተወላጆች (በአካባቢው 'ቀይ' ይባላሉ) ላይ የግድያ፣ የዘረፋ እንዲሁም የማሳደድ ተግባር ተፈፅሟል። እስካሁን ባለኝ መረጃም ወደ 17 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 11ዶቹ የአማራ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የአካባቢው ሰዎች ናቸው። እስካሁን መረጃ ባልተሰበሰበባቸው አካቢዎች ሌሎች ሰዎች ተገድለውም ሊሆን ስለሚችል ማጣራት እያረግን ነው። ግጭቱ የጀመረው ሚያዝያ 17 በዳንድር ወረዳ ሲሆን መነሻው በእቃ ጫኝ እና አውራጆች መሀል ነበር። በዚህ መሀል የአንድ የአካባቢው ሰው ህይወት ያልፋል። ከዚያ በሁዋላ ባሉት ሶስት ቀናት ያንን ለመበቀል ጥቃቶች በቀስት፣ ወንጭፍ እና በጥይት ተፈፀመዋል። #በሁለቱም ወገን የበቀል እንቅስቃሴዌች ሲደረጉ ነበር። ትናንት ብቻ በፓዌ ወረዳ አባወሬኛ ቀበሌ 25 ቤቶች ተቃጥለዋል፣ እነዚህ የጉሙዞች ቤቶች ናቸው። ዛሬ አንድ ግብረ- ሀይል ሁኔታውን ለማርገብ ወደቦታው እያመራ ነው።" @eliasmeseret

@tsegabwolde @tikvahethiopia