TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ⬇️

በሀዋሳ ከተማ ስጋት ለመፍጠር ሙከራዎች እየተደረጉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ አከባቢውን #በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በከተማዋ ከሰሞኑ የተፈጠረውን የፀጥታ ስጋት ችግር ለመቅረፍ የከተው የፀጥታ አካላት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ አክሎ ገልጿል።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በሰጡት መግለጫ፥ በሀዋሳ ከተማ ማንነታቸውና አላማቸው ያልታወቁ አካላት የከተማውን ነዋሪ ላይ #ስጋት ለመፍጠር ያልተጨበጠ የስነ-ልቦና ጦርነት ከፍተዋል ብለዋል።

ባለፉት 3 ቀናትም ምሽትን ተገን በማድረግ የተለያዩ ቀለማትን በግለሰቦች በር እና አጥሮች ላይ በመቀባት ነዋሪው ላይ ጥርጣሬን መፍጠሩን ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ተናግረዋል።

ተግባሩም ለውጡን በማደናቀፍ የህዝቦችን በአንድነት የመኖር እሴት ለማፍረስ ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አረጋግጧል ብለዋል።

ቀለም የሚቀቡትን አካላት ፖሊስ #በቁጥጥር ስር ለማዋል ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ ምንም የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ግን የጸጥታው መዋቅር አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንዳለም ነው የገለጹት።

የተቀቡት ቀለሞች ግን ሁሉም ቤቶች ላይ በመደረጉ #ብሄር ተኮር ባለመሆናቸው ህብረተሰቡ በዚህ ሆነ ተብሎ የከተማውን ሰላም ለማወክና በቀጣይ የሚካሄደውን የደኢህዴን ጉባኤ ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረትን ሊያወግዝና ሊያጋልጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብን🔝

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በቅርቡ በሚካሄደው የህዝብና የቤት ቆጠራ ላይ ስጋት እንዳለው ገለጸ። የፊታችን መጋቢት በሚካሄደው አገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነጻ መሆን መቻል አለበት ሲል አብን የገለጸው መጪውን የህዝብና ቤት ቆጠራ አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር #ደሳለኝ እንዳሉት በመጪው መጋቢት 29/2011 የሚካሄደው 4ኛው ዙር አገር አቀፍ የህዝብና የቤት ቆጠራ በትክክል እንዲካሄድ ህዝቡ #በንቃት መሳተፍና #ውጤቱንም መከታተል እንዳለበት ገልጸዋል።

ዶክተር #ሲሳይ_ምስጋናው በጎንደር ዩኒቨርሰቲ የስነ ህዝብ መምህር እንዳሉት ከዚህ በፊት የተደረጉ ቆጠራዎች በርካታ ችግሮች እንደተስተዋሉባቸው በውይይቱ ላይ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ የህዝብና የቤት ቆጠራ የተስተዋሉ ህጸጾች በቀጣዩ ቆጠራ ወቅት እንዳይደገሙ ምሁራን ህዝቡን ማንቃት እዳለባቸው እንዲሁም የአማራ ህዝብም ሁኔታዎችን በንቃት መከታተል እንዳለበት ሊቀመንበሩ አሳስበዋል።

የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ #ውብሸት_ሙላት የህዝብና የቤት ቆጠራ ከህግ ማዕቀፍ በሚል ርዕስ የሌሎችን አገሮች ተሞክሮ በማጣቀስ በአገራችን የሚደረግ ቆጠራ በገለልተኛ አካል መካሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ከወሊሶ_ቤተሰቦች

"በወሊሶ ከተማ በነገው ዕለት የሀምሌ 22/2011 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራን የማስቀመጥ ቀንን በማስመልከት በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች #ከ50 ሺህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉና ህብረተሰቡም #በንቃት እንዲሳተፍ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን እያስተላለፈ ይገኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013 #ኢትዮጵያ

እጅግ የተከበራችሁ የTikvah Ethiopia ቤተሰብ አባላት በሙሉ ነገ ሀገራችን ከምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር በተያያዘ መልዕክታችሁን በእነዚህ አድራሻዎች አስቀምጡ ፦

- በቴሌግራም Bot : @tikvahethiopiaBOT
- በድረገፅ www.tikvahethiopia.net
- በትዊተር በመልዕክት መቀበያ twitter.com/tikvahethiopia?s=09
- በኢሜል [email protected]
- SMS : +251919743630

ውድ አባላት በምርጫው ወቅት ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን ደንቦች፣ ህጎች እና መመሪያዎች አክብራችሁ ሰላማዊ የሆነ ምርጫ ሂደት ይኖር ዘንድ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እንላለን።

እያንዳንዱን የምርጫ ሂደት #በንቃት እንድትከታተሉ ይሁን።

@tikvahethiopia