TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃትን በመሩ፣ ባቀነባበሩና የፋይናንስ ድጋፍ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ #አጠናቋል። በዚህም መሰረት ጥቃቱን በማቀነባበር፣ በመምራትና በፋይናንስ በመደገፍ የተሳተፉ ግለሰቦች ማንነትና የምርመራ #ውጤቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በሚቀጥለው ሳምንት #መግለጫ እንደሚሰጥ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ #ብርሃኑ_ጸጋዬ ተናግረዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት‼️

የሰኔ 16ቱን የቦንብ ጥቃት በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ #ብርሃኑ_ጸጋዬ የተናገሩት፦

• የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በብሄራዊ መረጃ ደህንነት ኃላፊ የተቀነባበረ ወንጀል ነው፡፡

• ወንጀሉን የፈፀሙት በብሔር ሲታዩ #ኦሮሞ ናቸው፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮሞ በመሆናቸው የኦሮሞ ህዝብ እራሱ እንዳልተቀበላቸው #ለማስመሰል የተደረገ ወንጀል ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ እየተስፋፋ ከመጣው ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ ሰፊ ጥናት እያደረገ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገልጧል፡፡ ጦር መሳሪያዎቹ የሚመጡባቸው እና የሚመረቱባቸው ሀገሮች ያሉ ሲሆን ባብዛኛው ከሱዳን እንደሚመጡ እና ቱርክ ሰራሽ መሆናቸውንም አቃቤ ሕግ #ብርሃኑ_ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡ ወንጀሉን ለመከላከል በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል ከሀገራቱ ጋር ለመነጋገር ዕቅድ ተይዟል፡፡ በወንጀሉ ምርመራቸው ተጠናቆ ለፍርድ ቤት ሊቀርቡ የተዘጋጁ መዝገቦች አሉ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia