TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቀደለት።

ቀሲስ በላይ መኮንን በሃሰተኛ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

በተጠረጠሩበት ወንጀል ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ከእሳቸው ጋር ሌሎች 2 ግለሰቦች ያሬድ ፍስሃ እና ጣባ ገናና የተባሉ ቀርበዋል።

ከዚህ ቀደም ለፌዴራል መርማሪ ፖሊስ 7 ቀን መሰጠቱ ይታወሳል።

በዚህ ጊዜ መርማሪ ፖሊስ ምን እንደሰራ ለችሎቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ምን አለ ?

- " የምስክሮችን ቃል ተቀብያለሁ። "
- " በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም ጠይቂያለሁ። "
- " የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሰጠኝ ጠይቂያለሁ። "
- " ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው የሚገኙ ሂሳቦችን ለማጣራት ማረጋገጫ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " በወቅቱ የነበረ የካሜራ ቅጂ ጠይቂያለሁ። "
- " ለወንጀል ተግባር የዋለ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ተቋም ጠይቂየለሁ። "
- " በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ አድርጌ በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራሁ ነው። " ... ብሏል።

የቀሩ ስራዎች ፦
- " ከተለያዩ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ። "
- " ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል። "
- " ግብረአበሮችን ተከታትሎ መያዝ። "
- " ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ተግባሮች ላይ የማጣራት ስራ መስራት ሌላም ሰፊ የምርመራ ስራ ስለሚያስፈልግ ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ " ብሏል።

የተፈጸመው ድርጊት " ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ጥላሸት የሚቀባ ተግባር ነው " ብሏል።

ተጠርጣሪው ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ነው የቀረቡት።

ጠበቆቻቸው ምን አሉ ?

° " የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ደንበኞቻችን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም " ብለዋል።

° " ቀሲስ በላይ የተገኘው የጦር መሳሪያ ህጋዊ ነው። ሀብት ማፍራት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ሊገናኝ አይገባም " ብለዋል።

° " የሃይማኖት አባት መሆናቸው ፣ የልማት ስራ አስተባባሪ በመሆናቸው ፣ ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ ቢወጡ ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ማስረጃዎችን የማጥፋት አቅም የላቸውም " ብለዋል።

ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን ምን አሉ ?

ወንጀል አለመፈጸማቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር እንዲሁም ፖሊስ ተባባሪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

➡️ " ምሽት ላይ #እቤቴ_እየሄድኩ ጠዋት ላይ ልምጣላችሁ " በማለት ፖሊስን መጠየቃቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

ከእሳቸው ጋር አብረው የታሰሩት #ሹፌራቸው እና #አጃቢያቸው እንደሆኑ ገልጸው ምንም የወንጀል ተሳትፎ በሌለበት ሁኔታ ከኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ በእስር ማቆየት ተገቢ አይደለም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በማለት የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ ፥ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (#ኤፍቢሲ) መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia