TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምንጃር ሸንኮራ----ፈንታሌ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራና በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌና በሦሰት ወረዳዎች መካከል በቦታ እና በግጦሽ መሬት ይገባኛል ምክንያት ሰሞኑን በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።፡ መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ የማረጋጋት ሥራ እየሠራ መሆኑም ተመልክቷል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአረርቲ ከተማ ነዋሪ በስልክ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በፊትም ከእሳር ግጦሽና ከውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አልፎ አልፎ ግጭቶች እንደሚስተዋሉ አመልክተዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በኢዶ፣ ፊናናጆ፣ ቂሌ አርባና ክትቻ በተባሉ አካባቢዎች የታየው ግን ከሁሉም የከፋ ነበር ያሉት እኚህ የዓይን ምስክር ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበርና በግጭቱም የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረትም ወድሟል ብለዋል፡፡ የመከላከለያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመግባቱ ተኩስ መቆሙንና አሁን አንፃራዊ ሰላም እየታየ እንደሆነም አረጋግጠዋል።

ስለአካባቢው ሁኔታ እንዲስረዱኝ ለምንጃር ሽንኮራን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይትባረክ አብርሀም ሰልክ ደውዬ ጠይቂያቸው ነበር። ነገር ግን ስብሰባ ላይ ነኝ በሚል ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልፈቀዱም።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው በበኩላቸው ከግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ በአካበቢው ግጭት አልፎ አልፎ እንደሚከሰት ጠቅሰው ይህም የዛው አካል ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ሌላ የተለየ ፍላጎት ያለው አካል ነገሩን አባብሶት ከሆነ እንደሚጣራም አስረድተዋል።

በግጭቱ ከአማራ ክልል በኩል ሦስት ሰዎች ተገድለዋል፣ ሌሎች 3 ደግሞ ቆስለዋል ነው ያሉት። በሌላው ወገን በኩል ያለውን ጉዳት እንደማያውቁም ለባህርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ጋር #በሚዋሰንባቸው በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በኦሮሚያ ፈንታሌና ቦሦት አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም መከላከያ ወደ አካባቢው እንዲገባ ተደርጓል። በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያም ሆነ የአማራ የጸጥታ አካላት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓልም ብለዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት አሁንም ቢሆን ችግሩ #በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በስምምነት እንጅ #ግጭት በመቀስቀስ ይፈታል ብሎ እንደማምንና በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ ኗሪዎችን ባካተተ መልኩ የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጠውም ይሠራል ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia