TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቆማ‼️

"በአፋር ሚሌ ኣካባቢ ነው ያለ ነዉ መንገዶቹ እስካሁን ዝግ ናቸዉ። የሚመለከተዉ ኣካል ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ካልፈለገ ብዙ ህፃናት እና ኣዛዉንቶች በረሃብ መጎሳቆላቸዉ ነዉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ #ሰላምና #መረጋጋት ለማምጣት የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ እየተወጡ #አለመሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሀና እንዳሉት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ለውጥ ለማምጣት ህዝቡ ተቃውሞዎች ሲያደርግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተሳታፊዎች ነበሩ፤ ለውጡ ከመጣ በኋላም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መንግሥትና የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሁከቶቹ ተበራክተዋል ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩትን የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጠና ቡድን ማዋቀሩን በመጥቀስ፤ በቀጣይ ለሚሠራቸው ሥራዎች አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡንም ገልጸዋል፡፡ ሰላም ከሌለ ልማትና የመኖር ነፃነት ስለማይኖር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላማዊ ሰልፍ-አፋር🔝

በአሁን ሰዓት በአዋሽ አካባቢ የአካባቢው ወጣቶች #ሰላማዊ_ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ነው።

ምንጭ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ #ዝናሽ_ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ በ20 ሚሊን ብር የሚገነባ የ2ኛ ደ/ት ቤት መሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ‼️

የአፋር ክልል ነዋሪዎች #በሰመራ_ከተማ ከመንግስት ሀላፊዎች ጋር በጥያቄዎቻቸው ዙሪያ በመወያየት ላይ ይገኛሉ።

ፎቶ፦ ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋር‼️

መንገድ ተዘግቶባቸው በአንዳንድ አካባቢዎች ለቆሙ መንገደኞች የአካባቢው ህዝብ ውሃ እና ቆሎ እያቀረበ ይገኛል። በመንገደኞች ደህንነት ላይ ምንም ጉዳት ባይደርስም አስተያየታቸው ለTIKVAH-ETH የላኩ የቤተሰባችን አባላት እንዳሉት በቂ ምግብ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ህፃናት እና አዛውንቶች እየተቸገሩ ይገኛሉ። መንግስት ህዝቡን አወያይቶ መፍትሄ እንዲፈልግም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ🔝

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች ተቋሙ እጅጉን #እየበደለን እና #እያሰቃየን በመሆኑ ግቢውን ለቀን ለመውጣት ተገደናል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #የመኪና_አደጋ አልደረሰባቸውም” አቶ አሰማኸኝ አስረስ
.
.
.
በማህበራዊ ሚዲያ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ #አሰማኸኝ_አስረስ ተናገሩ።

በምዕራብ ጎንደር ገንዳ ውሃ ከተማ ሰሞኑን በተከሰተው ግጭት ዙሪያ ትናንት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ያደረጉት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ባህር ዳር ሲመለሱ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸውና የሾፌራቸውም ህይወት እንዳለፈ በእርሳቸው ላይም ጉዳት እንደደረሰ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ትክክለኛ አለመሆኑን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ወደ ገደውሃ ሲሄዱም ሆነ ወደ ባህር ዳር ሲመለሱ በሄሌኮፍተር እንደተጓዙ አስታውሰው በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ #ከእውነት_የራቀ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ገዱ በተከሰተው ግጭት ዙሪያ ከገንዳ ውሀ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገው መመለሳቸውን አቶ አሰማኸኝ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋሽ 7🔝መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት በአዋሽ 7 ለቆሙ የባቡር ተጓዥ ዜጎች የአካባቢው ነዋሪ ምግብ እና ውሃ እያቀረበ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገሪቱ #አንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ #ግጭቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህንን ሚናቸውን እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩና #ተቀባይነታቸውም በመቀነሱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አለመሆኑን ባሙያዎች ተናግረዋል።

ሙሉውን አንብቡት...
https://telegra.ph/የሐይማኖት-አባቶችና-የአገር-ሽማግሌዎች-ሰላም-የመፍጠር-ሚና-ኮስሷል-01-14
ምክትል ጠሚ አቶ ደመቀ‼️

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ሀበሻ ለፍቅር በሚል ማህበር የታቀፉት የኮሚኒቲ አባለቱ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲያስፖራውን ተሳትፎ፣ በኢትየጵያ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ እና በሌሎች ጉዳዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የኮሚነቲ አባለቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብለሹ አሰራር ለመከለከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ሊተገበር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

"በያዝናቸው የለውጥ መንገዶች የለውጡ አንዱ ትልቅ ደጋፊና አጋር ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው በውጪ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው" ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስር ደመቀ መኮነን የለውጡ ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ በ43 ሚሊየን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎች እየተገጠሙ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ከቀይሽብር ሰማዕታት እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አደባባይ ቁጥራቸው 140 የሆኑ የደንህነት ካሜራዎች መገጠማቸውን ተናግረዋል። ይህም የመጀመሪያው ዙር የከተማዋ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው 90 በመቶ መጠናቀቁን ያሳያል ብለዋል። የመግጠም ስራው ተጠናቆ የሙከራ ስራ ላይ ይገኛሉ የተባሉት ካሜራዎችም በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አገልገሎት የሚጀምሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም ለፌደራል ፖሊስ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በመስጠት በከተማዋ የሚስተዋለውን የደህንነት ችግር ለማስወገድ ይረዳል ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በስፔን ቫሌንሽያ በተደረገው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ፀሓይ ገመቹ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን የኢትዮጵያ ርከርድ አሻሽላለች፡፡ ፀሓይ ገመቹ 30 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባትና በጥሩነሽ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በ15 ሰከንድ በማሻሻል ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
"በምዕራብ ወለጋ 10 ባንኮች ተዘርፈዋል"- የዞኑ አስተዳዳሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን 10 ባንኮች በታጣቂዎች መዘረፋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ለDW ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በዞኑ የአራት ወረዳዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና በሌሎቹ ወረዳዎች #ዝርፊያ መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን ለDW እንደተናገሩት በመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት 10 ሰዓት ገደማ ነው። አስተዳዳሪው የታጠቁ ባሏቸው ኃይሎች ተፈጸመ ያሉት ዝርፊያ የተከናወነው በተመሳሳይ ሰዓት መሆኑንም ገልጸዋል።

“የታጠቀው ኃይል እዚህ አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እና በደረሰን መረጃ መሰረት 10 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል ባንኮች ተዘርፈዋል” ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ። ከተዘረፉት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ እንዲሁም የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ባንክ እንደሚገኙበት አስረድተዋል። በባንኮቹ ዝርፊያ የተወሰደው ገንዘብ መጠኑ ግን እስካሁን አለመታወቁን ጨምረው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia