TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ • " ከ13,000 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው " - የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት • " በሰሃላ ወረዳ 94 በመቶ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች፣ 45 በመቶ ከአምስት ዓመት በታች ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል " - የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በአበርገሌና…
#አማራ #ዋግኽምራ

" ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ 9 አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። … የህፃናትና የእናቶች የህክምና አገልግሎት አደጋ ውስጥ ነው " - የዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ

ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ፦
* የመድኃኒት፣
* የትራንስፖርት፣
* የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ በዞኑ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ፈተና እንደሆነባቸው በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ምን አሉ ?

- ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ ዘጠኝ አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። በሰርቪስ፣ በሥራ ጫና ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። 

- በተፈለገና ባለቀ ሰዓት ወቅቱን ጠብቆ መድኃኒት ለመግዛት እንቅስቃሴዎች ገድበውናል። የሴኩሪቲ ችግር በጣም አሳሳቢ ነው። ሪፈራሎች በሚፈለገው መልኩ እየተንቀሳቀሱ አይደለም። ስለዚህ በእናቶችና በህፃናት የጤና አገልግሎት ጠቅላላ አደጋ ውስጥ ነው። 

- ሰውከፍሎ መታከም አልቻለም። የጤና መድህን ሽፋናችን ዝቅተኛ ነው። ራሳቸውን ሰርቫይብ ማድረግ ያልቻሉ፣ ለመከላከያ፣ ለልዩ ኃይል ለሌሎች ቁስለኞች ሁሉ ጠቅላላ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የጤና ተቋማት ናቸው ያሉት። እየጠፉ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ግን ደግሞ በትግል እንደምንም እየተቋቋምን ማኅበረሰቡን ለማዳረስ እየሞከርን ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጸጥታው ችግር በድርቅ ለተጎዱት ምን ጉዳት አስከተለ ? ሲል ጠይቋል።

° ይህ ሁኔታ በተለይ በዞኑ በድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እያሳደረው ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው።

* ኮሌራ ተከስቶብናል። እንደ ጤና ተቋማት ትልቅ ሥጋት፣ ከባድ ወረርሽኝ ላይ ነው ያለነው። ቁጥር አንድ ተጋላጭ የሚባሉት ህፃናት፣ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ናቸው። 

° ከኅዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የልየታ ሥራ በሁሉም ወረዳዎች አሰርተን ነበር። በዚያ መሠረት አስደንጋጭ ቁጥር ነው ያገኘነው። ከለየናቸው ነፍሰጡር፣ አጥቢ እናቶች 81 በመቶ የሚሆኑት አጣዳፊ መካከለኛ የምግብ እጥረት ያለባቸው ናቸው።

° እንደ ዞን ከለየናቸው ህፃናት 45 በመቶዎቹ አጣዳፊ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸው ናቸው። ይህ ቁጥር ከተቀመጠው ስታንዳርድ በላይና አስደንጋጭ ነው። አስደንጋጭ ከመሆኑም በላይ አሁን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በጣም ዘገምተኛ ናቸው ብለዋል።

የዋግኽምራ ብሄረሰብ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፦
☑️ 95 በመቶ እናቶች በምግብ እንደተጎዱ፣
☑️ የህፃናት የረሃብ መጠን 15 በመቶ ከደረሰ እንኳ ከስታንዳርድ በላይ እንደሆነ ነገር ግን ከ30 በመቶ በላይ ህፃናት በምግብ እጥረት እንደተጎዱ ገልጾ ነበር።

አሁን የጤና መምሪያ ኃላፊው በገለጹት መሠረት ደግሞ የህፃናቱ የምግብ እጥረት ጉዳት ወደ 45 በመቶ ከፍ ብሏል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ፤ በተለይ የጸጥታው ችግር ከድርቁ ጋር ተያይዞ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተና መሆኑን፣ ድርቅ፣ ጦርነት፣ ወረርሽኝ በዞኑ መደራረባቸውን ገልጾ እስካሁን ድጋፍ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው፣ አሁንም መንግሥት፣ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ከችግሩ ውስብስብነት አንፃር ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተረድተው #እርዳታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናክሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia