TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ለማስተላለፍ ታስቧል፡፡

በመዲናዋ የመሬት፣ የቀበሌ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ሕንፃዎችን የኦዲት ስራም ተጀምሯል፡፡

ምክትል ክንቲባ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የቆጠራ ስራውን #ለማወክ ጥረት የሚያደርጉ መኖራቸውን አስታውሰው ሕብረተሰቡ በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬትና ቤቶችን ጥቆማ ካለው ለአስተዳደሩ ያድርስ ብለዋል፡፡

የመዲናዋን ሰላም #ለማደፍረስ ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን ምልክቶች መታየታቸውንና ህብረተሰቡ በንቃት ከአስተዳደሩ ጋር እንዲቆም
ጥሪ አቅርበዋል፡፡

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ⬇️

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የሰው ህይውት #አልፏል ተብሎ በድብቅ /በሽፋን/ በተከፈቱ በውስን ማኅበራዊ ሚዲያዎች (በTwitter እና Facebook) እየተገለፀ ያለው መረጃ የሃሰት እና ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን #እናረጋግጣልን

በመቐለ ከተማም ሆነ በዩኒቨርስቲያችን በተማሪ ላይ ምንም አይነት ጥቃት እና አደጋ ያልደረሰ መሆኑን በድጋሜ እናረጋግጣልን።

ባደረግነው ማጣረት የውሸት መረጃዎቹ እየተሰረጩ ያሉት በድብቅ /በሽፈን/ በተከፈቱ ውስን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሆን፣ በአገረችን የተጀመረውን ሰላማዊ የመማር እና ማስተማር ሂደት #ለማወክ
/ለማበላሸት/ ዓላማ ያደረገ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ ባደረግነው ዳሰሳ በትግረይ ክልል በሚገኙ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ የመማር ማስተማር ኢደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደቀጠለ ነው።

እነዚህን የውሸት መረጃዎች በጋራ በመከላከል እና ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ በመስጠት እና በማሰረጨት ሃላፊነታችንን እንወጣ።

ይህን መልዕክት Share በማድረግ ለሌሎች እናስተላልፍ!
፨፨፨
The safety of our students and providing quality academic service are utmost priority of our university. We Really Care!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 25/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

መንግስት በቅርቡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ላነሳቻቸው ጥያቄዎች ከፍተኛ ትኩረትና አፅንዖት በመስጠት ከአስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በሰላማዊ መንገድ በፌደራልና በክልል አውንታዊ ምላሽ መስጠት ጀምሯል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት ጉዳዩ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ባለበት በዚህ ወቅት የቤተ-ክርስቲያን ጥያቄን ሽፋን በማድረግ አንዳንድ አካላት ጥያቄውን መስመር በማሳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማሳሳትና የእምነቱ ወግና ስርዓት ከሚፈቅደው ውጪ ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ ለማስኬድ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳለ ፖሊስ ደርሶበታል፡፡

በተጨማሪም የሃገራችን ወጣቶች የደመራ በዓል ለማክበር በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ ምዕመናኑ ሲሄዱ በሰላም ወደ ክብረ በዓሉ እንዲደርሱና የደመራ በዓሉ በሰላምና በደስታ እንዲያከብሩና አምላካቸውን የሚያመሰግኑበትን ተግባራት ሲፈፅሙ የሚታወቁበት እንጂ የተለያዩ አጀንዳዎች የሚያሰሙበት እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባገኘው መረጃ መሰረት በዓሉ በሰላም እንዳይጠናቀቅ የተለያዩ የግል አጀንዳዎችን አንግበው የበዓሉን ስነ-ስርዓት #ለማወክ የተዘጋጁ ሃይሎች እንዳሉ ደርሶበታል፡፡

በዚሁ መሰረት ከበዓሉ ስነ-ስርዓት ውጪ፣ ግጭት ቀስቃሽ ፅሁፎች፣ አንዱን የሚያሞግስ ሌላውን የሚያንቆሽሽ ፅሁፍ፣ ብዙሀነታችንን የማይገልፁ ፅሁፎች በማንኛውም መንገድ ይዞ መገኘት ፣ በህገ መንግስቱ ከተፈቀደው ሰንደቅ ዓላማ ውጪ እና የተለያዩ አርማዎችን ይዞ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ መምጣት የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስታውቃል።

ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

@tsegabwolde @tikvahethiopia