TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢንጅነር ታከለ ኡማ⬆️

ህብረተሰቡን ያሳተፈ #አዲስ የቤት ልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ ይደረጋል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ። ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ያለውን የግብአት እጥረት ለመፍታት የሚያስችሉ አማራጮችን በመጠቀም እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ተጠናቀው ለነዋሪዎች በፍጥነት እንዲተላለፉም #አሳስበዋል

◾️ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ #ቦሌ_ሀያት ሳይት በግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 ቤቶችን የግንባታ አፈፃፀም #ተዘዉዋረዉ ተመልክተዋል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ #ቦሌ አካባቢ የተፈጠረውን ክስተት በቂ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን አሰባስቤ እንደጨረስኩ ወደእናተ አድርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ፦

#ከመገናኛ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

የአዲስ አበባ መገዶች ባለስልጣን ፤ የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍልና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Credit : AARA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ታዳጊ ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24/ 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ #ከመስቀል፣አደባባይ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የትራፊክ መብራቶችና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር ፖሊስ አመልክቷል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ለይ ተሳትፈው የተገኙት ህፃናቶች መሆናቸውን ገልጿል።

በዚህ መነሻ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን አሳውቋል።

" አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ እንዲሁም ደግሞ እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ የወንጀል ተግባራት እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው በትራፊክ መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙ እና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል " ሲል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia