TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «ከጥር 1 - ጥር 21 : የሰለም፣ የፍቅር እና የአንድነት ሳምንታት-#TIKVAH_ETHIOPIA @tsegabwolde @tikvahethiopia»
#Update በሰሜንና በምዕራብ ጎንደር ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ ከ500 በላይ ታጣቂዎች ከመንግስት ጋር #ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ዛሬ ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።

በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያን ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ለማስተዋወቅ ያለመ የኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲ ቀን ተከብሮ ውሏል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀኑ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነን ጨምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ አፍሪካ ሀገሮች አምባሳደሮች ተገኝተዋል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀንን በማስመልከትም የእንጦጦ ቤተ መንግስትና ሙዚየም፣ የአዲስ አበባ ቱሪስት መዳረሻ ፓርክ እና ያያ ቪሌጅ ጉብኝት ተደርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጥበባትና ባህላዊ እሴቶች፣ ባህላዊ ሙዚቃዎችና ባህላዊ ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ቅርሶች ለበዓሉ ታዳሚዎች ቀርበዋል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopiq
ከባህር ዳር...

"ሰላም ጸግሽ እንዴት ነህ? የዛሬው የባህርዳር እና የደደቢት ጨዋታ ፍጹም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት የተንጸባረቀበት ነበር!! የባህርዳር ደጋፊም ለ ደደቢት ክብር ሰጥቶ ሲያጨበጭብ ነበር!! አንድ የደደቢት ተጫዋችም፡ሜዳውን እየዞረ ህዝቡን ፍቅር ሲያሳይ ነበር!! እናም በጣም ደሥ ብሎናል!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊ሰላም🕊

ሚዲያዎች ለሀገሪቱ #ሰላም የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒሰቴር ዴኤታዋ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ምሁራን ትውልድን በእውቀት በማነፅ ሰላምን ይገነባሉ" በሚል መሪ ቃል በምሁራን በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ከማህበረሰብ ጋር በመሆን የሚጠበቅ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታዋ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የህብረተሰቡ አንድ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው የሰላም ሚኒስተር ደግሞ ይሄን በማሰብ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡

በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ በዋናነት ሰላም በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በተለያዩ ምልከታዎች አብራርተውታል፡፡ በፅሁፉ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ምሁራንና ተማሪዎች ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱም ሰላምን ማስፈን የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ላይ በተፈጠረ #ፍንዳታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ገደማ በተፈጠረው ፍንዳታ ከ50 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 12ቱ የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሑበርት የተባለው የዳቦ መጋገሪያ ፍንዳታው በተከሰተበት ቅፅበት ክፍት እንዳልነበር የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ፍንዳው በተከሰተበት ወቅት ጋዝ ከዳቦ መጋገሪያው እየወጣ ነው የሚል ጥቆማ የደረሳቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞች መፍትሔ ለመፈለግ ወደ ቦታው በመጓዝ ላይ ነበሩ። አደጋው ሲከሰት ቢጫ ለባሾቹ ተቃዋሚዎች መንግሥትን ለመተቸት አደባባይ ወጥተው ነበር።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጁልየስ ማዳባዮ ጋር በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞው የጤና ሚኒስትር ዶክተር #ከሰተብርሃን ‘የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ። ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ የአፍሪካ ባለራዕይ መሪዎች አጋር በማድረግ በአህጉሩ ልማት፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት፣ የሰለጠነ ሰው ልማት፣ ትምህርት ለምርታማነት እንዲውል እና በወጣቶች የስራ ዕድል ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ነው።

via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዛሬ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አካባቢዎች በትናንትናው እለት ተከስተው የነበሩት ግጭቶች መረጋጋት አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን በምዕራብ ጎንድር ዞን መተማ ወረዳ ከገንዳውኃ ከተማ በስተ ደቡብ ምስራቅ በኩል በምትገኘዋ ሽንፋ ቀበሌ አሁንም ግጭቱ #አልበረደም፡፡ ከሁለቱም የታጠቁ ሀይሎች (ከቅማንትና አማራ) ወደ ቦታው እየተንቀሳቀሱ ተጨማሪ ግጭት የፈጠሩ ነው፡፡ በዚህ ግጭት ሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ወደስፍራው በመንቀሳቀስ ግጭቱን ለማብረድ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

Via Asemahagn Aseres
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ #አይታገስም፡፡" ኢ/ር ታከለ ኡማ
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች የስራ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለብክነት የተጋለጠ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

በግንባታ ላይ ያሉ ነባር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ውስጥ የማይጠናቀቁ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ያሳወቁት ኢ/ር ታከለ ኡማ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ የተሰጧቸውን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ያልቻሉ እና የህዝብን ሃብት ለከፍተኛ ብክነት እየዳረጉ ያሉ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች በቀጣይነት የከተማ አስተዳደሩ በሚያሰራየው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ እንደማይታገስም አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡት ግንባታዎች በአስቸኳይ ኦዲት ተደርገው ለከተማ አስተዳደሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ አጠናቅቀው እንዲያስረክቡ አሳስበዋል፡፡

via Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia