ጎንደር🔝
በጎንደር ከተማ ዛሬ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል በልዩ ልዩ ክንውኖች እየተከበረ ነው፡፡ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ በ1811 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡
ምንጭ:- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አሳዛኝ ዜና‼️
በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አቅራቢያ የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ አይሮፕላን በመጥፎ የአየር ሁኔታ ሊንደረደር ሲሞክር ተጋጭቶ 15 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ቦይንግ 707 የሆነው አውሮፕላኑ ከቴህራን በስተምዕራብ 40 ኪሎ ሜትር ላይ በሚገኘው ካራጅ በተባለ አውሮፕላን ማረፊያ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
አውሮፕላኑ ከመንደርደሪያው በመውጣት ነው ከሰዎች መኖሪያ ቤት ጋር የተጋጨው።
የኢራን ሰራዊት በአደጋው በህይወት የተረፈውን አንድ የአውሮፕላኑን ሰራተኛ ወደ ሆስፒታል በመውሰድ የነብስ አድን ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
የጭነት አውሮፕላኑ ከኪርጂዝ ዋና ከተማ ቢቢሽኪ ስጋ ሲያጓጉዝ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡
የአውሮፕላኑ ባለቤት ማን እንደሆነ እስካሁን በግልፅ አልታወቀም፡፡
ምንጭ፦ bbc

ባህር ዳር‼️
ከአንድ ወር ገደማ በፊት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ጥለው የወጡ ተማሪዎች #በአማራ_ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልንመደብ ይገባል የሚል ጥያቄ ይዘው በባሕር ዳር ከተማ ሰልፍ አደረጉ። በዛሬው ሰልፍ ወደ 2500 ተማሪዎች መገኘታቸውን በቦታው የተገኘው የDW ዘጋቢ ተናግሯል። ተማሪዎቹ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተነስተው እስከ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተጉዘዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ መንግሥት ቢሮ ፊት ለፊት "መንግሥት የለም! መንግሥት ቢኖር ጥያቄያችንን ይመልስልን ነበር" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የDW ዘጋቢ ታዝቧል። የጸጥታ አስከባሪዎች ኹኔታውን በርቀት ሲከታተሉ ነበር። በአብዛኛው ጥቁር የለበሱት ተማሪዎች መንግሥት ጥያቄያችንን ይመልስልን፤ በአማራ ክልል እንመደብ" የሚል ጥያቄ በሰልፉ ላይ አሰምተዋል። የኢኖቬሽን እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ይመለሱ የሚል ምላሽ ባለፈው ሳምንት ሰጥቶ ነበር። ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑት "ሴቶች ይደፈራሉ፤ ወንዶች ይደበደባሉ" በሚል ምክንያት ነው። DW እንደዘገበው ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በሚገኝ ስታዲየም ተጠልለው ይገኛሉ።
ምንጭ፦ DW

#update የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ወቅታዊ ችግሮችን ከማርገብ ባለፈ ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን ከወትሮው በላቀ እንዲወጡ ተጠየቀ። ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️
በዱቄት መልክ #አደገኛ_ዕጾችን ሲያዘዋዉር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ። ለሰው ልጅ ጤና ጉዳት የሚያደርሱ የተከለከሉ አደገኛ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰው የውጭ ዜጋ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ሚስተር ዳኒ ቺካ ኑዋዱኬ የወንጀል ህግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር፣ በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን የኮኬይን እጽ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከብራዚል ሳኦወፖሎ ወደ በመነሳት ወደ ቦሌ አየር መንገደ ለትራዚተ ባረፈበት ወቅት በተደረገው ፍተሻ በያዘው የጉዞ ሻንጣ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀውን 5.2 ኪሎ ግራም እና በሆዱ ውስጥ ደግሞ 87 ጥቅል ፍሬ የሆነውን ኮኬይን የተባለውን እጽ ድብቆ በመያዝ ወደ ኢንጉ ከተማ ሊሄድ ሲል የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው መርዛማ እና አደገኛ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ተከሳሹ ማንነቱ ተረጋግጦ ክሱ ደርሶትና በችሎት ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የለኝም ባለቤቴ መንታ ልጁ ስለወለደች በቸግር ምክንያት ድርጊቱን ፈፀሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ በማለት ተናግራል፡፡ዐቃቤ ሕግን ተከሳሽ ድርጊቱን ባመነው መሰረት ሌላ ማስረጃ ማሰማት ሳያስፈል ጥፋተኛ ይባል ብሏል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ በተከሰሰበት አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ በመላት የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና በገንዘብ ችግር ምክንያት መሆኑን በማቅለያነት በመቀበል በ8 አመት ጽኑ እስራትና በ8000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

የተዘጋው መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተከፈተም‼️
በተቃውሞ ሳቢያ የተዘጋው የአዲስ አበባ፤ አዋሽ ጅቡቲ መንገድ ዛሬም ሙሉ በሙሉ #አልተከፈተም። ወደ #ጅቡቲ የሚያመራው እና የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ የደም ሥር እንደሆነ የሚነገርለት የመኪና መንገድ አዋሽ ሰባት ከተማ ላይ ዛሬም ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪ ለDW አረጋግጠዋል።
ተቃዋሚዎች ከትናንት ጀምሮ ዋናው መንገድ ከሚያልፍባት የአዋሽ ከተማ መውጪ እና መግቢያዎች እንደዘጉ መሆናቸውን የዐይን እማኙ ተናግረዋል።
በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዋሽ ነዋሪ "መንገዱ አልተከፈተም፤ ምንም የሚንቀሳቀስ ነገር የለም" ብለዋል።
በሎጊያ አካባቢ የሚገኘው የመንገዱ ክፍል ግን በዛሬው ዕለት ተከፍቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል። ትናንት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት መንገድ ላይ ማደራቸውን ለDW የገለጹት አሽከርካሪ ዛሬ ወደ ሎጊያ ከተማ ለመግባት መቻላቸውን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ላይ ስለመሆኑ መረጃ እንደደረሳቸው የገለጹት የከባድ መኪና አሽከርካሪ "ሕዝቡ ለሰባት ቀን ጊዜ ሰጥቶ አሁን መኪና መንቀሳቀስ ጀምሯል። በሰባት ቀናት ውስጥ ጥያቄያችን ካልተመለሰ #አሁንም_እንዘጋለን ብለዋል" ሲሉ ኹኔታውን አስረድተዋል።
በአዋሽ ሰባት የሚኖሩት ነጋዴ ግን የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ክፍኛ ያስተጓጎለው የመንገድ መዘጋት "እስከ ነገው ዕለት ይቀጥላል" የሚል መረጃ ደርሷቸዋል። "ሶስት ቀን እያሉ ነው። ነገንም ይጨምራል መሰለኝ" ያሉት የአዋሽ ሰባት ነዋሪ ከመንግሥት መፍትሔ ካልተገኘ ሊከፈት እንደማችል በተቃውሞው የተካፈሉ ሲዝቱ መስማታቸውን ለDW አረጋግጠዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ተጨማሪ ባንኮች ተዘረፉ‼️
በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ተጨማሪ ስድስት ባንኮች በታጣቂዎች በትላንትናው ዕለት መዘረፋቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለDW ገለጹ። ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በሁለት የወለጋ ዞኖች የተዘረፉት ባንኮች 17 መድረሱን የየአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ኃይሉ ዛሬ ለDW እንደተናገሩት በአካባቢያቸው ባሉ ስድስት የመንግስት እና የግል ባንኮች ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት እሁድ ከቀኑ አምስት ሰዓት ጀምሮ ነው። “በትላንትናው ዕለት የባንክ ዘረፋ የተካሄደው በሃዋ ገላን ወረዳ፣ እሮብ ገበያ ላይ፣ በአንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ [ላይ] ነው። እዚያው ወረዳ ላይ መቻራ የምትባል ከተማ ላይ አንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፈዋል። ከዚያ ደግሞ ሰዲ ጨንቃ ወረዳ ላይ በጨንቃ ከተማ አንድ የንግድ ባንክ፣ አንድ የኦሮሚያ የህብረት ስራ ባንክ ዝርፊያ ተካሂዶበታል” ብለዋል።
ተዘረፉ በተባሉት ባንኮች እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በታጣቂዎች መወሰዱን የገለጹት የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የየባንኮቹ ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል የሚል ስጋት እንዳለም አስረድተዋል። “ ካሸሪዎች [ገንዘብ ያዥዎች] እና ስራ አስኪያጆችን ይዘው ሄደዋል ነው የሚባለው። እንግዲህ ሰዎቹን ስላላገኘን እስካሁን ምን ያህል ገንዘብ ተወሰደ የሚለውን ማወቅ አልቻልንም። ግን ደግሞ ሰዎቹን ይዘው ሄደዋል የሚል መረጃ ነው ያለን” ሲሉ አብራርተዋል።
ታጣቂዎቹ ከባንክ ዘረፋ በተጨማሪ በሁለት ወረዳዎች ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤት ማውደማቸውን አቶ ታመነ ይናገራሉ። “በላሎ ክሌ የመንግስት መስሪያ ቤት አቃጥለዋል። በዋሃ ገላን፣ በየ ማለጊ ወረዳ ላይም የመንግስት መስሪያ ቤት የተቃጠለበት ሁኔታ ነው ያለው። እንግዲህ እነኚህ ወረዳዎች ሰራዊት የሌለበት ወረዳ ነው። ሰራዊት ከሌላ አጎራባች ቦታ እስኪደርስ ይሄን ጉዳት አድርሰው የታጠቁት ኃይሎች ከአካባቢው ተንቀሳቅሰዋል” ብለዋል።
ዘረፋ እና የንብረት ቃጠሎ በደረሳባቸው ቦታው ግጭት እንደሌለ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አሁን በቦታዎቹ ላይ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው ህዝቡን እየያረጋጉ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት በሄሊኮፕተር ታግዞ ጥቃት ፈጽሟል የሚባለውንም #አስተባብለዋል።
Via DW

ተከፍቷል‼️
ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስዳው መንገድ #ተከፍቷል። ተጨማሪ እየተከፈቱ የሚገኙ መንገዶችን መረጃዎች እንደደረሱኝ አሳውቃለሁ።
🔹የአፋር ክልል ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ። የተዘጉ መንገዶችም እንደሚከፋቱ በአፋር የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል።

መንገዱ ተከፍቷል‼️
ከትናንት ጠዋት ጀምሮ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ ጅቡቲ መንገድ እና የባቡር አገልግሎት ሥራ ጀመረ። ከ24 ሰዓታት በላይ ከአዋሽ አቅራቢያ ቆሞ የነበረው ባቡር ጉዞ ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑን ተሳፋሪዎች አረጋግጠዋል። በአፋር ክልል ገዋኔ አቅራቢያ የቆሙ በርካታ መኪኖች አሽከርካሪዎች መጓዝ እንደሚችሉ እንደተነገራቸው ለDW ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚገኘው የDW ዘጋቢ ወደ ጅቡቲ እንዲሁም ሐረር፣ ድሬዳዋ እና ጅጅጋ የሚያቀናው ዋና አውራ ጎዳና ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ገደማ መከፈቱን ታዝቧል። መንገዱ የተከፈተው ተቃውሞ ካስነሱ ወጣቶች ጋር በተደረገ ድርድር መሆኑን የDW ዘጋቢ ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ተናግሯል።
ከአዲስ አበባ መንገደኞች አሳፍሮ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ ባቡር በአፋር ክልል ተቃውሞ ሳቢያ ከ24 ሰዓታት በላይ ለመቆም ተገዶ ነበር። ተቃውሞው ከመሐል ኢትዮጵያ ወደ ምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እንዲሁም ወደ ጅቡቲ የሚደረጉ ጉዞዎችን አስተጓጉሎ ቆይቷል።
ትናንት ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ ከአዲስ አበባ የተነሳ ባቡር አዋሽ አካባቢ ሲደርስ መንገድ በዘጉ ተቃዋሚዎች እንዲቆም የተገደደው አዋሽ አካባቢ መሆኑን በባቡሩ ላይ የሚገኙ መንገደኛ ለDW አስረድተዋል። "ትናንትና ቀን ስድስት ሰዓት ገደማ ነው የቆመው። እስካሁን ድረስ ከቦታው አልተንቀሳቀስንም። እዚያው ነን ያለንው። ወደ ኋላ እንድንመለስ ጠይቀናቸው ነበር። እኛ መንግሥትን የጠየቅንው ጥያቄ እስኪመለስልን ድረስ ወደ ኋላም መመለስ አትችሉም ወደ ፊትም አትሔዱም ተብለናል" ሲሉ እኚሁ መንገደኛ ተናግረዋል።
መንገድ ከዘጉ ተቃዋሚዎች መካከል አንዱ ወደ ባቡሩ በመግባት "የእኛ ጥያቄ የእናንተም ጥያቄ ነው። አርፋችሁ ተቀመጡ። መልስ እስኪሰጠን ድረስ እዚሁ ነው የምትሆኑት" የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አንድ መንገደኛ ተናግረዋል። ባቡሩ በዛሬው ዕለት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት 30 ድረስ ቆሞ እንደነበር DW አረጋግጧል።
መንገደኛው እንዳሉት ከአዲስ አበባ የተነሳው ባቡር አምስት ፎርጎዎች አሉት። የባቡሩ አንድ ፉርጎ 100 ገደማ መንገደኞች የመጫን አቅም አለው። አዋሽ አካባቢ ቆሞ በነበረው ባቡር በእያንዳንዱ ፉርጎ ከ50 እስከ 60 የሚደርሱ መንገደኞች እንደነበሩ DW ለመረዳት ችሏል። በባቡሩ ውስጥ ለሚገኙ መንገደኞች የአካባቢው ሰዎች እና ተቃዋሚዎች ምግብ እና ውሐ ሲያቀርቡ እንደነበር መንገደኞች ተናግረዋል።

ሰላማዊ ነበር‼️
መንግስት ለጥያቄዎቻችን ትኩረት ይስጥ በሚል በአፋል ክልል ከትላንት አንስቶ መንገዶችን በመዝጋት ህዝቡ ተቃውሞ ሲያሰማ ነበር። በዚህ ፍፁም ሰላማዊ የነበረው ተቃውሞ የትኛውም ሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም፤ ንብረትም አልተዘረፈም። ይልቁንም መንገዶች ተዘግተው መንገደኞች በቆሙባቻው ቦታዎች የየአካባቢው ህብረተሰው ውሃ እና ቆሎ ሲያቀርብ ነበር።
©Abdi(TIKVAH-ETH)

”ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ስልጣኔዋ ለመመለስ ለሰላም ዘብ መቆም አለበት”-ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ
.
.
.
ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ስልጣኔዋ ለመመለስ ታሪኩን አውቆ #ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለበት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ገለጹ፡፡
“የአስተሳሰብ አብሮነት መልካም ነገርን ለማየት” በሚል መሪ ቃል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ከታዋቂው ደራሲና ገጣሚ ጋር ተወያይተዋል።
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ወጣቱ የአገሩን የቀደመ ታሪክ ማወቅና ለአብሮነትና አንድነት የሚጠቅሙ እሴቶችን እንዲያጠናክር አስገንዝበዋል፡፡
የተጀመረው አራዊ የለውጥ ጉዞ ውጤታማ የሚሆነው ወጣቱ በሰከነ መንገድ የአገሩን ሰላም ሲጠብቅና ሲያከብር ነው ብለዋል፡፡
በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና አለመግባባቶች የግለሰቦች የጥቅም ግጭት እንጂ ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች መገለጫዎች አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የተረጋጋ ሰላም እንዲኖርና የኢትዮጵያውያን አንድነት በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲጸና ወጣቶች በአስተውሎ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም ፕሮፌሰር ፍቅሬ# አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update ሜጀር ጀነራል #ክንፈን ጨምሮ 14 ግለሰቦች በመንግስትና ህዝብ ላይ ከ544 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ #የሙስና_ወንጀል ተከሰሱ።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ሜጀር-ጀነራል-ክንፈን-ጨምሮ-14-ግለሰቦች-በመንግስትና-ህዝብ-ላይ-ከ544-ሚሊየን-ብር-በላይ-ጉዳት-እንዲደርስ-በማድረግ-የሙስና-ወንጀል-ተከሰሱ-01-14

Telegraph
ሜጀር ጀነራል ክንፈን ጨምሮ 14 ግለሰቦች በመንግስትና ህዝብ ላይ ከ544 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ
ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 የሜቴክ የቀድሞ ሰራተኞች በመንግስትና ህዝብ ላይ ከ544 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው 1ኛ ተከሳሽ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ገብረሥላሴ፣ 2ኛ ኮሎኔል በርሄ ወልደሚካኤል ገብሩ (ያልተያዘ)፣ 3ኛ ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤል ገብረእግዚአብሄር፣ 4ኛ ብርጋዴር…
ለለውጥ እንነሳ‼️
መጠላላቱን፣ በብሄር በዘር መከፋፈሉን፣ መሠዳደቡን፣ መተነኳኮሉን፣ እርስ በእርስ ለመጠፋፋት መሮጡን፣ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መሽቀዳደሙን ትተን ይህ እጅግ #አሳፋሪ እና #አስነዋሪ በዓለም ደረጃ አንገት የሚያስደፋንን ታሪክ ለመቀየር 24 ሰዓት እንስራ‼️
Half of the world's poor live in these 5 countries:
🔹India
🔹Nigeria
🔹Democratic Republic of Congo
🔹Ethiopia(#ኢትዮጵያ)
🔹Bangladesh
https://wrld.bg/Oeak30nhefz

World Bank Blogs
Half of the world’s poor live in just 5 countries
Of the world’s 736 million extreme poor in 2015, 368 million lived in just 5 countries. The 5 countries with the highest number of extreme poor are: India, Nigeria, Democratic Republic of Congo, Ethiopia, and Bangladesh.
#ሼር ከላይ ያለውን መረጃ ሁሉም የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል በፌስቡክ ገፁ ላይ እንዲለጥፈው በታላቅ ትህትና እለምናለሁ👆
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቤ ከቤ" ~ የሚስጥር ስም‼️
በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች የነበሩ ግለሰቦች #የሚስጥር ስም፣ ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡
https://telegra.ph/በሰብዓዊ-መብት-ጥሰት-ተጠርጥረው-የታሰሩ-የደኅንነት-ሠራተኞች-የሚስጥር-ስም-አቤ-ከቤ-እንደነበር-ተገለጸ-01-14

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የታሰሩ የደኅንነት ሠራተኞች የሚስጥር ስም ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ተገለጸ
በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች የነበሩ ግለሰቦች የሚስጥር ስም፣ ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 943/2008 ድንጋጌ ሥልጣን እንደተሰጠው በመግለጽና በችሎት ተገኝቶ እንደ መርማሪ ፖሊስ ሆኖ መከራከር እንደሚችል አመልክቶ በፍርድ ቤቱ…