TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#uodate የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን 7ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ጉለሌ በሚገኘው መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል፡፡

በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ቦርድ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊን አጭር የህይወት ታሪክ አቅርበዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ዓለም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ መመራት እንዳለባት ያደረጉት ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀርቧል፡፡

አቶ መለስ በዚህ ንግግራቸው ያደጉ አገራት ለምድሪቱ ስጋት የጋረጠውን የዓለም ሙቀት መጠን መጨመርን እንደ አፍሪካ ካሉ ታዳጊ አገራት ጋር በመሆን እንዲዋጉ ጠይቀው ነበር፡፡

በመቐለ ከተማም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ 7ኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

Via #ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#uodate በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጽሐፍትን በማሰባሰብ ለአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለገሱ፡፡ ወጣቶቹ ከአዲስ አበባ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር በሆስፒታሉ ኑ! መደርደሪያዉን እንሙላ በሚል መሪቃል መጽሐፍ የማሰባሰብ ፕሮግራም አከናውነዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#uodate ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ ሲደረጉ በነበሩና በአዳዲስ ድጋፎች ዙሪያ መክረዋል።

በአሁኑ ወቅት በኤግዚም ባንክ ድጋፍ ከ600 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 300 ሚሊዮን ዶላሩ በ2011-2012 በኮርያ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ ማእቀፍ ስር የተፈረመ ነው።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia