TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፍርድ ቤት ውሎ⬇️

በሃገር ኢኮኖሚ ላይ #አሻጥር በመስራት እና በኢኮኖሚ ላይ #ጫና ማሣደር ወንጀል ተሣትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የነበሩ 9 የሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ሰራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት በአቀረበው የምርመራ መዝገብ ተጠርጣሪዎች በቡድን በመደራጀት መንግሥትና ህዝብን ለማለያየት ተንቀሣቅሰዋል የሚለውን ጠቅሷል፡፡

ወርሀዊ ደሞዛቸው በአስር እጥፍ እንዲያድግና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች አልተከበሩልንም በማለት ከነሐሴ 21 ጀምሮ የሥራ ማቆም #አድማ ማድረጋቸውንም ፖሊስ ጠቅሷል፡፡

ለዚህም እንዲረዳቸው የሌሎች ሰራተኞችን ፊርማ በማስመሰል መፈረም እና ስራ እንዲያቆሙ አነሣስተዋል በሚል #ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር እንዲውሉ ካደረጓቸው ምክንያቶች ይጠቀሣል የሚለውንም የምርመራ ቡድኑ በመዝገቡ አካቷል፡፡

ቡድኑ ሌሎች የምርመራ ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የመብት ጥያቄዎችን ማንሣታቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲያከብርላቸው አመልክተዋል፡፡

ግራቀኙን የተመለከተው ችሎት ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን በመፍቀድ ለመስከረም 2 /2ዐ11 #ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ፌክ ኒውሶች ናቸው!"

አቶ አዲሱ አረጋ ከላይ በምትመለከቱት #የዋዜማ_ሬድዮ ሪፖርት ላይ ክልሉ ምን ይላል ተብለው በጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ፦

"እነዚህ ህዝብ መሀል #ጥርጣሬ ለመፍጠር የሚሰራጩ #ፌክ_ኒውሶች ናቸው። እንግዲህ ጠ/ሚሩ #ኦሮሞ ነው፣ ከንቲባውም ኦሮሞ ነው በማለት ከተማዋን በኦሮሞ #ለማስወረር ነው በሚል ኦሮሞን ስግብግብ አድርጎ ለመሳል ነው። እኛ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን ዜጎቻችንን የማስፈር ስራ #ጨርሰናል። እኛ #በወረራ አዲስ አበባ ላይ ያለንን ጥያቄ እናሳካለን የሚል አቋም የለንም። ስንጠላው እና ስንታገለው የነበረውን አይነት #አሻጥር የመስራት ፍላጎቱም አእምሮውም የለንም።"

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia