TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ⬆️

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የቅበላ ኮሚቴዉ አስታወቀ፡፡

ለአቀባበሉ የተዋቀረዉ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ አቀባበል ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብሏል፡፡

ታማኝ በየነ በኪነ ጥበቡ ዙሪያ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማነቃቃት፣ የመድረክ ፈርጥ ሆኖ ሌሎች ተከታዮቹን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡

ለረጅም ዓመታት #አንድነትን#ፍቅርን#መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን በተሰጠዉ መግለጫ ተገልጿል፡፡

ይህ ኢትዮጵያዊ #ጀግና ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ብለዋል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ ዕለት ተገኝተዉ በፍቅር እጃቸዉን ዘርግተዉ እንዲቀበሉት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ👆

/ሚያዚያ 23/

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ረቡዕ ምሽት #የTIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት ሲገቡ በተቋሙ ተማሪዎች እና በተማሪዎች ህብረት ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በፍቅር ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል!! እራታቸውን እጉርሰው ማደሪያቸውን አመቻችተው ወንድምና እህቶቻቸውን በክብር አስተናግደዋቸዋል።

√ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር ቀደም ብለን በተነጋገርነው መሰረት #የStopHateSpeech መድረክን ያካተተ ሌላ ትልቅ መድረክ እያዘጋጁ ስለነበር የውይይት መድረኮች ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ ሆኗል። ዩኒቨርሲቲውም በራሱ ፕሮግራም በትልቅ ዝግጅት ሊጠራ ስላሰበ የታቀዱ ስራዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።

እውነት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይለያሉ! #ፍቅርን#መተሳሰብን#አንድነትን ያሳዩን የቤተሰባችን አካል ናቸው። #ክብር ይገባችኃል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia