TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአገሪቱ #አንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ #ግጭቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህንን ሚናቸውን እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩና #ተቀባይነታቸውም በመቀነሱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አለመሆኑን ባሙያዎች ተናግረዋል።

ሙሉውን አንብቡት...
https://telegra.ph/የሐይማኖት-አባቶችና-የአገር-ሽማግሌዎች-ሰላም-የመፍጠር-ሚና-ኮስሷል-01-14
መንገዱ ድጋሚ ተዘጋ!

#ከሀረር ወደአዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ድጋሚ #መዘጋቱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

በስልክ ያነጋገሩት የቤተሰባችን አባል ይህን ብሏል፦

"ከሀረር ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነበር አዋሽ ላይ/ወደ ጅቡቲና አዲስ አበባ #መገንጠያ ላይ መንገድ ተዘግቶ ቆመናል። አስፓልቱ ላይም ጎማ እየተቃጠለ አይተናል። #አንዳንድ መኪኖች #ወደሀረር እየተመለሱ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጽያ የሚድያ ህግ ከሴቶችና ህጻናት መብቶች አንጻር በሚል ርዕስ ከሚድያ አካላት እና ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ የኢትዮጵያ የሚድያ አዋጅና ድንጋጌዎቻቸው ከሴቶች እና ህጻናት ጥበቃ አንጻር የተቀመጡት ድንጋጌዎች የቀረቡ ሲሆን ቢሮው የሰራቸውንና በመስራት ላይ ያለው ስራ ቀርቧል።

ቢሮው ፦
👉 ለዓመታት ስትደፈር ስለቆየች ሴት፤

👉 በአባታቸው ስለተደፈሩ ልጆች፤

👉 ተገለው በመንገድ ስለተጣሉ ልጆች እና  ሌሎችም በመዲናዋ (አዲስ አበባ) የተከሰቱ ዘግናኝ ኬዞችን እየተከታተለ እንዳለ አሳውቋል።

#አንዳንድ ሀኪሞች፣ መምህራን፣ መንገደኞች ፣ ሚድያዎች እና ሌሎችም በሴቶችና ህጻናት ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ መካከል እንደሚመደቡም ተነግሯል።

በመድረኩ በሀገሪቱ የሚሰሩ ፊልሞችና ማስታወቂያዎች ለአብነትም የዳይፐር፣ የሳሙና፣ የማድ ቤት እቃዎችና ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይ የሚሰሩት ሴቶች መሆናቸውን በመጠቆም የማስታወቂያዎቹ አሰራርም የሴቶችን አቅም የሚያዳክምና መሰል ኃላፊነቶች የእነሱ ብቻ መሆናቸውን አመልካች በመሆኑ ሊስተካከል እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም የኪነጥበብ ስራዎች የሴቶችና ህጻናትን መብቶች የሚያከብሩ እና ክብራቸውን የሚጠብቁ ሊሆኑ እንደሚገባና ሚድያውም የራሱን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው " - ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከዓላማው ውጪ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" ... ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ #አንዳንድ_ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ #ሰላም እና #ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ #ደም እና #ላብ በግልፅ አሳይታለች።

- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድንበር ተጋርተው የሚኖሩ ጎረቤቶች ብቻ ሳይሆኑ የጋራ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል እና ህዝብ የሚጋሩ ወንድማማች ሀገራት ናቸው።

- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ጠንካራ ናቸው ፤ እጣ ፈንታችን የማይነጣጠል ነው።

- ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት የሚሆን የባህር አገልግሎት የሚሰጥ የትብብር እና አጋርነት ስምምነት ነው። ስምምነቱ በየትኛውም ሀገር ላይ ሉዓላዊነትን የሚጥስ / የሚገዳደር / በግዳጅ የየትኛውንም ሀገር ሉዓላዊነት የሚረግጥ አይደለም።

- እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ አንዳንድ ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ያነሳሳቸው ለሶማሊያ ያላቸው ወዳጅነት ሳይሆን #ለኢትዮጵያ_ያላቸው_ጥላቻ / የጠላትነት ስሜት መሆኑ ግልጽ ነው።

- እነዚህ ተዋናዮች አጀንዳቸው የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ፣ መረጋጋት እና ደህንነት አይደለም። ሊዘሩ የፈለጉት #አለመግባባት እና #ትርምስን ነው። እየታየ ያለው ነገር ውጥረት የሚያባብስ እንዲሁም ደግሞ አጋጣሚውን ለመጠቀም ለሚፈልጉ የውጭ ተዋናዮች ፍላጎት ብቻ የሚያገለግል ነው።

- ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመስረተ ሁሉን አቀፍ ቀጠናዊ ትስስርን ለመፍጠር ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በትብብር መንፈስ ለመስራት እየጣረች ነው።

- ኢትዮጵያ ውጥረትን ከሚፈጥሩና ከሚያባብሱ መግለጫዎች፣ ንግግሮች እና ትርክቶች ይልቅ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ በጽኑ ታምናለች።

#AmbassadorRedwanHussien #X

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ…
#ሙሉ_ቃል

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ምን አለ ?

" ' ግደሉ ብሎ ' ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል እና ቅዱስ ሲኖዶስን የማይመጥን ንግግር ነው " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በንባብ ያሰሙት ፦

" በአሁኑ ሰዓት ላይ ትልቅ ተግዳሮትና የፈተና ምንጭ በመሆን ቤተክርስቲያናችንን ዋጋ እያስከፈሏት ያሉትን የአንዳንድ አባቶች መግለጫ እና የአውደ ምህረት ትምህርቶች እንደ አብነት በመጥቀስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰፊው ተወያይቷል።

በውይይቱ የተለዩ ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- አብዛኛው የአውደ ምህረት ስብከቶቻችን ከትምህርተ ወንጌል ይልቅ የነገር እና የደረቅ ትችት መድረክ እየሆኑ መምጣታቸው ፤

- በተለይም በመዋቅር ውስጥ የስራ መደብ የሌላቸው ተዘዋዋሪ " #ሰባኪ_ነን_ባዮች " የወገንተኝነት እና የፖለቲካ ትችትን እንደ ተከታይ ማፍሪያ በመቁጠር በሚዘሩት ፍጹም ከቃለ ወንጌል የራቀ ዘር ቅድስት ቤተክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑ ፤ ይህን ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ አህጉረ ስብከት ላይ ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተፈጠረ መሆኑ ፤

- በተለይም ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበትና ምእመናንም በተሰበሰቡበት እንደ ቀኖና ቤተክርስቲያን ዕለቱን አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርተ ወንጌል ከመስጠት ይልቅ ቤተክርስቲያንን የማይመጥን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን የተከበረ ጠቅላይ ሚኒስትር ፦

° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " የሚሉ ህገወጥ እና ክብረነክ የሆኑ ንግግሮች በመናገር በፈጸሙት ያልተገባ ተግባር በቤተክርስቲያኒቱ እና በመንግስት መካከል የነበረውን ግንኙነት በማሻከር ቤተክርስቲያንን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ከመሆኑ በላይ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶችን ክብር እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ ያደረገ ተገቢነት የሌለው አድርጎት መሆኑን፤

- ክብር ይግባውና ጌታችን፣ አምላካችን መድሃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ቁጥር ሰላሳዘጠኝ ላይ እንደተናገረው " እኔ ግን እላችኋለሁ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግመህ አዙርለት " ብሎ ያስተማረውን አብነት አድርጋ አትግደል የሚለውን ህገ ኦሪት አጽንታ እያስተማረች እስካሁን ድረስ ጸንታ በቆየችው እናት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ " ብሎ ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክልና ቅዱስ ሲኖዱስን የማይመጥን ንግግር መሆኑን ፤

- ልክ እንደ አቡነ ሉቃስ ፈጽሞ ጫፍ የረገጠ ባይሆንም ሌሎችም #አንዳንድ_አባቶች በተለያዩ ቦታዎች ያስተላለፏቸው መልዕክቶች አግባብነት የሌላቸውና ቤተክርስቲያንን ለትችት የዳረጉ መሆናቸውን ምልዓተ ጉባኤው በዝርዝር ገምግሟል።

ውሳኔ ፦

1ኛ. ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ ፣ ዘርህ ይጥፋ፣ የአድማ ብተና ይበትንህ " ... ሌሎች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆኑ ንግግሮች ቤተክርስቲያኒቱንም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል ከቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ እና ቀኖና ውጭ የሆነ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር መሆኑ ፤

2ኛ. በቀጣይም እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ስህተት #በብዑጽነታቸው ሆነ በአንዳንድ አባቶች ሰባክያን ወንጌል እንዳይደገም ተፈጽሞም ቢገኝ ተገቢው የእርምት ውሳኔ ለመስጠት ይቻል ዘንድ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ አስመልክቶ ገዢ የሆነ ህገ ደንብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አገልግሎት መምሪያ እና በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ፤

3ኛ. ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ዕለት ጀምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ አህጉረ ስብከት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጸም ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ፤ ከክትትል እና ከቁጥጥር ጉድለት ምክንያት በየትኛውም የቤተክርስቲያኒቱ አውደምህረት ላይ ለሚተላለፉ የተሳሳቱና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች እና ንግግሮች በኃላፊነት የሚያስጠይቅ መሆኑን ለሁሉም ሀገረ ስብከት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ይህ ሙሉ ቃል የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ነው። "

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia