TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል~ሀዋሳ🔝

"ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተካሄከው ሰለማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ ላይ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ፦ “ህገ መንግስቱ እንዲከበር፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ እንዲሰጠው፤ የሪፈረንደም ቀን በአስቸኳይ ተወስኖ ለህዝብ እንዲነገር ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፦

•ሲዳማነት ከሌለ #ኢትዮጵያዊነት የለም!

•ለውጡን እንደግፋለን!

•በኮሚሽን የሚመለስ ጥያቄ የለንም!

•ለማንም ዘረኛ የማንበረከክ በባህላችን የምንኮራ ህዝን ነን!

•ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር!

•የሪፈረንደም ቀን #ተቆርጦ ይነገረን!

•የሲዳማ ህዝብ መንግስትን እንዳከበረ መንግስትም የሲዳማን ህዝብ ያክብር!

•ሁሉንም #ብሄር እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•ሁሉንም #ሀይማኖት እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•የሁሉንም #ባህል እንወዳለን፤ እናከብራለን! የሚሉት ይገኙበታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አልሞትኩም፤ ሞቴን ለተመኛችሁ እንሆ አልተሳካላችሁም" አባ ወ/ሰንበት ገ/ሚካኤል

በጅማ ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ ተካሂደዋል። በዛሬው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች አንገታቸው #ተቆርጦ ሞተው ተገኙ ተብልው ሲናፈስ የነበረው አባ ወ/ሰንበት ገ/ሚካኤል ኮንፍረንሱ ላይ በመገኘት "እኔ አልሞትኩም! ሞቴን ላለማችሁ እንሆ አልተሳካላችሁም" በማለት የሀሰት ወሬ አራጋቢዎች ብሎም የግጭት እና ውድቀት ናፋቂዎች አላማ እንደማይሳካ እና ጅማ በምታወቅበት ፍቅር እና አንድነትዋ እንደ ምትዘልቅ አስገንዝበዋል። የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች ጅማ ለህዝቦችዋ ፍቅርን እንጂ መከፋፈልን የምትለግስ ከተማ አይደለችም በማለት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰላማችንን በአንድነት ጠብቀን ለዘላቂ ልማት እንተጋልን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia