TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ነው። የም/ ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ፦ - ከኦነግ ሸኔ፣ - ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ - ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ - ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ - ወደ አዲስ…
#ፓርላማ

" እነኚህ ሰዎች ሰላም ቢኖር ምን ያጣሉ ? #ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? #ከኦነግ_ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? "

ዶክተር ከፈና ኢፋ (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ?

" .... በኦሮሚያ ክልል ጦርነት በኢኮኖሚ ላይ በፖለቲካ ላይ ፣ በማህበራዊ ህይወት ላይ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት እና ጉዳት ዘርዝሬ መጨረስ አልችልም፤ ህዝብ ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ህዝባችም በጣም እየተንገላታ ነው፤ በቅርቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ታጥቆ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቅርቦላቸዋል፤ ይሄ የሰላም ጥሪ ምን ላይ ደርሷል ? ጅምሩ ምን ይመስላል ? ህዝባችን በአሁን ጊዜ በጉጉት አይደለም እየጠበቀ ያለው ይሄን የሰላም ድርድር በፀሎት ጭምር ነው በፆም በፀሎት ጭምር የዚህን ድርድር መጀመር እየጠበቅን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ስለዚህ #ሰላም ለተጠማው ህዝባችን ሰላም ለማውረድ በዚህ ረገድ መሬት ላይ ምን እየተሰራ ነው ?

ከኦነግ ሸኔም ጋር ይሁን ከህወሓት ጋር ለተደረገው የተሳካ ስምምነት ኢትዮጵያውያን ሆነው የሚቃወሙ ሰዎች አሉ፤ ይሄን የሚያደርጉት ከውሥጥም ከውጭም ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሰላም ከምንም በላይ ብሄራዊ ጥቅማችን ነው ፤ ኢትዮጵያውያን ሆነው ከራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም በተፃራሪነት መቆም ትርጉሙ ምንድነው ? ምን ለማግኘት ነው ? ምን ለማጣት ነው ?

እነኚህ ሰዎች ምን ያጣሉ ሰላም ቢኖር ? ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? ከኦነግ ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? መፈናቀል ነው የሚቀረው ፣ ተጨማሪ የሰው ስቃይ ነው የሚቀረው ፣ የንብረት መውደም ነው የሚቀረው፣ የመሰረተ ልማት መውደም ነው የሚቀረው ይሄን የሚቃወም ኢትዮጵያዊ ምን አይነት ኢትዮጵያዊ ነው ? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አመሰግናለሁ !! "

@tikvahethiopia