TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ደቡብ አፍሪካዊ ዜግነት ያለው ተከሳሽ በፈፀመው #የተከለከሉ ዕጾችን በሆዱ ውስጥ እና በመፅሔት መልክ አዘጋጅቶ ማዘዋወር ወንጀል ተከሶ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ልዩ ፍቃድ ሳይኖረው ከብራዚል ሳኦፖሎ ተነስቶ ወደ ከቶኒ በሚጓዝበት አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ከምሽቱ 1፤00 ሰዓት ሲሆን በኢትዮጵያ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራዚት ባረፈበት ወቅት አደገኛ እፅ ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርጉ የፌዴራል ፖሊስ አባላቶች ባደረጉት ፍተሻ በሆዱ ውስጥ ደብቆ የያዘው በፕላስቲክ የተጠቀለለ ብዛት 73 ጥቅል ፍሬዎች እና በሶስት መፅሔት መልክ የተዘጋጀ ብዛቱ 3,999 ሲሆን በአጠቃላይ ላይ 4,072 ፍሬ ወይም 410 በግራም ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ወደ ሌላ ሀገር ለማሳለፍ በማሰብ ይዞ የተገኘ በመሆኑ ተከሳሽ በመፈፀመው የተከለከሉ አደገኛ የኮኬን እጾችን ማዘዋወር የወንጀል ሕግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሽ ክሱ ደርሶት እና በችሎት ተነቦለት እንዲረዳዉ ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልቃወምም ፈፅሜለሁ በማለት ጥፋተኝነቱን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ዐቃቤ ሕግም ተከሳሽ ድርጊቱን ያመኑ በመሆኑ ጥፋተኛ እንዲባል አመልክቷል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በማለት ጥፋተኝነቱን ማመኑን፣ሪከርድ የሌለበት መሆኑን እና ሌሎች ማቅለያዎችን በመቀበል ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ8 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ-የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ‼️

#የሲዳማ_ክልል_ጥያቄ የሕዝቤ ውሳኔ ቀን መዘግየት አስመልክቶ በቀን 14/6/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው ሰልፍ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት #ማጠናቀቁን የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በጋራ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሰልፉ ዓላማ የሲዳማ ሕዝብ በክልልነት የመደራጀት መብት አስፈላጊውን ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ በቀን 12/3/2011 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢቀርብም እስከ አሁን ድረስ ሕዝቤ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን ተወስኖ ምላሽ ባለመሰጠቱና በመዘግየቱ የሚካሄድ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅም ተችሏል።

"ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር" በሚል መሪ ቃልና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ በዕለቱ ከጧቱ 1:00-6:00 ሰዓት ድረስ መነሻውን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገ በሲዳማ ዞን አስተዳደር- በአሮጌው መናኸሪያ -በተስፋዬ ግዛው ሕንጻ-በመሳይ ሆቴል አቋርጦ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሳረጊያ የሚደረግ ይሆናል።

በሰልፉ ላይ ከሲዳማ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ ሰልፈኞች የሚሳተፉ መሆኑን በመግለጽ ሰልፉም በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከተለያዩ ፀጥታ አካላትና ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጫው አክሏል።

ኀብረተሰቡም ይህን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የራሱንና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ማንኛውንም ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለፀጥታ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ: በሰላማዊ ሰልፉ መነሻ-መድረሻ እንዲሆኑ በተፈቀዱ መንገዶች ላይ ማንኛውም ዓይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑንና የሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለትራፍክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከዚህ ውጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል የከተማውን ኀብረተሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ህደቱን ማወክ የተለያዩ #የጦር_መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ የተከለከሉ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኙ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ኃላፊዎቹ በመግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በማጠቃለያም ሕዝባዊ ትዕይንቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰራ በድጋሚ ጥሪ በማቅረብ ኃላፊዎቹ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ~ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#በቡድንም ሆነ #በተናጠል የሀዋሳ ከተማ ኀብረተሰብን #ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ሂደቱን ማወክ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣ በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ #የተከለከለ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኝ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል።

#ሲዳማሪፈረንደም2011 #ሀዋሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia