TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ‹‹የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ህዝብ እየሞተበት ያለ ጥያቄ እንደመሆኑ #በቀላሉ የሚታይ አይደለም›› ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ዶክተር #አምባቸው_መኮንን አስታወቁ፡፡ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትነት መታጨታቸውን ህዝቡ ባለመፈለጉ በፖለቲካ ተሳትፏቸው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል፡፡ አማካሪ ሚኒስትሩ ዶክተር አምባቸው መኮንን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በወልቃይትና በራያ አካባቢ የሚታየው ችግር በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፣ ለአገሪቱም የሰላም #መናጋት ምክንያት እየሆነ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ካልተፈታ ሁለቱ ክልሎችም ሆኑ አገሪቱ ሰላም አያገኙም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia